Main Article Content

Assessment of the Impacts of Tsetse and Trypanosomosis Control Activities in Dawuro Zone, Ethiopia


Temesgen Zekarias
Teferi Mandado
Geja Gechere
Assefa Kebede

Abstract

 


አህፅሮት


የገንዲ በሽታ በቆላ ዝንብ በተወረሩ አካባቢዎች ላይ ለእንስሳት ርባታ ሥራ ከፍተኛ ማነቆ ሲሆን በዳውሮ ዞንም ተመሳሳይ የሆነ ችግር እያስከተለ ይገኛል:: በቆላ ዝንብ በተጠቁ በዞኑ አከባቢዎች የተለያዩ የቆላ ዝንብና ገንዲ በሽታ መከላከያ ዜዴዎች ተግባራዊ ሲደረጉ ቆይቷል:: ይሁን እንጂ እነዚህ ዜዴዎች ያመጡትን ፋይዳ የሚያሣይ መረጃ የለም:: በዚህ ጥናት በአከባቢው በሽታው ያለበትን ደረጃ የሚገመግም የምርምር ዜዴ በመጠቀም ከሕዳር 2017 እስከ ሰኔ 2018 .. ድረስ ምርምር ተካሂዷል:: የጥናቱ ዋና ዋና ዓላማዎችም: የቆላ ዝንብና ሌሎች የገንዲ በሽታ አስተላላፊ ነፍሳት ስርጭትን ማሰስ እና በዞኑ ተግባራዊ የተደረጉ የመከላከያ ዜዴዎች ያመጡትን ፋይዳ መገምገም ናቸው:: የተለዩ ዓላማዎችን ለማሳካት የቆላ ዝንብ ማጥመጃ መሣሪያ በመትከል የቆላ ዝንብና ሌሎች የገንዲ በሽታ አስተላላፊ ነፍሳትን መለየት ተችሏል፡፡ የተዘጋጁ መጠይቆችም ለእንስሳት አርቢዎች ተሠራጭቶ መረጃዎች ተሰብስቧል:: የዚህ ጥናት ውጤት እንደሚያሳየው የቆላ ዝንብና ሌሎች የገንዲ በሽታ አስተላላፊ ነፍሳት መጠን በቅደም ተከተል 5.37 እና 0.39 ዝንብ/ትራፕ/በቀን ሆኗል:: የመከላከያ ዜዴዎች ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት የነበረው አማካይ የቆላ ዝንብ መጠን 0.17+0.38 ዝንብ/ትራፕ/በቀን ሲሆን ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ያሁኑ ጥናት ውጤት 5.50+0.51 ዝንብ/ትራፕ/በቀን ሆኖ ተመዝግቧል:: የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንደሚያሣዩት የመከለከያ ዜዴዎቹ ከተደረጉበት ጊዜ ጀምሮ ሳያቋርጡ እየተተገበሩ የቆዩ ቢሆንም ነገር ግን የዚህ ጥናት ውጤት እንዳረጋገጠው የቆላ ዝንብ መጠንና የበሽታው ሥርጭት ደረጃ እየጨመረ መጥቷል:: ስለሆነም የገንዲ በሽታ አስተላላፊ ነፍሳት ከቅርብ ርቀት ቀጥጥር የተደረገበትን ቦታ መልሶ በመውረር በሽታውን ሥርጭት የመጨመር ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል ቀጣይነት ያለው የተቀናጀ እና ሀገር አቀፍ የሆነ የቆላ ዝንብና ገንዲ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ዜዴዎች ግምገማና ክትትል መደረግ አለበት::


 


Abstract


African Animal Trypanosomosis is the major constraint of livestock production in tsetse infested areas of Ethiopia and is the major challenge in Dawuro zone. Various interventions have been applied to control the disease in tsetse infested areas. However, there is a shortage of information on the impacts of these control methods. A cross-sectional study was conducted from November, 2017 to June, 2018 with the aims of assessing the apparent prevalence of the diseases and density of tsetse flies and the impacts of applied control interventions. The trap deployment and questionnaire survey were conducted. The apparent density of tsetse and Stomoxys were 5.37 FTD and 0.39 FTD respectively. The overall mean vector density of pre-intervention was 0.17 + 0.38 while post intervention was 5.50 ± 0.51 respectively. The findings of the questionnaire survey showed that livestock keepers were familiar with ruminant trypanosomosis, its vectors as well as the effect of the major control interventions applied in areas. There are continuous control interventions applied in the area but the results show that the disease prevalence and apparent density were increasing. Therefore, a comprehensive national wise evaluation of the impacts of control interventions should be undertaken.


 


 


 


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605