Main Article Content

Factors Affecting the Profitability of Smallholder Common Bean Producers in Central Rift Valley of Ethiopia


Abebe Teshome
Sintayehu Hailu
Endeshaw Habte
Yared Deribe
 Berhanu Amsalu

Abstract

አህፅሮት

ቦሎቄ ከዋና ዋናዎቹ የጥራጥሬ ሰብሎች የሚመደብ ሰብል ሲሆን ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሁም ለአርሶ አደሩ የምግብና የገቢ ምንጭ በመሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያ በቦሎቄ ምርት የሦስተኛ ደረጃን ትይዛለች፡፡ በ2010 ዓ.ም. ሀገሪቱ 40 በመቶ የሚሆነውን የቦሎቄ ምርት ወደ አለም አቀፍ ገበያ ልካለች፡፡ ቦሎቄ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለው ሰብል ቢሆንም ሰፊ የሆነ የተሸሻሉ የቦሎቄ ዝርያዎች ስርጭት በተለያዩ ጊዜያት ቢከናወኑም በቅርብ ጊዜ በተለይም በመካከለኛው ስምጥ ሸለቆ ያሉ አርሶ አደሮች ወደሌሎች ሰብሎች ሲያዘነብሉ ይታያል፡፡ ከዚህ ችግር ጋር በተያያዘ ሁኔታ የቦሎቄ ምርት የትርፋማነት ጥናት አለመኖር የመረጃ ጉድለት ፈጥሯል፡፡ አብዛኞቹ ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች የሰብሉን የትርፋማነትና አዋጭነት ጥናት ያላደረጉ ሲሆን ጥናቱ ይህንን ጉደለት ለመሙላት ታስቦ የተተገበረ ነው፡፡ የአርሶ አደሩ ትርፋማነት ለማጥናት ይረዳ ዘንድ የቦለቄ አምራች በሆኑ አካባባዎች አርሶ አደሮች በተለየ የመምረቻ ዘዴ ተለይተው የቅኝት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የተሰበሰበውም መረጃ ቀለል ያሉ የመረጃ ቀመሮችና እና ለአዋጭነት አስተዋጽኦ ያለቸው ምክንያቶች ትንተና ተደርጎበታል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ከሆነ የአርሶ አደሩ ያልተጣራ ጠቅላላ ትርፍ በአማካይ 13486 ብር በሄክታር  ሲሆን ጠቅላላ የተጣራ ገቢ ደግሞ 8127 ብር በሄክታር ይሆናል፡፡ ለቦሎቄ ምርት ትርፋማነት አስተዋዕኦ ከሚያደርጉ አበይት ምክንቶች ውስጥ አርሶ አደሩ ከዋና ገበያ ያለው ርቀት፣ የአርሶ አደሩ የእድሜ ሁኔታ፣ የቤተሰቡ ቁጥር፤ ከግብርና ስራ ውጭ ያሉ ገቢዎች እና የማዳበሪያ ማግኛ ምንጮች አስፈላጊ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በአንጻራዊ መልኩ ሲታይ የወንድ አባወራ አርሶ አደሮች የተሻለ ትርፋማ ሲሆኑ፤ በግብርና ስራ ያለ ልምድ፤ በገበሬ ቡድን አባል መሆንና ምርቱ የተሸጠበት የገበያ ሰንሰለት ዓይነቶች አዎንታዊ በሆነ መልኩ ተጽዕኖ የሚሳድሩ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም የቦለቄ አምራች አርሶ አደሮችን ትርፋማነት ለመጨመር፤ አዎንታዊ ምክንያቶችን ከፍ ማድረግና አሉታዊ ምክንያቶችን በመቀነስ የፖሊሲ እርምጃዎችን ማቀናጀት ያስፈልጋል፡፡


 


Abstract

Common bean is one of the major pulse crops which played an important role in the Ethiopian national economy and to farmers as food and cash income. Ethiopia ranked third in common bean production in Eastern and Southern Africa. The country exported 40 percent of its total common bean production in 2010. Despite the wide dissemination of improved common bean varieties and its economic importance, there is a dearth of information on the profitability of smallholder farmers from common bean production. Most of the previous studies on common bean did little on the profitability of smallholder bean producers. This study is designed with the aim of assessing the profitability status of smallholder common bean producers and factors correlated with it. Sample bean producers were selected randomly using simple random sampling. The cross-sectional data collected from sampled households are analyzed using descriptive statistics and Ordinary Least Square (OLS). The result of the study shows that the mean common bean gross margin and net farm income was 13486 and 8127 Birr/ha respectively. Distance from the nearest market, Age, Family size, off farm income and fertilizer source are the factors influencing the profitability of smallholder common bean producers negatively. However, Gender, farm experience, group membership and target market channel had a positive significant influence on smallholder based common bean production profitability. Therefore, in order to enhance the profitability of smallholder households, among others, it is important to improve access to input and output market and collective actions by farmers. There is also a need to minimize the gender gap in the profitability through affirmative action such as the provision of special credit and access to modern technologies by female farmers.   


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605