Main Article Content
Spatial Distribution of Enset Bacterial Wilt (Xanthomonas campestris Pv. musacearum) and its Association with Biophysical Factors in Southwestern Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
የእንሰት አጠውልግ በሽታ በዛንቶሞናስ ካምቴስትሪስ ፓቶቫር ሙሳሴረም በሚባል የባክቴሪያ ተህዋስያን አማካኝነት የሚከሰትና በኢትዮጵያ ውስጥ እንሰትን ከሚያጠቁ በሽታዎች ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ አደገኛ በሽታ ነው፡፡ የዚህ ጥናት አላማ በደቡብ ምዕራብ እንሰት አብቃይ አካባቢዎች ላይ የዚህን በሽታ ስርጭትንና በሽታው በአካባቢው በሚለዋወጡ ከሥነ-ሕይዎታዊና ሥነ-አካላዊ ነገሮች ጋር ያለውን ዝምድና ለማጥናት ነው፡፡ ለዚህም በ10 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ የ120 የእንሰት ማሳዎች ውስጥ የዳሰሳ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በበሽታው የተጠቁ የእንሰት መጠን (Incidence) በአማካይ በወረዳዎች መካከል 23.67- 31.92 በመቶ ነው፡፡ እንደዚሁም የበሽታው የጥቃት መጠኑን በተመለከተ (Severity) ከፍተኛ የሆነ ጥቃት (62.50 በመቶ) በሰሜን ቤንች ወረዳ የተመዘገበ ሲሆን በአንድራቻ ወረዳ ዝቅተኛ የጥቃት መጠን (49.58 በመቶ) ተመዝግቧል፡፡ ሎጅስቲክ ሪግሬሽን ሞዴል እንደሚያስረዳው የእንሰት አጠውልግ በሽታ ስርጭቱ ከ25 በመቶ በላይ ሆኖ የመገኘት አጋጣሚው የእንሰት ማሳ የአፈሩ pH ከ5.5 - 7 መሆን፣ የእንሰት ሰብል ብቻ በአንድ ማሳ ውስጥ መትከል፣ በሽታ ተቋቋሚ ያልሆነ የእንሰት ዝርያ፣ ዝርያውን ከሌላ አርሶ አደር ማሳ መጠቀም እና ምንም ዓይነት አረም ማረምና የበሽታ መከላከያ ያልተካሄደበት ማሳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የበሽታ ጥቃት መጠን ከ55በመቶ በላይ የመሆኑ አጋጣሚ የአየር ፀባይ የሰሜን-ቤንችንና የየኪ ወረዳዎችን የሚመስሉ አካባቢዎች፣ አረም በሚታረምበት ወቅት እንሰትን በገጀራ መቁረጥ፣ ተቋቋሚ ዝርያ ያልሆነ የእንሰት ተክል፣ የእንሰቱ ዕድሜ ከመካከለኛው እስከ ምርት ለመስጠት ያለው ጊዜ፣ የአርሶ አደሩ ለበሽታው ያለው ዝቅተኛ ግንዛቤ ናቸው፡፡ የዚህ ዳሰሳ ጥናት ግኝቶች እንደሚያመለክቱት የእንሰት አጠውልግ በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ላይ የተሰራጨ ሲሆን የስርጭቱን መጠን ለመቀነስ እንሰትን እንደ አንድ አማራጭ የማሳው አፈሩ pH ከ5.5 እስከ 7 መካከል ውጪ መትከል፣ ከሌላ ሰብል ጋር አቀላቅሎ መትከል፣ በእንሰት ማሳ ውስጥ የምንጠቀምባቸውን የመገልገያ መሳሪያዎችን ማፅዳትና መጠቀም፣ በበሽታ የተጠቃውን ከማሳው ነቅሎ ማውጣትና ማቃጠል፣ የባለሙያ ምክር መጠቀም መቻል እና በአርሶ አደሮች መካከል የእንሰት ዝርያ መለዋወጥ እንዳይኖር ማድረግ ናቸው፡፡
Abstract
Enset (Ensete ventricosum) bacterial wilt (EBW), caused by Xanthomonas campestris pv. musacearum, is one of the highly destructive diseases of enset in Ethiopia. Field survey was conducted to determine the distribution of EBW and its association with biophysical variables in Southwestern Ethiopia. In the survey, 120 enset fields in 10 major enset growing districts were assessed. The mean disease incidence across districts ranged from 23.67 to 31.92%, and significantly different levels of disease severity were recorded among districts. Thus, among districts, the highest mean disease severity of 62.50% was recorded from Semen-bench, whereas Andiracha district showed the lowest (49.58%) mean severity. Logistic regression analysis indicated that EBW incidence of >25% had high probability of association with enset grown on soils with pH of 5.5-7, sole cropped, susceptible clones, using planting materials obtained from other farmers and enset fields with no weeding and EBW management practices. EBW severity of >55% had high probability of association with growing enset in Semen-bench and Yeki districts, weed management through machete slashing, growing local susceptible enset clones, vegetative to maturity growth stages, and low to medium levels of farmer’s awareness about EBW. Findings of this survey indicate that EBW is widely distributed and could be minimized through growing enset preferably on soils out of pH 5.5-7 ranges, intercropping system, proper weeding, access to disease-free planting material, disinfecting farm tools before using, rouging out and burning of infected plants, accessing of advisory services, and limiting free exchange of planting material among enset growers.