Main Article Content
Evaluation of Oats (Avena sativa) Genotypes for Seed Yield and Yield Components in the Highlands of Gamo, Southern Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
የሲናር መኖ ዘር ምርታማነትን ለማሻሻል በ14 ዝርያዎች በኤዞ ኦቴ ሙከራ ጣቢያ ከ2008 እስከ 2009 ዓ.ም. የምርት ዘመን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የዘር ምርታማነት ግምገማ ተካሂዷል፡፡ ሙከራው የመሬትን ለምነት ባገናዘበ መልኩ ሶስት ጊዜ (three replications) ተደጋግሞ የተዘራ ሲሆን የተለያዩ የባህሪ መረጃዎችን በመሰብሰብ የዘር ምርታማነት ተገምግሟል፡፡ በዝርያዎች መካከል የታየው ልዩነት በመኖ ምርታማነት ILRI-15153A ሌላውን ዝርያ CI-8233 አስከትሎ ተክሎቹ ያላቸውን የቅጠል ብዛት፣ የቅጥያ ብዛት፣ የተክሉ ቁመት እና አጠቃላይ ምርት የተሻለ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ የተለያዩ ዝርያዎች የተለያየ የዘር ምርት መጠን የታየባቸው ሲሆን CI-8233 ዝርያ ILRI-5527A፣ CI-8251 እና ILRI-5526 አስከትሎ ከሌሎች አንፃር ከፍተኛ የዘር ምርት በኪሎ ግራም፣ የዘር ግንድ መጠን፣ የሺህ ዘር ክብደት እና ሃርቨስት ኢንዴክስ አስመዝግቧል፡፡ የሲናር ባህሪ መለኪያዎቹ እርስ በእርስ ያላቸው ቁርኝት ሲታይ የቅጥያዎች መጠን፣ የዘር ግንድ፣ ሺህ ዘር ክብደት እና ሃርቨስት ኢንዴክስ መጨመር በዘር ምርት ላይ ቀጥተኛ ጥቅም እንዳለው ታይቷል፡፡ አጠቃላይ የመኖ ምርታማነት ደግሞ ለማበብ ከሚፈጀው ጊዜ፣ ከተክሉ ቁመት እና የዘር ግንድ ርዝመት ጋር ቀጥተኛና ጠቃሚ ግንኙነት እንዳለው ታይቷል፡፡ በዚህ መሠረት የሲናር መኖ ለማምረት የሚፈልጉ አካላት ሙከራው በተደረገበት አካባቢና በተመሳሳይ ሥነ ምህዳር CI-8233, ILRI-15153A, ILRI-5527፣ CI-8251 እና ILRI-5526 ዝርያዎችን ለሲናር ዘር እና መኖ ምርታማነት ማሻሻያ እንደ አማራጭ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንደሚችሉ ተረጋግጧል፡፡
Abstract
The field experiment was laid out in a randomized complete block design with three replications to evaluate the seed yield performance of fourteen oat varieties at Ezo Ote during the main cropping seasons of 2016 and 2017. Varieties in the trial were ILRI-5431A, ILRI-5444A, ILRI-5490A, ILRI-5499A, ILRI-5526A, ILRI-5527A, ILRI-15152A, ILRI-15153A, ILRI-16101A, CI-8233, CI-2291, CI-8251, CI-2252 and CI-80AB2806. Data was recorded for days to flowering (DTF 50%), plant height, leaf number per plant, tiller number per plant, panicle length, seed per spike, 1000 seed weight, biomass yield, seed yield and harvest index. The varieties showed significant variations in yield and yield related parameters that ILRI-15153A followed by CI-8251 and CI-8233 varieties of oats had a higher number of leaves per plant, number of tillers per plant, plant height and biomass yield. CI-8233 followed by ILRI-5527A, CI-8251 and ILRI-5526A varieties had higher seed yield, optimum spike number, thousand seed weight and harvest index. Oats seed yield positively correlated with tiller number per plant, spike number, thousand seed weight and harvest index whereas biomass yield positively correlated with the days to flowering, plant height, panicle length and seeds per spike. Hence, ILRI-15153A, CI-8233 and CI-8251 for biomass yield whereas CI-8233, ILRI-5527A, CI-8251 and ILRI-5526A genotypes could be recommended for seed yield, in Ezo Ote and similar agro-ecology.