Main Article Content

በማጠቃለል ብልኃት ማንበብን መማር፣ አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ውጤታማነት የማሻሻልና የማስቀጠል ሚና፣ የፍትነትመሰል ንድፍ ክትትላዊ ጥናት


Aragaw Shibabaw
Marew Alemu
Agegnehu Tesfa

Abstract

This study examined the long-term effects of a summarizing strategy on reading comprehension and motivation. Following a previous quasi-experimental study, 51 eighth-grade students from the experimental group were assessed nine months later. Data collected through tests and questionnaires were analyzed using paired sample t-tests and multiple linear regression analysis. Results show a significant improvement in reading comprehension from the post-test to the follow-up assessment. While reading motivation remained significantly positive, it showed a slight decline. These findings indicate that the summarizing strategy has a lasting positive effect on reading comprehension. Additionally, both individual and interactive effects from the previous study emerged as significant predictors of follow-up achievements, with the interactive effect being notably stronger. To sustain and enhance reading motivation over time, ongoing support and strategies are recommended to help students monitor and regulate their learning experiences. The implications for educational practices and future research are discussed.


የጥናቱ ዋና ዓላማ በማጠቃለል ብልኃት ማንበብን መማር፣ አንብቦ በመረዳት ችሎታና በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ያለውን የረጅም ጊዜ ተጽዕኖ መፈተሽ ነበር፡፡ ጥናቱ ቀደም ሲል በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተሳታፊነት ከተከናወነ ፍትነትመሰል ጥናት የቀጠለ ክትትላዊ ጥናት (follow-up study) ነው፡፡ በቀደመው ጥናት ብልኃቱ አንብቦ በመረዳት ችሎታና በማንበብ ተነሳሽነት ላይ ጉልህ አዎንታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተስተውሎ ነበር፡፡ በዚህም በቀደመው ጥናት በፍትነት ቡድን ተሳትፈው ከነበሩ 51 የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ከዘጠኝ ወራት በኋላ አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውንና የማንበብ ተነሳሽነታቸውን በተመለከተ በፈተናና በጽሑፍ መጠይቅ መረጃዎች ተሰብስበው በጥንድ ናሙና ቲ-ቴስትና በኅብረድኅረታዊ ስልቶች ተተንትነዋል፡፡ የውጤት ትንተናው እንዳመለከተውም የክትትላዊው ጥናት ውጤቶች በፍትነትመስል ጥናቱ በድኅረትምህርት ከተመዘገበው ውጤት አንጻር አንብቦ የመረዳት ችሎታ በጉልህ ደረጃ ከፍ ብሎ የተገኘ ሲሆን የማንበብ ተነሳሽነቱ በጉልህ ነገርግን በአነስተኛ ነጥብ (.1959) ዝቅ ብሏል፡፡ በተጨማሪም የቀደመው ጥናት ድኅረትምህርት ውጤቶች በተናጠልም ሆነ በቅንጂት የክትትላዊውን ውጤት በጉልህ ደረጃ ተንባይ ሆነዋል፡፡ ውጤቶችን በመተንበይ ረገድ የቅንጅቱ ከተናጠላዊው ድርሻ ከፍ ማለቱ አንብቦ መረዳትን በመማር ሂደት ብልኃቱ ኹለቱን ተላውጦዎች ይበልጥ አብረው ተሰላፊ እንዲሆኑ የማድረግ እድል እንዳለው ያሳያል፡፡ ውጤቶቹም የማጠቃለል ብልኃት አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ተነሳሽነትን ውጤታማነት የማረጋጋትና የማስቀጠል ጉልህ ሚና አለው፤ የሚል አንድምታ ይኖራቸዋል፡፡ ብልኃቱ የማንበብ ተነሳሽነትን ይበልጥ እንዲያስቀጥል ግን ተማሪዎች የመማር ስሜታቸውን በግላቸው መቆጣጠርና መምራት እስኪችሉ ክትትልና ድጋፍ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ከዚህ በመነሳትም ትምህርታዊና ምርምራዊ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919