Main Article Content

ተረቶችን ተጠቅሞ መጻፍን ማስተማር የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂሎት ለማዳበር ያለው ሚና በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ የ2016 ዓ.ም የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት


Tsehay Hailemeskel Kassa
Lemma Nigatu
Wudu Melese

Abstract

This study investigated the effectiveness of using tales to enhance the writing skills of Grade 5 Amharic first language students. A quasi-experimental design was employed with two groups (experimental and control) of 47 students each, randomly selected from among 246 Grade 5 students attending Karagutu Primary School in Desse City, South Wollo Zone, in 2016 E.C. The experimental group received instruction using tales, while the control group followed conventional teaching methods. Pre- and post-test writing assessments were administered to both groups. The analysis of the pretest results t (92) = 0.400, p< 0.690) showed that there was no significant difference between the experimental and control groups. However, after the intervention, the analysis of the post-test results revealed a significant difference in writing skills between the experimental and control groups t (92) = 4.686, p< 0.05). These findings suggest that incorporating tales into writing instruction can be a valuable strategy for improving the writing skills of Grade 5 Amharic first language students. Therefore, it would be good for the concerned parties to use the method of teaching writing through stories to improve the writing skills of the students.


የጥናቱ ዓላማ ተረትን ተጠቅሞ መጻፍን ማስተማር የመጻፍ ክሂልን ለማዳበር ያለውን አስተዋጽኦ መመርመር ነበር፡፡ ለዚህ የሚረዱ መረጃዎች በቅድመ እና ድኅረ ትምህርት ፈተናዎች ተሰበስበዋል፡፡ ከፊል ፍትነታዊ የምርምር ዘዴን ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በካራጉቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ.ም በአምስተኛ ክፍል ይማሩ ከነበሩ 246 ተማሪዎች በተራ እጣ ናሙና የተመረጡ 94 (በሙከራ ቡድን 47 በቁጥጥር ቡድን 47) ተማሪዎችን በማሳተፍ ነው፡፡ የቅድመ ትምህርት መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ፣ ለሙከራ ቡድኑ ተረትን በመጠቀም፣ ለቁጥጥር ቡድኑ በመደበኛው መማሪያ መጽሐፍ በተለመደው መንገድ የመጻፍ ክሂል ትምህርት ተሰጥቶ በመጨረሻም የድኅረ-ትምህርት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የቅድመ ትምህርት ፈተናው የባእድ ናሙና ስሌት t (92) = 0.400,P< 0.690 መሆን በሙከራ እና በቁጥጥር ቡድኖቹ የመጻፍ ክሂል መካከል ልዩነት የሌለ መሆኑን አሳይቷል፡፡ በአንጻሩ የድህረ ፈተናው መረጃ የባዕድ ናሙና (Independent Samples T-test) ስሌት t (92) = 4.686፣ P<0.05 (.000) ውጤት በሙከራ እና በቁጥጥር ቡድኑ መካከል የመጻፍ ክሂል ልዩነት መኖሩን አመላክቷል፡፡ የጥናቱ ግኝትም ተረትን በመጠቀም መጻፍን ማስተማር ከተለመደው መጻፍን የማስተማሪያ ዘዴ በተሻለ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ማሻሻሉን አሳይቷል፡፡ ስለሆነም የሚመለከታቸው አካላት የተማሪዎቹን የመጻፍ ክሂል ለማጎልበት መጻፍን በተረቶች የማስተማር ዘዴን ቢጠቀሙ መልካም ይሆናል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919