Main Article Content
የታሪክ ፈድለተቃርኖ በየስንብት ቀለማት፤ ድኅረዘመናዊ ንባብ
Abstract
This study investigates the deconstruction of historical truth in Yesenibit Kelemat, literally translated as Farewell Colors. Employing a postmodern framework, the analysis utilizes concepts of textuality, historical metafiction, fabulation, and irrealism to demonstrate the novel's multifaceted depiction of history. Farewell Colors is positioned as a text that recontextualizes the past, weaving together elements of myth, legend, and diverse historical narratives (pre-modern and modern). Through this approach, the “grand narratives” of traditional history are fractured, privileging the emergence of “small narratives” and emphasizing the active interpretation between “events” and “epistemes” within specific ideological and cultural contexts. The study concludes that Farewell Colors dismantles the idea of a singular, objective historical truth, instead presenting a dynamic interplay between historical fact, fiction, and individual interpretations.
የዚህ ጥናት ዓላማ የታሪክን ዕውነት ፈድለተቃርኗዊ ጠባይ በየስንብት ቀለማት ውስጥ ተንትኖ ማሳየት ነው፡፡ በዘዴነት ፈድለተቃርኖን ተጠቅሞ የድኅረዘመናዊነትን የአተያይ ብዝኃነት (multiple perspective) እየታገገ በልቦለዱ ውስጥ የታሪክን አስተማስሎ ለማስተንተን ተሞክሯል፡፡ በድኅረዘመናዊ ልቦለድ ውስጥ ታሪክን ለማስተንተን የሚያስችሉ እንደ ቴክስታዊነት፣ የታሪክ ዲበልቦለዳዊነት (Historical Metafiction)፣ የታሪክ ፍጥርነት (historical fabulation) እና ብዝኃግህደት (Irrealism) እንደመነሻ መታገጊያነት አገልግለዋል፡፡ በጥናቱ የስንብት ቀለማት ታሪክን እንደ አሃድ ወስዶ በተለያዩ ክፍሎቹ ከድኅረዘመናዊነት አንጻር እንዳቀረበው ለመመልከት ተችሏል፡፡ በዚህም ታሪክ ከሚትና አፈታሪክ ጋር በአቻዊነት እንደሚዋደድ፣ የቅድመዘመናዊና ጊዜ ዘመናዊ የታሪክ ሐቲቶች በትይዩነት እየተስተጋዎሩ ከሁለቱም ቅሩንነት አዲስ ታሪካዊ ሐቲት እንደሚዋለዱበት፣ ምስለ ግሁድ ገጸባህርያት በአዳዲስ ታሪካዊ ሐቲቶች እንደሚከሰቱበት፣ የ3000 ዘመን የነጻነትና የቅኝ ግዛት በሚል የፖለቲካ ፈድለተቃርኖዎች እንደሚካተቱበት፤ በዚህም ታሪክ ብዝኃግሁድ፣ ፍጥር፣ ለትርጓሜ ክፍት የሆነና በአውድ የሚገራ “ቴክስት” እንደሆነ ለመመልከት ተሞክሯል፡፡ ስለሆነም፣ በየስንብት ቀለማት ውስጥ ታሪክ በየዘመኑ የሚገራና ከታላቅ ሐተታ ተናጥቦ የትንንሽ ተረኮች ጣጣ በ“events” እና “epistemes” መካከል በሚነቃ የተረክ ትርጓሜ (narrative interpretation) ኅልው እንደሚሆን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የየዘመኑ ሐቲት ይዞት የሚነሳው ርእዮተዓለማዊና ባህላዊ ቁመናዎች ታሪክን ሲገሩትም ተስተውሏል፡፡