Main Article Content
ግብረመልስ በተማሪዎች የመጻፍ ክሂልና ተነሳሽነት ላይ ያለው ተፅዕኖ፤ በ 7ኛ ክፍል ተተኳሪነት
Abstract
This study examined the impact of feedback on students writing skill and motivation. It is a quasi-experimental research and has four groups (three experimental and one control) of students. The study conducted in 2016 E.C. at Haik no.1 primary school and the subjects are 144 grade 7 students. The school and the grade level were selected by simple random sampling and students were assigned in one of the four groups randomly. Pre - post essay writing test and motivation measuring questionnaire were administered to gather the study data. Before the intervention both the experimental and the control groups have taken pre writing test and motivation questionnaire. As a result, there no significance difference among the groups in their writing skill and motivational level. Then all groups practiced the same writing activities for 10 weeks. The only difference among the group during the writing activities is that group one receive written feedback ; group two receive oral feedback , group three revive peer feedback, whereas group four receive no feedback for their essay. Finally, all groups took post writing essay test and motivation questionnaire at the same time. The first question is that does feedback (written, oral and peer) has an effect on student writing skill?. The date analyzed by using one waye anova. The result show that feedback has an effect on students writing skills (F,(3,140)=13.9, p=.000 ). Tukey post hock show that both Oral feedback (m= 32.75, sd= 5.9), and written feedback (m=30.35, sd=6.4) have positive significance effect on students writing skill, While peer feedback has no effect on students writing skill. The second question is that does feedback (written, oral and peer) has an effect on students’ motivation?. The analysis show that feedback has an effect (F(3,140) =8.0,p=.000) on students writing motivation. Written feedback (m= 70.4, sd=10.5) and oral feedback (69.8, sd=10.4) have significantly positive impact on students writing motivation, whereas peer feedback has no any effect on writing motivation. Therefore in order to improve students writing skill and motivation, teachers should give constructive written and oral feedback for their students’ essay.
የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ግብረመልስ በተማሪዎች የመጻፍ ክሂልና ተነሳሽነት ላይ ያለውን ተፅዕኖ መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ ከፊል ፍትነታዊ (quasi-experiment) ንድፍን የተከተለ ሲሆን፣ ሶስት የሙከራ ቡድኖች (ሙከራ ቡድን 1፣ ሙከራ ቡድን 2 እና ሙከራ ቡድን 3 ) እና አንድ የቁጥጥር ቡድን (ቡድን 4) ያሉት ባለአራት ቡድን ጥናት ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በ2016 ዓ.ም. በሐይቅ ቁጥር1 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ 144 የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የተመረጠው በቀላል ዕጣ ናሙና ዘዴ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ በዕድል ሰጪ ናሙና ዘዴ ተመርጠው በሙከራና በቁጥጥር ቡድን ተደልድለዋል፡፡ የቅድመና ድህረ ትምህርት የመጻፍ ክሂል ፈተና እና 20 የተነሳሽነት መለኪያ ጥያቄዎችን የያዘ የጽሑፍ መጠይቅ ለመረጃ መሰብሰቢያነት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ በዚህም የሙከራና የቁጥጥር ቡድኖቹ ተመሳሳይ የመጻፍ ተግባር ያከናወኑ ሲሆን፣ ቡድን 1 የጽሑፍ ግብረመልስ፣ ቡድን 2 የቃል ግብረመልስ፣ ቡድን 3 የጥንድ ግብረመልስ እየተሰጣቸው መጻፍን ሂደታዊ በሆነ መንገድ ተለማምደዋል፡፡ በአንጻሩ የቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች የጻፉት አንቀጽ ያለ ምንም የማስተካከያ ግብረመልስ በመደበኛው ዘዴ እየታረመ ተመልሶላቸዋል፡፡ የተገኙት መረጃዎች በነጠላ ናሙና ልይይት (one way anova) ተተንትነዋል፡፡ በዚህም ግብረመልስ በተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ላይ ተፅዕኖ እንዳለው (F,3,140=13.9, P=.000) የታወቀ ሲሆን፣ የቃል ግብረመልስ (m= 32.75, sd= 5.9) እና የጽሑፍ ግብረመልስ (m=30.35, sd=6.4) በተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ላይ ጉልህ አዎንታዊ ተጽዕኖ ያላቸው መሆኑ በቱኬይ ፖስት ሆክ ተረጋግጧል፡፡ የጥንድ ግብረመልስ ግን በተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡ በተጨማሪም፣ ግብረመልስ በተማሪዎች የመጻፍ ተነሳሽነት ላይ ተጽዕኖ ያለው ሲሆን (F,3,140=8.0, P=.000)፣ የጽሑፍ ግብረመልስ (m=70.4፣ sd= 10.5) እና የቃል ግብረመልስ (m=69.8፣ sd= 10.4) በመጻፍ ተነሳሽነት ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንዳላቸው በቱኬይ ፖስት ሆክ ተረጋግጧል፡፡ በአንጻሩ የጥንድ ግብረመልስ በተማሪዎች የመጻፍ ተነሳሽነት ላይ ተጽዕኖ እንደሌለው ጥናቱ አመልክቷል፡፡ በዚህም፣ መምህራን ቀጥተኛ የሆነ የጽሑፍና የቃል የማስተካከያ ግብረመልስ ቢሰጡ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል ማሻሻል ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም፣ ከመምህር የሚሰጥ የጽሑፍና የቃል ግብረመልስ የተማሪዎችን የመጻፍ ተነሳሽነት ይጨምራል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል፡፡