Main Article Content

ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች በተማሪዎች ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች ግንዛቤና በመጻፍ ችሎታ ላይ ያላቸው ተጽዕኖ፤ በዘጠነኛ ክፍል አማርኛ አፍፈት ተማሪዎች ተተኳሪነት


Remla Ahmed
Marew Alemu
Selomie Zewdalem

Abstract

This study investigated the direct and indirect effects of metacognitive writing strategies on students' metacognitive writing strategy awareness and writing performance. A quasi-experimental pre-test and post-test control group design was employed with 104 ninth-grade students from Memhir Akalewold secondary school. The experimental group received instruction in metacognitive writing strategies, while the control group followed conventional writing practices. Data were collected using writing tests and a metacognitive writing strategy awareness questionnaire. Structural equation modeling (SEM) was used to analyze the data. Results indicated that metacognitive writing strategies have significant positive direct effects on both metacognitive writing strategy awareness (β = .811, p < .001) and writing performance (β = .646, p < .001). Additionally, metacognitive writing strategies have a significant indirect effect on writing performance through metacognitive writing strategy awareness (B = 7.830, t = 16.269, p = .037). These findings suggest that incorporating metacognitive writing strategies into Amharic language teaching can enhance students' writing skills.


የዚህ ጥናት ዋና አላማ ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች በተማሪዎች ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች ግንዛቤና በመጻፍ ችሎታ ላይ ያላቸውን ቀጥተኛና ኢቀጥተኛ ተጽዕኖ መፈተሽ ነበር፡፡ ፍትነትመሰል ቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት ባለቁጥጥር ቡድን የምርምር ስልት የተከተለው ይህ ጥናት በደሴ ከተማ መምህር አካለወልድ ኹለተኛ ደረጃ ትምህርትቤት የተካሄደ ነው። የጥናቱ ተሳታፊዎችም በ2015 ዓ.ም. በዚሁ ትምህርትቤት ከዘጠነኛ ክፍሎች መካከል በቀላል የእጣ ንሞና በተመረጡ ኹለት የመማሪያ ክፍሎች የሚማሩ 104 ተማሪዎች ነበሩ፡፡ የፍትነት ቡድኑ ተማሪዎች የመጻፍ ትምህርቱን በልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች፣ የቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች በመደበኛው ሥርዐተትምህርት መሠረት ለ10 ሳምንታት ተምረዋል፡፡ ኹለቱም ቡድኖች ከምርምሩ በፊትና በኋላ ተመሳሳይ ቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት የመጻፍ ፈተና ተፈትነዋል፤ ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች ግንዛቤ የጽሑፍ መጠይቅም ሞልተዋል፡፡ በቅድመትምህርት መረጃዎች የቡድኖቹ የፆታ ስብጥር በካይ ካሬ ቴስት፣ የዕድሜ ተመጣጣኝነት በነጻ ናሙና ቲ-ቴስት እንዲሁም የመጻፍ ችሎታና ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች ግንዛቤ በባለብዙ ተላውጦ ልይይት ትንተና ተፈትሸው ቡድኖቹ ከተጠቀሱት ተላውጦዎች አኳያ ተመጣጣኝ ኾነው ተገኝተዋል። በድኅረትምህርት የተገኙ መረጃዎችም በመዋቅራዊ እኩልዮሽ ሞዴል ተተንትነዋል፡፡ የድኅረትምህርት የትንተና ውጤቱ እንዳመለከተው መጻፍን በልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች መማር የተማሪዎችን ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች ግንዛቤ (β = .811, t = 4.456, p < .001) እና የመጻፍ ችሎታን (β = .646, t = 6.3, p < .001) የማሻሻል ቀጥተኛ አስተዋፆ አለው፡፡ እንዲሁም፣ ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች በልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች ግንዛቤ አማካይነት የመጻፍ ችሎታን የማሻሻል ኢቀጥተኛ ሚና (B = 7.830, t = 16.269, p = .037) አላቸው፡፡ በመኾኑም፣ ልዕለአእምሯዊ የመጻፍ ብልኃቶች መጻፍን ለማስተማር ቢተገበሩ በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የሚያበረክቱት አስተዋፆ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919