Main Article Content

በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ፍላጎትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብልሃቶች (Transactional Strategies) ያላቸው ሚና፤ በሰባተኛ ክፍልተማሪዎች ተተኳሪነት


አበባ ሁሴን
ማረው አለሙ

Abstract

የጥናቱ ዓላማ የተሻጋሪ ብልሃቶች ትምህርት አንብቦ የመረዳት ችሎታንና የማንበብ ፍላጎትን የማጎልበት ሚና መመርመር ነው፤ጥናቱ በአይነቱ መጠናዊ ምርምር (Quantitative Resaerch) ነው፤ እንዲሁም ፍትነትመሰል (Quasi-Experimental) ስልት ላይ በመመስረት የሙከራና የቁጥጥር ቡድኖች ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ፈተና የምርምር ንድፍን (pre test post test control group design) መሰረት አድርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ በልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤት በ2011 ዓ.ም በሰባተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከሚከታተሉ አምስት ክፍሎች መካከል በተራ ዕጣ ናሙና ዘዴ በተመረጡ ሁለት የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚማሩ 120 (60 የሙከራና 60 የቁጥጥር ቡድን) ተማሪዎች ናቸው፡፡ የሙከራ ቡድኑ በተሻጋሪ ብልሃቶች ትምህርትና የቁጥጥር ቡድኑ በተለመደው አቀራረብ ዘዴ ለስድስት ሳምንታት ተምረዋል፡፡ በአንብቦ መረዳት ፈተናና በማንበብ ፍላጎት የጽሁፍ መጠይቅ በቅድመና በድህረትምህርት የተሰበሰቡት መረጃዎች እንደአይነታቸው ከተደራጁ በኋላ፣ በአማካይ ውጤት፣ በመደበኛ ልይይት፣  በልይይት ትንተና (ANOVA) እና በአበር ልይይት (ANCOVA) ተተንትነዋል፡፡ ከትንተናው በተገኘው ውጤትም የሙከራውና የቁጥጥሩ ቡድኖች በቅድመትምህርት የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውና በማንበብ ፍላጎታቸው ተመጣጣኝ ደረጃ ላይ የነበሩ ቢሆንም፣ በድህረትምህርት አንብቦ የመረዳት ችሎታ ፈተናና በማንበብ ፍላጎት መለኪያ በተገኘው ውጤት የሙከራው ቡድን በስታትስቲክስ ጉልህ የሆነ የመሻሻል  (P  0.05) ልዩነት አሳይቷል፡፡ ይህም የተሻጋሪ ብልሃቶች ትምህርት የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ፍላጎት የማጎልበት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዳለው አመላክቷል፤ ለወደፊቱም የተሻጋሪ ብልሃቶች ትምህርት ከዚህ ጥናት በተለየ የክፍል ደረጃ፣ በሌሎች ክሂሎችና ስሜታዊ ባህርያት ላይ ያለውን ተጽዕኖ የተመለከቱ ጥናቶች ቢደረጉ የተሻለ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919