Main Article Content

በልዕለግንዛቤያዊ ብልሃት ማንበብን መማር በአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ያለው አስተዋጽዖ፤ አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ በሚማሩ ተማሪዎች ተተኳሪነት


ዘሪቱ አስፋው
ማረው አለሙ
ሙሉጌታ ተካ

Abstract

ጥናቱ በአማርኛ ትምህርት ልዕለግንዛቤያዊ ብልሃትን መማር አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ የሚማሩ ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማሻሻል ያለውን አስተዋጽዖ መርምሯል፡፡ ጥናቱ የተከናወነው በፍትነት መሰል የምርምር ስልት ላይ የተመሰረተ የሁለት ቡድኖች (የፍትነትና የቁጥጥር) ቅድመትምህርትና ድህረትምህርት ፈተና የምርምር ንድፍን ተከትሎ ነው፡፡ ተሳታፊዎች በአርባምንጭ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርትቤት በ2010 ዓ.ም የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የፍትነት ቡድን ተሳታፊዎች (n= 30) በልዕለግንዛቤያዊ ብልሃት፣ የቁጥጥር ቡድን ተሳታፊዎች (n= 30) በነባር ማንበብን የማስተማር ዘዴ በአምስት ሳምንት ለ15 ክፍለጊዜ አንብቦ መረዳትን ተምረዋል፡፡ ከተሳታፊዎቹ በቅድመትምህርትና በድህረትምህርት በአንብቦ መረዳት ፈተና መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በቅድመትምህርትና ድህረትምህርት የመረጃ ትንተና መሰረት የፍትነት ቡድን ተሳታፊዎች ከቁጥጥር ቡድን ተሳታፊዎች ይልቅ የተሻለ (p < 0.05) የአንብቦ መረዳት ውጤት አስመዝግበዋል፡፡ በአጠቃላይ የጥናቱ ውጤት አንብቦ መረዳትን በልዕለግንዛቤያዊ ብልሃት መማር የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ የማሻሻል በስታትሰቲክስ ጉልህ አስተዋጽዖ እንዳለው አመልክቷል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919