Main Article Content

የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብልሀቶች ሚና፤ በሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት


አበባ ሁሴን
ማረው አለሙ

Abstract

የጥናቱ ዓላማ የአንብቦ መረዳት ችሎታንና የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት ረገድ የተሻጋሪ ብለሀቶችን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ የቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን ፍትነትመሰል (Quasi- expermental research) ንድፍን መሰረት አድርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በጎንደር ከተማ በልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርትቤት በ2011 ዓ.ም በሰባተኛ ክፍል ትምህርታቸውን ከሚማሩ አምስት ክፍሎች መካከል ከሁለት የመማሪያ ክፍሎች በተራ ዕጣ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 120 (60 የሙከራና 60 የቁጥጥር ቡድን) ተማሪዎች ናቸው፡፡ በአንብቦ መረዳትና በማንበብ ግለብቃት እምነት የጽሐፍ መጠይቅ የተሰበሰቡት መረጃዎች በገላጭ ስትስቲክስ፣ በልይይት ትንተና (ANOVA) እና በአበር ልይይት ትንተና (ANCOVA) ተተንትነዋል፡፡ በዚህም በድህረትምህርት አንብቦ የመረዳት ችሎታና በማንበብ ግለብቃት እምነት ውጤት የሙከራው ቡድን በስታትስቲክስ ጉልህ የሆነ የመሻሻል ልዩነት አሳይቷል፡፡ ይህም የተሻጋሪ ብልሃቶች  የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታና የማንበብ ግለብቃት እምነት የማጎልበት ሚና እንዳላቸው አመላክቷል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919