Main Article Content

በማስተማር ልምምድ ሂደት የፅብረቃ ክህሎት አላባዎች (Elements of Reflective Skill) አተገባበርና ተግዳሮቶች ትንተና፣ በ3ኛ ዓመት የአማርኛ ቋንቋ እጩ መምህራን ተተኳሪነት


አሰፋ ወረታ
አመራ ሰይፉ
ሰፋ መካ

Abstract

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በማስተማር ልምምድ ሂደት የፅብረቃ ክህሎት አላባዎች አተገባበርና በሂደቱ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መመርመር ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም ዓይነታዊ ባለብዙ ንጥል ጥናት ንድፍ (Qualitative Multiple Case Study Design) ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በደብረታቦር ከተማ በበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2014 ዓ.ም በአፄ ቴዎድሮስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ5ኛ ክፍል ላይ የማስተማር ልምምዳቸውን ያካሄዱ አራት የ3ኛ ዓመት የአማርኛ ቋንቋ እጩ መምህራን ናቸው፡፡ ለጥናቱ በ5ኛ ክፍል ላይ ለማስተማር ልምምድ የተመደቡ እጩ መምህራን በዓላማ የእጣ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ መረጃዎቹም በዕለታዊ የፅብረቃ ጽሑፍ፣ በምልከታና በቃልመጠይቅ ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በዓይነት በዓይነት ከተደራጁ በኋላም ከመሠረታዊ ጥያቄዎች አንፃር የተራኪ (Narrative Analysis) እና የንጥል አዋቃሪ (Cross-Case Analysis) ስልቶችን በማጣመር ተተንትነዋል፡፡ በትንተናው የተገኙ ውጤቶች እንደሚያመላክቱት፣ የጥናቱ ተሳታፊዎች የፅብረቃ ክህሎት አላባዎች አተገባበር ክፍተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በአተገባበር ሂደቱም ቢሆን፣ የጥናቱ ተሳታፊዎች በርካታ ተግዳሮቶች ያሉባቸው መሆኑን የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ በመሆኑም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች፣ አላባዎቹ ለፅብረቃ ክህሎት እድገት ያላቸውን አወንታዊ ሚና በመረዳት ተግዳሮቶችን ለመቀነስ የሚያስችሉ አሠራሮችን በመቀየስ ለእጩ መምህራኑ ተገቢ ድጋፍና ክትትል ሊያደርጉ ይገባል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919