Main Article Content

የድህረ ቅኝ ግዛት ጭብጦች ትንተና በመንግሰቱ ለማ ፀረ ኰሎኒያሊስት ተውኔት


አብዮት ዓለም
አየነው ጓዱ

Abstract

ይህ ጥናት “የድህረ ቅኝ ግዛት ጭብጦች ትንተና በመንግስቱ ለማ ፀረ ኮሎኒያሊስት ተውኔት” በሚል ርዕስ የተከናወነ ነው በጥናቱ ከተጠኝ ተውኔቱ የተቀነጨቡ ሃሳቦችን በማቅረብ የንድፈ ሃሳባዊ ዳራውን ገቢራዊነት ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በጥናቱ ተውኔቱን በምን መሥፈርት እንደተመረጡ፣ በምን ዘዴ እንደተነተኑ፣ የመረጃ ምንጮችንና የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን እንዲሁም የመረጃ አተናተን ስልትና ሂደት ቀርቧል። ጥናቱን ለመተንተን የድህረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፍ ንድፈ ሃሳብ ጥቅም ላይ ውሏል። በጥናቴም በተውኔቱ ውስጥ የድህረ ቅኝ ግዛት ሥነ ጽሑፍ መገለጫ  ጭብጦች በምን መልኩ እንደተከሰቱ አሳይቷል። ይህ ጥናት ከተውኔቱ ውስጥ ተቀንጭበው በሚቀርቡ ማሳያዎች ላይ በመመስረት ከአውሮፓ ማዕካላዊነት (eurocentirism)፣ከምዕራብ-ምሥራቅ ፍረጃ (orientalism)፣ ከባይተዋርነት (unhomeliness)፣ ከራስን አለመሆን (Mimicry)፣ ከገዥ-ተገዥ ድልድል (Hegemony) እና ቋንቋ፦ድምፅ አልባው ጠመንጃ ከሚሉት ጭብጦች አንፃር ትንታኔ በመስጠት የድህረ ቅኝ ግዛት የሥነ ጽሑፍ ንድፈ ሃሳብ መገለጫዎችን አሳይቷል። በአጠቃላይ ፀረ ኰሎኒያሊስት የተሰኘው ተውኔት የድህረ ቅኝ ግዛት የሥነ ጽሑፍ ንድፈ ሃሳብ መገለጫዎችን የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል።


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919