Main Article Content

የጥያቄ-መልስ ትስስር ብልሃት የተማሪዎችን የማንበብ ግለብቃት እምነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ የማሳደግ ሚና


ፀጋዬ ግርማ
ማረው አለሙ
ሰፋ መካ

Abstract

የዚህ ጥናት ዓላማ የጥያቄ-መልስ ትስስር ብልሃት በተማሪዎች የማንበብ ግለብቃት እምነትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ያለውን ሚና መመርመር ነው። ፍትነትመሰል ቅድመትምህርትና ድኅረትምህርት ፈተና ባለቁጥጥር ቡድን (quasi-experimental pretest-posttest control group) የጥናቱ ስልት ነው። ተሳታፊዎቹ በ2015 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ በቁልቋል ሜዳ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትቤት ከሦስት የሰባተኛ ክፍል ምድቦች በተራ የዕጣ ንሞና ዘዴ የተመረጡ 110 የኹለት ክፍል (55 የቁጥጥር፣ 55 የፍትነት ቡድን) ተማሪዎች ናቸው። የፍትነት ቡድኑ በጥያቄ-መልስ ትስስር ብልሃት፣ የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ በመደበኛው ሥርዐተትምህርት መሠረት ለ12 ክፍለጊዜ አንብቦ የመረዳት ትምህርት ተምረዋል። አንብቦ በመረዳት ፈተናና በማንበብ ግለብቃት እምነት መጠይቅ የተገኙ መረጃዎች በመዋቅራዊ ስሌት ሞዴል (Structural equation model) የSPSS AMOS 23 ሶፍትዌር ተተንትነው የጥያቄ-መልስ ትስስር ብልሃት በተማሪዎች የማንበብ ግለብቃት እምነት ላይ (β = .440, t= 3.431, P= .001) እና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ (β = 1.919, t= 2.135, P= .033) ቀጥተኛ ተጽእኖ እንዳለው ያሳዩ ሲሆን፣ የማንበብ ግለብቃት እምነትን በማጎልበት አንብቦ በመረዳት ችሎታ ላይ ደግሞ (B= 1.462, t= 2.682, p= .002) ኢቀጥተኛ ተጽእኖ እንዳለው (P<.05) አመላክተዋል። በዚህም ብልሃቱ በአማርኛ ቋንቋ የማንበብ ግለብቃት እምነትንና አንብቦ የመረዳት ችሎታን እንደሚያሻሽል ተረጋግጧል።


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919