Main Article Content

የሰው ልጅ ኑባሬ ቅኝት በገ/ክርስቶስ ደስታ መንገድ ስጡኝ ሰፊ የግጥም መድብል


በላይነህ ታዬ ገድፈው

Abstract

ይህ ጥናት በገ/ክረስስቶስ ደስታ (1998) “መንገድ ስጡኝ ሰፊ”  በተሰኘው የግጥም ስራ የሰው ልጅ ኑባሬ (Being) በምን መልክ ተገለፀ በሚለው ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡ በዚህ ቅኝት በገ/ክርስቶስ የተለያዩ ግጥሞች መካከል ትስስር በመፍጠር  ለሰው ልጅ ኑባሬ መገለጫ ሆነው የቀረቡ መሰረታዊ ህግጋቶችን (categories) መርምሮ ያወጣል፤ በህግጋቶች ኑባሬ ስለተገለጠበት ሁኔታ ትርጉም ይሰጣል፡፡ ለዚህም ሲባል አንድምታ (hermeneutics) የደራሲው ሀሳብ ምልዓት (content) ሳይዛባ በግጥሞች ውስጥ ባሉ ቃላት፣ በስንኞች እንዲሁም በተለያዩ ግጥሞች መካከል ትስስር በመፍጠር ትርጉም ለመስጠት በማስቻሉ የጥናቱ ስነ-ዘዴ ሆኖ አገልግሏል፡፡ በዚህ ስነ-ዘዴ ከገ/ክርስቶስ 60 አካባቢ ከሚሆኑ ግጥሞች ውስጥ ከጭብጣቸው አንፃር ለጥናቱ ያስፈለጉት ትርጉምና ትንተና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት፣ ለገ/ክርስቶስ ኑባሬ በመሰረታዊነት ግላዊ ሲሆን በቅይይረዊ ጊዜ (temporal time) እና ህላዌ-ስፍራ (existentialle space) መሳክነት (continuum) የሚገነባ የመኖራችን ማሳያ መሆኑን ጥናቱ በግጥሞቹ የጭብጥ ትረጉም አሳይቷል፡፡ 


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919