Main Article Content

ዳግም ንባብ በአልወለድም


አንተነህ አወቀ

Abstract

የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነው አልወለድም የበርካታ ጥናቶችና የሥነጽሑፍ መድረኮች መወያያ ጉዳይ የነበረና ያለ ሲሆን፣ ይህ ጥናት ግን ለየት ባለ መልኩ በልቦለዱ ላይ ትንታኔ ለማድረግ የሞከረ ነው፡፡ ትንታኔው የተደረገው ሀዲስ ታሪካዊ ሂስን እንደማዕቀፍ በመጠቀም ከመጽሐፍ ቅዱስ፣ ከታሪክ ሰነድና ከደራሲው የህይወት ታሪክ ጋር በማዛመድ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የደራሲው፣ የድርሰቱና ድርሰቱ የታተመበት ዘመን ማህበራዊ ፖለቲካዊ አውዶችን ግምት ውስጥ ያስገባ ነው፡፡ በትንተናውም መሰረት አቤ ጉበኛ የሀገሪቱን ሁኔታ በልቦለዱ ሲገልጽ የመጽሐፍ ቅዱስን፣ የአክአብና ሎዊ ታሪክን፣ ምሳሌ እንደአደረገ፣ የልቦለዱ መቼት፣ ኢይዝራኤሎስ፣ የአክአብና ኤልዛቤል ግዛት ከሆነው ኢይዝራኤል/እስራኤል እንደተወሰደ፣ የአክአብ መንግስት በኢዩ እንደተወረሰ ሁሉ በልቦለዱም የነሙሴ ገራቢዶስ ፊዩዳላዊ መንግሥት በወታደራዊው መንግሥት በማርሻል ጃፌሮስ እንደተገለበጠ፣እነዚህ ደግሞ በጥቅሉ የኃይለሥላሴን መንግሥት አስተዳደር እንዳሳዩ እና የወታደራዊውን መፈንቅለ መንግሥት እንደተነበዩ 3፤ አቀንቃኙ ገጸ ባህሪ አንዳንድ የክርስቶስን ባህሪያት እንደተጋራ መረዳት ተችሏል፡፡ ደራሲውም ከአቀንቃኙ ገጸ ባህሪ መምህርነቱን፣ የለውጥ አርአያነቱን፣ መስዋዕትነቱን፣ከክርስቶስም የእውነት መምህርነቱንና መስዋዕትነቱን ተጋርቶታል ብሎ ማሰብ ይቻላል፡፡ ደራሲው በዚህ መልክ ለመጻፍ የቻለው አንድም የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ በማወቁ ሲሆን በስልት ረገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ምሳሌ መጻፉ ደግሞ የኃይማኖት ትምህርት እወቀቱን በመጠቀሙ ነው፡፡ ከዚህም ደራሲና ድርሰት በዘመኑ ባህል፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሥርዓት እንደሚቀረጹ ሁሉ በተቃራኒው ደራሲውም ሆነ ድርሰቱ ዘመኑን በመቅረጽ ረገድ የሚጫወቱት ሚና መኖሩን መገንዘብ እንችላለን፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919