Main Article Content

የመጽሐፈ እስክንድር የትውልድ ሐረግ ምንነትና አንድምታ


ጥበቡ አንተነህ

Abstract

የዚኽ ጥናት መነሻ ሐሳብ የታላቁ እስክንድር (Alexander the Great) ታሪክ በተለያዩ የብራና ቅጅዎች (Manuscript copies) ተመዝግቦ መገኘቱና በዚኽም ምክንያት የይዘት ልዩነት መኖሩ፣ ከብራና ቅጅዎች ብዛት የተነሳም የትኛው የብራና ቅጅ ከየትኛው የብራና ቅጅ እንደተቀዳ መለየት አለመቻሉ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ዋና ዓላማውም የመጽሐፈ እስክንድርን የብራና ቅጅዎች (Manuscript copies) በመሰብሰብ በ ‘ስቴማቲክ ስልት’ (Stemmatic method) የጥናት ዘዴ የመጽሐፉን የትውልድ ሐረግ (Stemma Codicum) ማሳየት ነው፡፡ በጥናቱም አራት የመጽሐፈ እስክንድር የብራና ቅጅዎች (copies) የተካተቱ ሲኾን ሀ፣ ለ፣ ሐ እና መ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል፡፡ አራቱም ቅጅዎች ከአንድ የዘር ሐረግ ለመቀዳታቸው የወል የገጸ ንባብ ስህተቶቻቸው (Archetype errors) ይጠቁማሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሦስቱ ቅጅዎች (ሀ፣ ለ እና ሐ) ከቅጅ “መ” በተለየ መንገድ ከአንድ የዘር ሐረግ ለመቀዳታቸው አመልካች ዐቢይ የገጸ ንባብ ስህቶቶቻቸው (Conjunctive errors) ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል ቅጅ “ሀ” እና “ለ” ደግሞ ከ “ሐ” በተለየ መልኩ ከሌላ የዘር ሐረግ እንደተገኙ ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ ስለኾነም የመጀመሪያው መጽሐፈ እስክንድር (Vorlage) ልጅ (መ)፣ የልጅ ልጅ (ሐ)፣ የልጅ ልጅ ልጆች (ሀ እና ለ) እንዳሉት ጥናቱ ያመለክታል፡፡ ስለዚኽ ቅጅዎች ባሏቸው የእጅ ጽሑፎች ላይ ትንተና ከማድረግ በፊት ቅጅዎቹን ማነጻጸር (Collate) የቴክስቱን የተሟላ መልእክት ለመረዳት ወሳኝ ሚና እንዳለው መረዳት ይቻላል፡፡  የቤተሰብ ዛፍ (Family tree or geneological tree) የሚል አቻ ስያሜ አለው፡፡ በዚህ ጥናት ግን የዘር ሐረግ በሚል ስያሜ ተተክቷል፡፡ ይህም የእጅ ጽሑፎችን የቅጅ ቅጅ ሂደት (Manuscript transmission process) ያመላክታል፡፡  


Journal Identifiers


eISSN: 2518-2919