Main Article Content
Estimation of Genetic Parameters for Crossbred Dairy Cattle in the Central Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
የዚህ ጥናት ዓላማ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ምርታማና አካባቢን የሚላመዱ ዲቃላ የወተት ከብቶች ዝርያዎችን በቀጣይነት ለማፍራት በተሻለ የማሻሻያ ስልት ለመደገፍ የዝርያዎች ንጽጽር እና የዘረ-ውርስ ሂደት ጥናት ለማካሄድ ነበር፡፡ ጥናቱ የቦረና እና 11 አይነት የዲቃላ የወተት ከብቶች ዝርያዎችን (የፍሬዥያን ከቦረና እና የጀርሲ ከቦረና ድቅሎች) የ38 ዓመት የወተት ምርት፣ የስነተዋልዶ እና አከባቢን የመላመድ ብቃት መረጃዎቸን በመጠቀም ተከናውኗል፡፡ ውጤቱ እንደሚያሳየው የተለያዩ የዲቃላ ዝርያዎች ከቦረና ላሞች ጋር ሲነጻጸሩ ከ 3 አስከ 7 እጥፍ የወተት ምርት ይሰጣሉ፡፡ የዲቃላ ላሞች ቀጣይ ትውልዶች የደም መጠን በ50 በመቶ ላይ ከመጠበቅ ይልቅ ወደ 75 በመቶ የውጭ ደም መጠን ማሳደጉ የወተት ምርትን በ34 በመቶ ያሳድጋል፡፡ ነገር ግን የስነተዋልዶ ብቃታቸው በጥቂቱ ስለሚቀንስ የከብቶች መረጣ ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል፡፡ የፍሬዥያን እና የጀርሲ ዝርያዎችን ለማዳቀል መጠቀማችን የዲቃላ ከብቶች የመጀመሪያ ትውልድ የወተት ምርትና የስነተዋልዶ ብቃታቸውን በከፍተኛ ደረጃ ቢያሻሽልም (additive and heterosis) በቀጣይ ትውልድ ላይ ግን በ recombination loss ምክንያት ምርታማነታቸው በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል፡፡ የወተት ምርት፣ የሚታለቡበት የቀን ብዛት (lactation length)፣ የመጀመሪያ ጥጃ የመውለጃ ዕድሜ፣ በወሊድ መካከል የቆይታ ጊዜ እና በእርባታ የሚቆዩበት ጊዜ (herd life) የዘረ-ውርስ (የመተላለፍ አቅም፤ heritability) መጠን በቅደም ተከተል 0.30±0.00፣ 0.18±0.02፣ 0.19±0.06፣ 0.09±0.03 እና 0.28±0.06 ናቸው፡፡ የዝርያ ባህሪያት ተዛምዶ (genetic correlation of traits) በተመለከተ በወተት ምርት እና በሚታለቡበት የቀን ብዛት (0.84±0.04)፣ በሚታለቡበት የቀን ብዛት እና በወሊድ መካከል የቆይታ ጊዜ (0.86±0.10) እንዲሁም በሚታለቡበት የቀን ብዛት እና በእርባታ የሚቆዩበት ጊዜ (0.94±0.07) መካከል ከፍተኛ ተዛምዶ ታይቷል:: በአጠቃላይ ውጤቱ በዲቃላ ከብቶች መካከል የታየው የምርት ልዩነት፣ ዘረ-ውርስ መጠን፣ የዝርያ ባህሪያት ተዛምዶ እና በትውልዶች መካከል ያለው የምርት መዋዠቅ የዲቃላ ከብቶችን በመረጣ ለማሻሻል እንደሚቻል የሚያመለክትና ለዚሁም ተስማሚ የማሻሻያ ስልት (breeding program) መንደፍ እንደሚያስፍልግ አመልክቷል፡፡
Abstract
The aim of this study was to estimate the additive, heterosis, recombination loss, heritabilities, and correlations between milk yield (MY), lactation length (LL), calving interval (CI), age at first calving (AFC), and herd life (HL) for crossbred of Friesian (F) and Jersey (J) with Boran (B). Analysis of fixed effects and crossbreeding parameters were undertaken using a general linear procedure. Genetic parameters were estimated by multivariate analysis procedure with wombat software. Crossbred cows significantly outperform the B cows by 3 to 7 folds of MY per lactation. Even though the performance of CI and AFC are slightly compromised, upgrading from 1/2F:1/2B (F1) to 3/4F:1/4B (F1) had a better advantage as average MY improved by about 34% following this approach. The additive effects of F and J breed were 3985.2±150 and 1195.6±257 kg for MY, 166.3±16 and 18.5±27 days for LL, 52.9±25 and -40.3±44 days for CI, -0.23±2 and -9.8±4 months for AFC, and 548.7±431 and -569.9±784 days for HL, respectively. The estimated heterosis effects were 1054.8±145 and -150. 6±76 kg for MY, 62.4±15 and -7.3±8 days for LL, -58.1±24 and -88.7±13 days for CI, -1.9±3 and -4.7±1 months for AFC and -215.0±446 and -890.1±226 days for HL for J and F with B breed crosses, respectively. The loss due to recombination of F and B was significant (p < 0.005) and undesirable for MY, LL, AFC which reflect the need for an appropriate breeding program. The heritability (h2) estimates were 0.30±0.00 for MY, 0.18±0.02 for LL, 0.09±0.03 for CI, 0.19±0.06 for AFC and 0.28±0.06 for HL. Strong genetic correlations were obtained between MY and LL (0.84±0.04), LL and CI (0.86±0.10), and LL and HL (0.94±0.07). The estimated genetic variance, heritabilities, and correlations between traits and decline in the performance of inter-se generations reveal the available potential of improvement through selection and the need of designing appropriate breeding programs.