Main Article Content

Black Soldier Fly (Hermetiaillucens) Larvae as a Sustainable Source of Protein in Poultry Feeding: A Review


Chala Edea
Etalem Tesfaye
Tekalegn Yirgu
 Misba Alewi

Abstract

አህፅሮት


በታዳጊ አገር የሚገኙ ዶሮ አርቢዎች በአሁን ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የዶሮ መኖ ዋጋ እና ዝቅተኛ ጥራት ያለው መኖ ችግር እያጋጠማቸው ይገኛል፡፡ በራሪ-ነፍሳት ዕምቅ የዶሮ መኖ የአካል-ገንቢ ምንጭ ናቸው፡፡ በራሪ-ነፍሳትን ለዶሮ መኖነት መጠቀም ከሰው ምግብ ጋር ምንም ዓይነት ቀጥተኛ የሆነ ሽሚያ የለውም፡፡ በመሆኑም የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በራሪ ነፍሳት በሆነው ጥቁር-ዝንብ ዕጭ ዙሪያ በዓለም ደረጃ ለዶሮ የአካል-ገንቢ መኖነት የተሰሩ ስራዎችን በማጣቀስ እና በአንድ በማድረግ በሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ በአማራጭነት ወደትግበራ እንዲገባ ለማመላከት ነው፡፡ የጥቁር-ዝንብ ዕጭ ጉዳት አልባ በራሪ-ነፍሳት ሲሆን ተጓዳኝ ጠቀሜታውም በዋናነት ለዶሮ እና ዓሳ ርባታ እንደ ዋና አማራጭ የአካል-ገንቢ መኖ ምንጭነት፤ የተፈጥሮ ቆሻሻን በማምከንና ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፡፡ አብዛኛው የጥናት ውጤቶች አንደሚጠቁሙት የጥቁር-ዝንብ ድቁስ ዕጭ ጤናማና አዋጭ የሆነ ከፍተኛ የአካል-ገንቢ ይዘት ያለው የዶሮ መኖ ለማቀናበር የጎላ አስተዋጽዖ ያደርጋል፡፡ የዚህ በራሪ-ነፍሳት ዕጭ ከፍተኛ የሆነ ካልሲየም፤ ፎስፈረስ እንዲሁም ከ35-42 በመቶ የሚደርስ የአካል-ገንቢ ይዘት ያለው ሲሆን የመዋሃድ ባህሪውም ከፍተኛ እና ከአኩሪ አተር ዘይት ጭማቂ ጋር ተነጻጻሪ ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የጥቁር-ዝንብ ድቁስ ዕጭ ይዘት በዶሮ መኖ ውስጥ ወሳኝ የሆኑት አሚኖ-አሲድ ይዘት ያላቸውን እንደ ላይሲን እና ሜታዬኒን መጠን ከተፈጨ ስጋና ዓሳ ጋር ተነጻጻሪ ነው፡፡ የብዙ ተመራማሪዎች ውጤት እንደሚያመለክተው የጥቁር-ዝንብ ድቁስ ዕጭ በዕንቁላል ጣይና ስጋ ዶሮ አመጋገብ ሂደት ውስጥ ምንም ዓይነት የጎንዬሽ ጉዳት የሌለውና የሚያስገኘው ውጤትም የአኩሪ አተር ዘይት ጭማቂ እና የተፈጨ ዓሳ ተረፈ- ምርት ከተመገቡት ጋር ተነጻጻሪ ነው፡፡ በተጨማሪም ምርምር ውጤቶች እንደሚጠቁሙት የጥቁር-ዝንብ ድቁስ ዕጭ ለዕንቁላል ጣይ ዶሮ መመገብ የዕንቁላል ምርትና ጥራት እንደሚጨምር ይጠቁማል፡፡ እንደማጠቃለያ ለማጣቀሻነት የተወሰዱት የምርምር ጽሑፎች እንደሚጠቁሙት የጥቁር-ዝንብ ድቁስ ዕጭ ሙሉ-ለሙሉ ወይም በከፊል የአካል ገንቢ ምንጭነት የሚውሉትን እንደ አኩሪ አተር ዘይት ጭማቂና የተፈጨ የዓሳ ተረፈ-ምርትን በመተካት ጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል ያመላክታል፡፡ ሰለሆነም ይህን የጥቁር-ዝንብ ድቁስ ዕጭ በዶሮ መኖ ማቀነባበር ሂደት ውስጥ መጠቀም አዋጭና አከባቢያዊ ጠቀሜታ አለው፡፡


 


Abstract


 Currently, poultry producers in developing countries are facing problems of high cost and poor quality of poultry feed. Insects are one of the potential protein sources for poultry feed. The use of insects as poultry feed is not in direct competition with human for food consumption. The objective of this paper is to review the current work related to the use of Black Soldier Fly (BSF) larvae meal as an alternative protein source in poultry feeding. Black soldier fly is a harmless insect serving as an alternative protein source in animal feeding and in the disposal of organic wastes, by-products, and side streams. The results of numerous studies showed that BSF larvae meal could safely and economically be used as protein concentrate in poultry ration.  BSF larva contains high calcium and phosphorus and contains about 35-42% crude protein with biological value and comparable amino acid profile to that of soybean meal (SBM). The lysine and methionine contents of BSF larva are comparable to that of meat meal. Recent evidence suggests that the nutritional value of BSF larva is comparable to that of fish meal.   Many authors suggested that BSF larvae meal could replace a fish meal or upgrade the nutritive value of SBM in broiler diets without any adverse effect on the production performance. The use of BSF larvae in layers diet resulted in enhanced laying performance and egg qualities.  Generally, all the available literature confirms the feasibility of total or partial replacement of fish meal and SBM with BSF larvae meal. No negative effects were reported from growing chicks fed on BSF larvae meal. Most of the publications reviewed indicated that the growth of chicks fed with BSF larvae meal was either equivalent or superior to SBM in nutritive value as measured by the production performance of growing and laying birds.   Therefore, the inclusion of BSF larvae meal into the poultry feeding system has both economic and environmental benefits.


 


 


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie