Main Article Content
Responses of Holstein and Boran X Holstein Crossbred Cows to Super-ovulatory Hormones used for In vivo Embryo Production
Abstract
አህፅሮት
የቦስ ኢንዲከስ እና ቦስ ታውረስ የተባሉት የከብቶች ዝርያ ወይም ዲቃሎቻቸው በአንድ ጊዜ በዛ ያለ ዕንቁላሎችን እንዲያኮርቱ ለማድረግ ለሚሰጣቸው የሆርሞን ህክምና የተለያየ ምላሽ መስጠታቸው መሰረታዊ የሥነ-ተዋልዶ ባህሪይ ልዩነት እንዳላቸው ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ በመሆኑም በፅንስ የማምረት ሂደት ውስጥ ተጨማሪ ዕንቁላሎችን እንዲያኮርቱ ለማድረግ ተመሳሳይ የአሰራር ሥልት መጠቀም የማይቻል መሆኑን ያሳያል፡፡ ስለዚህ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ለቦስ ታወረስ የተመረጠ የአሰራር ሥልትን የሆሊስቲን ዲቃላ ለሆኑት የቦረና ላሞች ላይ በቀጥታ ከመጠቀም ይልቅ ምላሻቸውን በመመርኮዝ የአሰራር ሥልት መረጣ ለማድረግ የተደረገ ጥናት ነው፡፡ ይህንን ጥናት ለማድረግ ከ3 - 8 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን 36 የቦረናና ሆሊሲቲን ዲቃላ ላሞችና ንፁህ ሆሊስቲን ላሞች ለሙከራው ተጠቅመናል፡፡ በሙከራው ጅምር ላይ ለ7 ቀናት የሚቆይ በብልታቸው ውስጥ ፕሮጄስትሮን ሆርሞን የተነከረ ሲ.ዳ.ር. የተቀመጥ ሲሆን ላሞቹን በሦስት ቡድን ተከፍለው 500፣ 650 እና 800 አይ.ዩ. ፕሉሴት (የኤፍ.ኤስ.ኤች. እና ኤል ኤች ሆርሞን ድብልቅ) ከ4ኛ ቀን እስከ 7ኛ ቀን በ12 ሰዓታት ልዩነት ጧትና ማታ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በ7ኛ ቀን ከብልታቸው ውስጥ የተቀመጠው ሲ.ዳ.ር. ሲወጣላቸው ኢስትሩሜት ሆርሞን በመውጋት ለ72 ሰዓታት የኮርማ ፍላጎት እንደሚያሳዩ ለማረጋገጥ ክትትል ተደርጓል፡፡ በመቀጠልም ተጨማሪ ዕንቁላል ማኮረታቸውን ለማረጋገጥ አድገው ነግር ግን ያልተለቀቁ ዕንቁላሎችና የተለቀቁ ዕንቁላሎች ብዛት በአልትራሳዎንድ መሳሪያ ተቆጥሯል፡፡ ያልተፀነሱ ዕንቁላሎችና የተፈጠሩ ፅንሶች ተሰብስበው ተቆጥረው ተመዝግቧል፡፡ ተጨማሪ ዕንቁላል እንዲያኮርቱ ሆርሞን ከተወጉ ፅንስ ሰጪ ላሞች ውስጥ ከንፁህ ሆሊስቲን (8.67± 3.06) ይልቅ የቦረና እና የሆሊስቲን ዲቃሎች (15.45 ± 0.5) በቁጥር ከፍ ያለ ዕንቁላል መልቀቃቸውን የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳላቸው ታይቷል፡፡ የተሰበሰቡት ፅንሶች ወይም ያልተፀነሱ ዕንቁላሎችን ቁጥር ሲታይም የቦርና ዲቃሎች ከንፁህ ሆሊስቲን የበለጠ በዛ ያለ ቁጥር የሰጡ መሆኑ ታይቷል፡፡ በጣም የጎላ ልዩነት ባይኖርም ከሦስቱ የፕሉሴት ዶዝ መጠን ውስጥ የ650 አይ.ዩ. የወሰዱት እንስሳት የተሻለ የፅንስ ቁጥር እና የተለቀቁ ዕንቁላሎች ብዛት አስገኝቷል፡፡ ከአምስቱ የአካል ሁኔታ ምዘና መስፈርት (ከ2.5 እስከ 5 መካከል ያሉት ተወስደው) በ3.5 እና 3.8 ነጥብ መካከል ያሉት ላሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዕንቁላሎችን (15.74 ± 0.59፤ 14.33 ± 2.90 በቅደም ተከተል) የሰጡ ሲሆን በ3.8 ነጥብ ላይ ያሉት በቁጥር የተሻለ ዕንቁላል/ፅንስ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ በመነሳት የቦረና እና የሆሊስቲን ዲቃላ ላሞች ተጨማሪ ዕንቁላል እንዲያኮርቱ ለተሰጣቸው የሆርሞን ህክምና ለአነስተኛ ዶዝ የተሻለ ምላሽ የሚሰጡ መሆኑንና ባለ 650 አይ.ዩ. ዶዝ ሆርሞን በሁሉም መስፈርት በቦረና እና ሆሊስቲን ዲቃላ ላሞች ላይ የተሻለ ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
Abstract
Variability in the response to super-ovulatory treatments in Bos indicus, Bos taurus, and their crosses was reported to be a fundamental biological difference in reproductive function between them and has been a major barrier to the adoption of similar superovulation protocols. Therefore, this study was designed to optimize the super-ovulatory protocol for the Boran x Holstein crossbred cows. A total of 36 Boran x Holstein crossbred and pure Holstein cows 3-8 years of age were utilized for this study. A 7-day CIDR treatment was initiated on Day 0, and cows were treated on Days 4-7 with 500, 650, or 800 IU of Pluset® (combined FSH and LH product) administered at 12-hour intervals in a decreasing dose regimen. Estrumet (Prostaglandin F2α analogue) was given on day 7 before CIDR withdrawal. Each super-ovulated cow was monitored for 72 hours to assess behavioral estrus in response to super-ovulatory treatment. Ovarian response was also assessed by counting the number of corpora lutea and number of un-ovulated follicles via transrectal ultrasound scanning, the number of total collections, and the number of viable embryos. From the super-ovulated donor cows, Boran X Holstein crosses had a higher (P<0.009) number of corpora lutea (15.45 ± 0.5) than pure Holstein (8.67± 3.06). The number of collected embryos/oocytes and the number of viable embryos collected was significantly higher for crossbred cows (p<0.01, p=0.06) than the pure Holstein cows. Although it was not statistically significant, from the three Pluset® (combined FSH and LH product) dose levels the 650 IU dose have produced a higher response in terms of corpora lutea number and number of collected viable embryos. From the five-scale body condition scoring (Recorded 2.5 to 5) cows with 3.5 and 3.8 scales have produced a higher number of corpora lutea (15.74 ± 0.59; 14.33 ± 2.90, respectively), while those with 3.8 scores had the highest total number of collections (6.33 ± 2.60). From the findings, it can be concluded that Boran X Holstein crossbred cows have a better ovarian response to lower doses of exogenous gonadotropins than pure Holstein cows. The 650IU Pluset® dose level is the optimal level for superovulation of crossbreeds.