Main Article Content
Effect of Furrow Method and Mulch on Bulb Yield and Water Productivity of Irrigated Onion under Central Highland Vertisol of Ethiopia
Abstract
ይህ የምርምር ሥራ በመስኖ በሚመረት ሽንኩርት ላይ በጣም ውጤታማ የውኃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ለመምረጥ እና የውኃ ምርታማነትን ለማሻሻል በደብረ ዘይት የግብርና ምርምር ማዕከል የተካሄደ ነው፡፡ ሙከራው የተካሄደው በሶስት የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴዎች እና በሶስት አፈር የመሸፈን ዘዴዎች በተከፋፈለ መደብ ውስጥ ነው፡፡ ከጥናቱ ውጤት እንደተገኘው የተለያዩ የቦይ መስኖ ዘዴዎች በሽንኩርት ምርትና ውኃ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በተጨማሪም፣ የሽንኩርት ዕድገት፣ የምርት እና ምርታማነትን ከማሻሻል አንፃር የተለያዩ የትነት መከላከያ ልባስ ዘዴዎች መካከል የታየው ተፅዕኖ ከፍተኛ እንዳልሆነ ውጤቱ አሳይቷል፡፡ ይሁንና በጣም ከፍተኛ የሆነ የሽንኩርት ምርት (39.5 ቶን በሄክታር) በተለመደው መደበኛ የመስኖ ዘዴ የተመዘገበ ሲሆን ተለዋጭ የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ (34.3 ቶን በሄክታር) ምርት በማስገኘት በሁለተኛነት ተመዝግቧል፡፡ ሆኖም ከፍተኛ የውኃ አጠቃቀም ውጤታማነት (9.7 ኪ.ግ/ኩዩቢክ ሜትር) የተገኘው በተለዋጭው የመስኖ ዘዴ ምክንያት ሲሆን ይህም ከተለመደው የመስኖ ውኃ አሰጣጥ የውኃ ፍጆታ (5.7 ኪግ/ኩዩቢክ ሜትር) ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም የሽንኩርት ምርት እና የውኃ ምርታማነት ከተለምዶ የመስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴ ከ18 እስከ 22 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ተለዋጭ የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴ ደግሞ ከተለመደው እስከ 42 በመቶ የውሃ አጠቃቀምን ምርታማነትን አሳይቷል፡፡ ስለዚህ የመስኖ ውሃ እጥረት ባለባቸው አከባቢዎች ተለዋጭ የቦይ መስኖ ውኃ አሰጣጥ ዘዴ የአፈርን በፕላስቲክ የመሸፈን ዘዴን በማቀናጀት በተለያየ ምክንያት የሚባክነውን የመስኖ ውኃ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ እንደሚቻል የተገኘው ውጤት ያሳያል፡፡
Abstract
The aim of this study was to select the most effective water-saving techniques and improve the water use efficiency of irrigated onions under limited agricultural water availability. The experiment was conducted in split plot design with three types of furrow irrigation methods and mulch types in three replications. The result revealed that different types of furrow method and mulch type are significantly affected (p<0.01) marketable yield of onion. It has been observed that the significantly highest marketable yield (39.5 t/ha) of onion was recorded due to CFI and followed by AFI method (34.3 t/ha). However, the highest WUE (9.7 kg/m3) was obtained due to AFI method when compared with the CFI method of 5.7 kg/m3. Hence, there was 18 to 22% increment of marketable yield and WUE of the onion by applying mulching over the non-mulching condition and also 42% improvement of WUE by using AFI over the conventional furrow method. Therefore, for maximizing the marketable yield of onion under limiting irrigation water resources, irrigation of onion could be done with AFI method with plastic mulch application to minimize evaporation loss and maximize water productivity of onion for similar agro-ecology and soil type.