Main Article Content

A Holistic Bioeconomic Assessment of the Lake Koka Fishery (Ethiopia): Implications for Management and Livelihood


Gashaw Tesfaye

Abstract

አህፅሮት


የቆቃ የዓሣ ሀብት በዙሪያው በሚገኙ የማህበረሰብ አባላት የምግብ እና ስነ-ምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ እንዲሁም በመተዳደሪያ የገቢ ምንጭነት የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህን ጠቀሜታ ከትውልድ ትውልድ ለማስቀጠል ዘለቂነት ያለው የዓሣ ሀብት አጠቃቀም መተግበር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የቆቃ ሀይቅ የዓሣ ሀብት ያለበት ደረጃ በደንብ አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ የዓሣ ሀብት ምርት መጠን ግምገማ ዘዴን ከኢኮኖሚዊ ትንተና ጋር በማጣመር በቆቃ ይቅ የሚገኙጥማጆች ተፈላጊ የሆኑ የዓሣ ዝርያዎች  የአጠቃቀም ሁኔታ ከሥነ-ህይወታዊ  እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር ዘላቂነት አላቸው ወይስ ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ማወቅ ነው። ዘለቂነት ያለው ከፍተኛ የዓሣ ምርት የሚሰጥ መጠን (MSY) ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚሰጥ የምርት መጠን (MEY) እና እነዚህን የምርት መጠኖች ለማምረት የሚያስፈልጉት የማጥመድ ጥረቶች (fMSY & fMEY) ጋር የተዛመዱ የዓሣ ሀብቱን በአግባቡ ለመጠቀምና ለመጠበቅ የሚያስችሉ የማመሳከሪያ ጠቋሚ ነጥቦችን (management reference points) ለመገመት የባዮማስ ተለዋዋጭ ሞዴሎች (ሚዛናዊ እና ሚዛናዊ ያልሆነ) የባዮኢኮኖሚክስ ሞዴል እና የቶምሰን እና ቤል የዓሣ ምርት መተንበያ ሞዴል ተጠቅሚያለሁ የቶምሰን እና ቤል ሞዴልን በመጠቀም የተገኙት የማመሳከሪያ ጠቋሚ ነጥቦች (reference points) ሚዛናዊ ካልሆኑት ሞዴሎች በእጅጉ የተለዩ ባይሆኑም የቀድሞው ሞዴል ከሌሎቹ ሞዴሎች የተሻለ ተለዋዋጭ (flexible) ግምት ሰጥቷል። ከተሞከሩት ሞዴሎች ውስጥ አንዳቸውም  በጥማጆች ተፈላጊ የሆኑ የዓሣ ዝርያዎች ከመጠን በላይ መመረታቸውን አላመላከቱም፡፡ በመሆኑም የቆቃ ይቅ ዓሣ ሀብት አጠቃላይ ሁኔታ ጤናማና የዓሣ ሀብቱ በተገቢው ሁኔታ እየተመረተ መሆኑን ጥናቱ ያመለክታል፡፡  ነገር ግን አሁን ወቅት በአጥማጆች በመያዝ ላይ ያለው ዝቅተኛ የዓሣ መጠን (Lc) ወደ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታና የምርት መጠን (MEY) ወደሚያስገኘው የዓሣ  መጠን ወይም ርዝመት (LMEY) ቢጨምር ከማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች አንፃር የተሻለ እንደሚሆን ጥናቱ ያሳያል፡፡


 


Abstract


The fishery resource in Lake Koka is very important for food and nutrition security, and the livelihoods of many riparian communities. Proper resource utilization is very essential to sustain the benefits of this natural capital for the present and future generations.  So far little is known about the state of the fishery in Lake Koka. Therefore, the study aims at combining stock assessment of fishery target species of Lake Koka with an economic analysis to find out if current exploitation levels are biologically and economically sustainable or need adjustment. Biomass dynamic models (equilibrium and non-equilibrium), bioeconomic model, and the Thompson and Bell model were applied to estimate reference points related to Maximum Sustainable Yield (MSY), Maximum Economic Yield (MEY), and their corresponding efforts (fMSY & fMEY). While the reference points estimated using the length-based Thompson and Bell predictive model were not significantly different from the non-equilibrium model, the former model provided a more flexible estimate than the other models. As none of the models tested suggested overfishing of the target resources, I conclude that the general state of the Lake Koka fishery is healthy, but see scope for improvement in terms of socioeconomic benefits if the current minimum length of capture were increased toward the length of capture at MEY.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605