Main Article Content

Evaluation of Tradecorp AZ Bentley plus Fertilizer for Tomato Crop Yield Improvement under Irrigation in East Shoa Zone of Oromia, Ethiopia


Getinet Adugna
Agere Lupi
Israel Bekele
Dejene Abera

Abstract

አህፅሮት


 


ኢትዮጵያ ዳፕና ዩሪያ የተባሉ ማዳበሪያዎችን ለረጅም ጊዜ ስትጠቀም ብትቆይም በሀገሪቱ ያለው የአፈር ዓይነትና የስነ-ምህዳር ልዩነት መስፋት ሌሎች ማዳበሪያዎችን ማለትም የተለያዩ ማይክሮ ንጥረ-ነገሮችን ጭምር የያዙ ቅይጥ ማዳበሪያዎችን መጠቀም እንዳለባት ግንዛቤ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም የአፈርን ዓይነት፣ የተለያዩ ሰብሎችንና አካባቢን ግምት ውስጥ ያስገባ የተለያዩ አዳዲስ ማዳበሪያዎችን የመገምገምና አማራጭ ማዳበሪያ ለተጠቃሚው የማቅረብ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ምክንያት ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ የተባለ አዲስ ማዳበሪያ ውጤታማነቱንና  አዋጭነቱን ለመለየት በመስኖ ውሃ በመጠቀም በሚመረት የቲማቲም  ሰብል ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል ከ2010-2011 ዓ.ም. ጥናቱ ተከናውኗል፡፡ ለዚህም ጥናት አዲሱን ማዳበሪያ በሦስት የተለያየ መጠን አሁን ለቲማቲም ሰብል ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው የኬሚካል ማዳበሪያ ምክረ-ሃሳብ ጋር አቀናጅቶ ማሳ ላይ በመጨመር ተከናውኗል፡፡ የጥናቱ ውጤት አንደሚያሳየው ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ ማዳበሪያን መጨመር የቲማቲም ምርት ላይ ጥሩ የሚባል መሻሻል አሳይቷል፡፡ በተጨማሪም ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ ማዳበሪያን ጥቅም ላይ እየዋለ ካለው ምክረ-ሃሳብ ጋር አቀናጅቶ ማሳ ላይ መጨመር የቲማቲም ምርትን እንደጨመረና የገብያ አዋጭነቱም ተረጋግጧል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ጥናት ማጠቃለል የሚቻለው ትሬድኮርፕ ኤዜድ ቤንትሊ ፕላስ ማዳበሪያን ጥናቱ ከተካሄደባቸው አካባቢዎች እንደ ደጓሚ ማዳበሪያ መጠቀም እንደሚቻል ነው፡፡


 


Abstract


Ethiopia was using urea and DAP fertilizers as sources of nitrogen and phosphorous nutrients for a long time. However, the crop and agro-ecology diversity in the country demand more multi-nutrient blends including micronutrients than nitrogen and phosphorus. This increasing demand requires evaluation of different fertilizer resources based on soil type, crop species, and location to provide new alternative fertilizer products to the Ethiopian production system.  Cognizant of this fact, an experiment was conducted to evaluate the efficacy of Tradecorp AZ Bentley plus as a supplementary fertilizer to improve yield of tomato under irrigation in different areas in East Shoa Zone of Oromia, during 2018-2019. The experiment consisted of five treatments ( Control, recommended fertilizer, recommended fertilizer + 1.8 kg product, recommended fertilizer + 3.0 kg product and recommended fertilizer + 4.2 kg product) laid out in randomized complete block design (RCBD) with four replications. The results revealed that application of Tradecorp AZ Bentley plus fertilizer product improved tomato marketable and total yields at testing sites.  In addition, the application of Tradecorp AZ Bentley plus as supplementary fertilizer in combination with the recommended fertilizer rate attained acceptable net returns of tomato at both locations. Hence, Tradecorp AZ Bentley plus is recommended as supplemental fertilizer for tomato producing farmers in testing areas.


 


Keywords: East Shoa, Tomato yield, Tradecorp AZ Bentley plus


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie