Main Article Content

Determinants of Milk Marketing Channel Selection by Urban and Peri-Urban Commercial Dairy Producers in Ethiopia


Tadele Mamo
Jema Haji
Adam Bekele
Tilaye Teklewold
Stefan Berg
Henrietta L. Moore
Catherine Hodge

Abstract

አህፅሮት


 ይህ ጥናት ገበያ ተኮር የወተት ላሞች ርባታ ላይ የተሰማሩ የወተት አምራቾች የጥሬ ወተት ግብይት መንገዶችን ለማጥናት እና የአምራቾችን የመሸጫ (የግብይት) አማራጮች (ቻናል) አመራረጥን የሚወስኑ ጉዳዮችን ለመለየት የተካሄደ ነዉ፡፡ ጥናቱን ለመተግበር በዋና ዋና ከተሞች እና በከተሞች ዙሪያ በተለያየ የሥራ የወተት ላሞች ርባታ ላይ ከተሰማሩ 475 አካላት ጥሬ መረጃ ተሰብስቧል፡፡ ትንተናዉም የተለያዩ ገላጭ ዘዴዎችንና በዛ ያሉ አማራጮችን መሠረት ያደረጉ ሞዴሎች (መልቲ ቫሪዬት ፕሮቢት ሞዴል) በመጠቀም ተከናውኗል፡፡ የጥናቱ ዉጤት እንደሚያሳየዉ ምንም እንኳን በወተት ርባታዉ ላይ የተሰማሩት አካላት የተለያዩ የወተት መሸጫ አማራጮች ቢኖሯቸዉም የወተት ሽያጩ በዋናነት የሚካሄደዉ በኢ-መደበኛ የግብይት አማራጭ ነዉ፡፡ የመልቲ ቫሪዬት ፕሮቢት ትንተና ዉጤቱ እንደሚያሳየዉ የወተት አምራቾቹ የትምህርት ደረጃ እና በላሞች ርባታ ላይ ያካበቱት የሥራ ልምድ፣ የሥራዉ ስፋት፣ የወተት መሸጫ ቦታ ርቀት፣ በወተት ላሞች ርባታ የኅብረት ሥራ ማኅበር አባልነት፣ በእያንዳንዱ የወተት መሸጫ አማራጭ የሚቀርበዉ የወተት ዋጋ እና የወተት ላሞች ርባታዉ የሚከናወንባቸዉ ቦታዎች የወተት አምራቹ የሚሸጥበትን ቻናል የሚወስኑ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ ስለዚህ አሁን ያለዉን ኢ-መደበኛ የወተት ግብይት ወደ መደበኛዉ ለመቀየር የሚቀየስ የግብይት ሥልት ግብይቱን ማዘመን ላይ የተኮረ መሆን እንዳለበት ጥናቱ አመልክቷል፡፡ ይህን ስልት ተግባራዊ ለማድረግ ከሚረዱ ተግባራት መካከል መደበኛና ኢ-መደበኛ ስልጠናዎችን ለወተት አምራቾች በመስጠት መደበ ግብይቱን እንዲቀላቀሉ ማድረግ፣ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን በማጠናከር እና በሁሉም ትላልቅ ከተሞች ላይ እንዲመሠረቱ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ለወተት አምራቾቹ ጥሩ የገበያ አማራጭ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የወተት አምራች የኅብረት ሥራ ማህበራትን አቅም በመገንባት ከወተት አምራቾቹ ወተት የመሰብሰብ ሚናቸዉን እንዲወጡ ማድረግ፣ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በከተማ ዳር እንደሚያደርጉት ሁሉ በትላልቅ ከተሞች ዉስጥም የወተት መሰብሰቢያ ጣቢያዎችን በማቋቋም በኢ-መደበኛ መንገድ የሚሸጠዉን ጥሬ ወተት ወደ መደበኛ ግብይት የመቀየሩን ሂደት ከማሳለጣቸዉም በላይ የማቀነባበሪያ ፋብሪካቸዉን ሙሉ አቅም በመጠቀም የወተት ዘርፉን ትርፋማነት መጨመር ይቻላል፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605