Main Article Content

Registration of Tagasaste (Chamaecytisus palmensis) Variety "Lattuu" for the Highland Areas of Ethiopia


Gezahagn Kebede
Muluneh Minta
Fekede Feyissa
Getnet Assefa
Diriba Geleti
Kedir Mohammed
Aschalew Tsegahun
Solomon Mengistu
Yibrah Yacob
Mezgeb Workiye

Abstract

አህፅሮት


ከዚህ በፊት የተለቀቀውን ዝርያ (MoA) ጨምሮ አስራ አምስት የታጋሳስቴ ዝርያዎች ያላቸው የመኖ ምርት፣ የመኖ ጥራት፣ በሽታን የመቋቋምና ሌሎች ከምርታማነት ጋር የተያያዙ ባህሪያትን ለመገምገም የምርምር ስራው በሆለታና በጀልዱ የምርምር ጣቢያዎች ላይ ለአራት ዓመታት (2008-2011 እኤአ) ተካሄዶ ነበር፡፡ ከእነዚህ ዝርያዎች ውስጥ ሶስት የተሻሉ ዝርያዎች ( CI-15052፣ CI-17497፣ እና CI-15039) ተመርጠው በሆለታ፣ በቁሉምሣና በጀልዱ የምርምር ጣቢያዎች ላይ እኤአ በ 2017 የማረጋገጫ ጥናት ተካሂዷል፡፡ ለቱ (CI-15052) ተብሎ የተለቀቀው አዲሱ የታጋሳስቴ ዝርያ ከፍተኛ የሆነ የሚበላ የመኖ ምርት (7.46 ቶን በሄክታር) ሲሰጥ CI-15039 የተባለው የታጋሳስቴ ዝርያ ደግሞ ዝቅተኛ (3.60 ቶን በሄክታር) የሚበላ የመኖ ምርት ሰጥቷል፡፡ ከዚህ በፊት የተለቀቀው የታጋሳስቴ ዝርያ (MoA) ከሌሎች እጩ ዝርያዎች ጋር ሲወዳደር በተቃራኒው ከፍተኛ የሆነ የማይበላ የመኖ ምርት (6.40 ቶን በሄክታር) ነበረው፡፡ ታጋሳስቴ የሚበላና (ቅጠልና የሚበላ ቅርንጫፍ) የማይበላ (ግንድ) የተክል ክፍል ያለው ሲሆን ለቱ ተብሎ የተለቀቀው ዝርያ በትክክለኛው ጊዜ ከታጨደ 61 ፐርሰንቱ የሚበላ ሲሆን 39 ፐርሰንቱ ግን የግንድ ክፍል ስለሆነ የማይበላ ነው፡፡ የተለቀቀው ለቱ ዝርያ 7.46 ቶን በሄክታር የሚበላ የመኖ ምርት፣ 1.64 ቶን በሄክታር የክሩድ ፕሮቲን ምርትና 3.99 ቶን በሄክታር የሚፈጭ የመኖ ምርት ሰጥቷል፡፡ ለቱ ዝርያ ከዚህ በፊት ከተለቀቀው ዝርያ ጋር ሲወዳደር 24.63 ፐርሰንት የክሩድ ፕሮቲን ምርትና 10.33 ፐርሰንት የሚፈጭ የመኖ ምርት ጭማሪ ነበረው፡፡ በአጠቃላይ የተለቀቀው ለቱ ዝርያ የተሻለ የሚበላ የተክል ክፍል፣ ክሩድ ፕሮቲን እና በእንስሳት ሆድ ውስጥ በተሻለ ሁኔታ የመፈጨት ባህሪያት ነበሩት፡፡ ስለዚህ በብሔራዊ የዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ ዝርያዎቹ ያላቸው የምርታማነት ሁኔታ  እኤአ በ2017 በመስክ ላይ ከተገመገመ በኋላ እኤአ በሚያዝያ 2018 ለቱ የተባለው ዝርያ ለደጋማ አከባቢዎች እንዲለቀቅ የተወሰነ ሲሆን ዘሩን በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ይገኛል፡፡   


 


Abstract


 


Fifteen tagasaste varieties including the standard check variety (MoA) were evaluated for forage dry matter yield, nutritional profiles, disease and insect pest reaction, and other agro-morphological characteristics at Holetta and Jeldu research sites during the main cropping seasons of 2008-2011. Based on the overall performance, three best performing varieties (CI-15052, CI-17497, and CI-15039) were selected and verified with the standard check at Holetta, and Kulumsa Agricultural Research Centers and Jeldu sub-site in 2017 cropping season. The overall mean result indicated that the released variety Lattuu (CI-15052) produced the highest edible yield (7.46 t/ha) while variety CI-15039 produced the lowest (3.60 t/ha) edible yield when compared with other varieties. On the other hand, the standard check variety (MoA) produced the highest (6.40 t/ha) inedible yield. The tagasaste varieties comprise edible (leaf and edible branch) and inedible (stem) plant parts; however, the share of the edible part (61%) of the released Lattuu variety was much higher than its inedible (39%) part of the plant. The total edible dry matter, crude protein, and digestible yields of the Lattuu variety were 7.46, 1.64, and 3.99 t/ha, respectively. Moreover, the released Lattuu variety had 24.63 and 10.33% CP yield and digestible yield advantages over the standard check variety, respectively. Generally, the released Lattuu variety had relatively better leaf to stem ratio, CP, and IVOMD advantages over the standard check variety. Therefore, the national variety releasing committee evaluated the varieties at field conditions in October 2017 and variety Lattuu (CI-15052) was officially released in April 2018 for the highland areas and similar agro-ecologies of the country. The pre-basic and basic seeds of the released Lattuu variety are maintained by the feeds and nutrition research section of Holetta Agricultural Research Center.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605