Main Article Content
Evaluation of Banana (Musa spp.) Cultivars for Growth, Yield, and Fruit Quality
Abstract
አህፅሮት
ይህ ጥናት የተካሄደው ዘጠኝ (አራት ከውጪ የገቡ እና አምስት ከሀገር ውስጥ የተሰበሰቡ) የሙዝ ዝርያዎችና አንድ በመመረት ላይ የሚገኝ የማወዳደሪያ ዝርያ በአራት የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሁለት የምርት ዓመታት ያላቸውን የዕድገት፣ ምርት እና ጥራት ሁኔታ ለመገምገም ነበር፡፡ በእያንዳንዱ የሙከራ ቦታ እያንዳንዱ ዝርያ ሶስት ጊዜ በተለያየ ረድፍ ተተክሎ አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው ተገምግመዋል፡፡ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በተክል ቁመት፣ ተተክሎ ማበብ እስከሚጀምር እና ተተክሎ ምርት እስከሚደርስ በሚወስደው ጊዜ፣ በአምባዛ (ዘለላ) ክብደት፣ በፍሬ ውፍረት፣ በፍሬ ርዝመት፣ በፍሬ ክብደት፣ በምርት መጠን፣ በልጣጭ ውፍረት፣ የሚበላው ክፍል ከልጣጩ ጋር ባለው ጥምርታ፣ በሚሟሙ ጠጣሮች መጠን፣ በአሲድ መጠን፣ በፒኤች፣ በፍሬ እርጥበት እና በፍሬ የአመድ ይዘት መጠን በዝርያዎች መካከል ከፍተኛ ልዩነት ተመዝግቧል፡ እንደአጠቃላይ ዝርያዎቹ አጭርና ወፍራም ተክል (ግንድ) ነበራቸው፡፡ ዝርያዎቹ ተተክለው እስኪያብቡ ከ243.8 እስከ 316.8 ቀናት እንዲሁም ተተክለው ምርታቸው እስኪሰበሰብ ከ374.4 እስከ 446.7 ቀናት ወስዶባቸዋል፡፡ የሁሉም የሙከራ አካባቢዎች አማካይ የምርት መጠን ከ43.67 እስከ 52.46 ቶን በሄክታር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አምስት ዝርያዎች ከማወዳደሪያው ዝርያ አኳያ ተወዳዳሪ (ተመሳሳይ) የሆነ ምርት አስመዝግበዋል፡፡ በስሜት ህዋሳት አማካኝነት በተካሄደ የትንተና መረጃ መሰረት ሁሉም ዝርያዎች በቀማሾች ዘንድ ተመራጭ ሆነዋል፡፡ ከማወዳደሪያ ዝርያው አኳያ እጩ ዝርያዎች ከፍተኛ የሚሟሙ ጠጣሮች መጠን፣ ፎስፎረስ እና ፖታሲየም እንዲሁም አነስተኛ የአሲድ መጠን አስመዝግበዋል፡፡ የፍሬ እርጥበትና የአመድ ይዘት መጠን እንደቅደምተከተላቸው ከ71.53 እስከ 76.56 በመቶ እና ከ2.5 እስከ 3.36 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የዕድገት፣ የምርትና የጥራት መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ‘ሌዲ ፊንገር’ እና ‘ድንኬ-1’ የተባሉት ዝርያዎች በዋና ዋና የሙዝ አምራች አካባቢዎች ወደምርት እንዲገቡ ምክር ተሰጥቷል፡፡
Abstract
A study was conducted to evaluate four introduced and five local banana cultivars with a check variety for growth, yield and quality performances at four locations for two crop cycles. The experiment was laid out in a randomized complete block design with three replications. The results revealed significant varietal differences in plant height, days to shooting, time from planting to harvest, bunch weight, finger diameter, length and weight, yield, peel thickness, pulp-to-peel ratio, soluble solids, titratable acidity, pH, moisture and ash contents. The cultivars had generally short and thick plants. Cultivars took from 243.8 to 316.8 days to flowering while from 374.4 to 446.7 days to first harvest. The yield ranged from 43.67 to 52.46 t ha-1. Five cultivars had comparable yields to the check. The sensory results indicated that all the cultivars were generally preferred. The candidate cultivars recorded higher soluble solids, phosphorus and potassium, but lower titratable acidity than the check. The moisture and ash contents ranged from 71.53 to 76.56% and 2.50 to 3.36%, respectively. Considering the growth and yield performances as well as fruit physicochemical and sensory characteristics, ‘Lady Finger’ and ‘Dinke-1’ are recommended for production in the major banana growing areas of Ethiopia.