Main Article Content
Participatory Evaluation and Demonstration of Onion Spacing in Irrigated Agriculture at Kencho Kebele in Uba Debre Tsehay Woreda, Southern Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
ይህ ምርምር ጥናት ሥራ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በተሳትፏዊ ተከላ ርቀት ለተሻላ ሽንኩርት ምርት በአነስተኛ መስኖ በሚል በአርባምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል የተሰራ ነዉ፡፡ ሙከራዉ የተካሄደዉ በአራት ተከላ ርቀት ማለትም በ8 ሳ.ሜ፣ በ10 ሳ.ሜ፣ በ12 ሳ.ሜ እና አርሶ አደሩ በለመደዉ ወይም እራሱ በሚተክለዉ ነዉ፡፡ የሌሎች ግብአቶች አሰጣጥ ማለትም ማደበሪያ፣ ዩሪያ፣ ዉሃ፣ ኬሚካልና አረም ቁጥጥር ሥራ ለሁሉም ተከላ ርቀት ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡ ከአራቱም ሽንኩርት ተከላ ርቀቶች የተሻለ ምርት ዉጤት የተገኘዉ በ10 ሳ.ሜ (17.178 ቶን በሄክታር) እና 12 ሳ.ሜ (17.740 ቶን በሄክታር) ነዉ፡፡ በዚህ ጥናት አርሶ አደር በእራሱ ልምድ በአማካይ ተከላ ርቀት 7.3 ሳ.ሜ የተገኘዉ ምርት ዝቅተኛ ዉጤት (11.464 ቶን በሄክታር) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እንደ ኮምፕዩተር ፕሮግራም ትንተና ከአርሶ አደር ተከላ ርቀት ዉጭ፤ በሌሎቹ ተከላ ርቀቶች ምንም ዓይነት ልዩነት አልታየም፡፡ ምንም እንኳን የተገኘዉ ምርት ዉጤት በአማካይ አነስተኛ ቢሆንም፤ በወቅታዊ ገበያ አንፃር በአንድ ኪሎ ግራም 34 ብርና በሄክታር 532,831ብር በመሸጥ አርሶ አደሩ ከሌሎቹ ጊዜያት የተሻለ ገቢ ያገኘበት ጥናት ነዉ፡፡ ይህ ዋጋ ጭማሬ የታየዉ፣ በወቅቱ ከተመረተዉ አነስተኛ ምርት መጠን መሆኑ ታዉቋል፡፡ ከዚህ ጥናት መነሻ፤ ተሳትፏዊ አነስተኛ መስኖ ሥራ ላልተጠበቀዉ አየር ንብረት ለዉጥም ሆነ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለዉ ታይቷል፡፡ ስለዚህ በተሳትፏዊ አነስተኛ መስኖ ሥራ ሽንኩርት በጥሩ ሁኔታ በተዘጋጀ ማሳ በ10 ሳ.ሜ ተከላ ርቀት ቢተከል፤ ምረትና ምርታማነትን ሳይቀንስ አርሶ አደሩን ይበልጥ ዉጠታማ ያደርገዋል፡፡
Abstract
This study was conducted for two consecutive years to find optimum onion spacing under full irrigation, which allows the maximum yield of onion at Kencho kebele of Uba debretsehay woreda Gofa Zone Southern, Ethiopia through the support of the Participatory Small-scale Irrigation Development Program(PASID II). The experiment has four levels of onion planting spacing (8cm, 10cm, 12cm, and Farmer's practice or planting with own practice), laid down in Randomized Completed Block Design (RCBD) with four Replications. The same amount of irrigation water (416.56mm) which is 100%ETc was applied for all treatments in the five-day intervals during the study. There was no significant difference among treatment spacing 8cm,10cm, and 12cm on the total yield of onion (16.304 t/ha,17.178 t/ha, and 17.740 t/ha), respectively. The only statistical difference was observed between the three treatments and farmer practice which is 7.3cm (11.464t/ha) on average spacing. Accordingly, farmers’ (FREG) were very profitable from the study in both years. Of course, the yield obtained from the study was very low as compared to the potential yield of Red Creole variety in Ethiopia. As a result, farmers were earned a seasonal income of 34ETB/kg which was very costly, and 532,831ETB/ha on average from seasonal production. This implies that low production potential, but makes high profitable for the farmers during the season. So the PASIDP has vital economic values on the livelihood of farmers and even good training for neighborhood farmers. Therefore it was recommended that application appropriate onion spacing of 10cm with a properly managed field irrigation system makes it highly profitable with marketable yield under full irrigation (100%ETc).