Main Article Content

Productivity and Land Use Efficiency of Wheat-Lentil Inter-cropping under Two Tillage Practices


Almaz Meseret
Bizuwork Tafes
Abuhay Takele
Sisay Eshetu

Abstract

አህፅሮት


 ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ህዝብ ለመመገብ በአንድ የእርሻ ማሳ ላይ ምርታማነትን ማሳደግ በጣም አስፈለጊ ነው፡፡ ስለሆነም ሰብልን አሰባጥሮ መዝራት ምርትን ለማሳደግ ተስፋ ሰጪ ሥርዓት ተደርጎ ይወሰዳል በተጨማሪም ምርታማነትን እና የመሬት አጠቃቀምን ውጤታማ ያደርጋል፡፡ የስንዴ እና ምስር የተለያዩ የሰብል ስብጥር በስንዴ እና በምስር ምርታማነት እና የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት በሁለት የእርሻ አስተራረስ ዘዴ  ለመገምገም በምንጃር ወረዳ  እ.ኤ.አ. ከ 2015-2017 ባለው የሰብል ምርት ወቅት የመስክ ጥናት ተካሂዷል፡፡ ምርምሩ የተካሄደዉ እስፕሊት ፕሎት በተባለ ዲዘይን ሲሆን እያንዳንዱ ትሪትመንት ሶስት ጊዜ ተደጋግሟል፡፡ ትሪትመንቶቹ ያካተቱት ሁለት የአስተራረስ ዘዴ (ባህላዊ እና ዝቅተኛ) በዋና ፕሎት ላይ ሲዉሉ አምስት የስንዴ እና ምስር ስብጥር አዘራር ዘዴ(1፡0፤1፡1፤2፡1፤1፡2 እና 0፡1) ደግሞ በንዑስ ፕሎት ላይ በማድረግ ነዉ፡፡ የሙከራዉ ዉጤት እንዳሳየዉ በስንዴ እና ምስር የእድገት መለኪያዎች ላይ ጉልህ ተፅኖ አልነበረዉም፡፡ የአስተራረስ ዘዴዎችም በስንዴ ምርታማነት ላይ የጎላ ተፅኖ አልነበረዉም ነገር ግን በምስር ምርታማነት ላይ የጎላ ተፅኖ ነበረዉ፡፡ ከፍተኛ የምስር ምርት (1546 ኪ.ግ/ሄ.ክ) የተገኘዉ ከዝቅተኛ የአስተራረስ ዘዴ ሲነፃፀር የባሕላዊ አስተራረስ ዘዴ የተሸለ ምርት አስገኝቷል፡፡ በስብጥር አዘራር ዘዴ በሁለቱም ሰብሎች ላይ የጎላ ተፅኖ ነበረዉ፡፡ ከፍተኛ የስንዴ ምርት (2932 እና 2982 ኪ.ግ/ሄ.ር) የተገኘዉ ስንዴ ብቻውን ሲዘራ (1፡0) እና 2፡1 ስንዴ እና ምስር ስብጥር ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ አሰባጥሮ መዝራት የምስር ምርት እንደሚቀንሰው ጥናቶ ያሳያል፡፡ ከስብጥር አዘራር ዘዴ መካከል 2፡1 ስንዴ-ምስር ስብጥር ከፍተኛ የመሬት አጠቃቀም፤የመሬትና የጊዜ አጠቃቀም እንዲሁም የገንዘብ ጥቅም አስገኝቷል፡፡ ስለሆነም 2፡1 ስንዴ-ምስር ስብጥር ለስንዴ እና ምስር በስብጥር የማምረት ዘዴ ምቹ መሆኑን ጥናቱ አረጋግጧል፡፡


 


Abstract


To feed the ever-increasing population, increase productivity per unit area is one of the most attractive strategies. Intercropping is considered a promising system for increasing crop productivity and land-use efficiency. A field study was conducted to evaluate the effect of different crop combinations of wheat-lentil on the productivity of wheat (Triticum aestivum L.) and lentil (Lens culinaris) and land-use efficiency under two tillage practices in Minjar district during 2015-2017 cropping seasons. The experiment was carried out using split-plot design with three replications. The treatments consisted of two tillage practices (conventional and minimum tillage) assigned as the main plot and five wheat-lentil intercropping combinations (1:0, 1:1, 2:1, 1:2 and 0:1) assigned as the subplot. The tillage practices and intercropping had a significant effect on the growth parameters of wheat and lentil. Minimum tillage increased growth parameters for wheat, but reduced growth parameters for lentil. The yield of wheat was non-significantly affected by tillage practices, but the yield of lentils was significantly affected by tillage systems. A higher yield of lentil (1546 kgha-1) was obtained in conventional tillage as compared to minimum tillage practices. Intercropping combination had a significant effect on both the growth and yield parameters of both crops. The highest yield of wheat (2932 and 2982 kgha-1) was recorded in sole wheat (1:0) and 2:1 wheat-lentil combination, while the highest yield of lentil (1575 kgha-1) was obtained in sole lentil (0:1). Among intercropping combinations, 2:1 wheat-lentil gave the highest LER, ATER, and MAI values. Therefore, 2:1 wheat-lentil intercropping combinations were found suitable for higher productivity and production of component crops, and the intercropping system of wheat-lentil in any of the combinations found to be more profitable and productive compared to sole wheat and lentil.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie