Main Article Content

Evaluation of Different Agricultural Lime Sources for their Agronomic Effectiveness, Yield of Food Barley and Faba Bean and Acid Soil Properties in the Central Highlands of Ethiopia


Fekadu Mosissa
Geremew Taye
Mihiretu Bedasa
Kebede Dinkecha
Tolosa Debele
Temesgen Desalegn
Matiyas Dejene

Abstract

አህፅሮት


አሲዳማ አፈርን በኖራ ማከም የአፈርን ጤናማነትና ለምነት ቀጣይ ለማድረግ  ምርጥ የአፈር አያያዝ ዘዴ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይሁን እንጂ የኖራ ፍቱን ውጤታማነት የሚለካው በምንጩ/የተገኘበት ቦታ፣ ስርቱ/ኬሚካላዊ ይዘቱ፣ የንፁህነትና የድቀት ደረጃውን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማ በአገርቷ የተለያዩ ቦታዎች  የሚመረቱ ለእርሻ ግብዓት የሚዉሉ ኖራዎችን ብቃት ለመገምገም ነው፡፡ የኖራዎቹም የብቃት ማረጋገጫ የተሠራው በሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል የአፈር ላቦራቶሪ ነው፡፡ ከብቃት ማረጋገጫ ሥራው በኋላ በማዕከሉ የሙከራ ማሣና በሮብ-ገበያ የአርሶአደር ማሣ ላይ የኖራዎቹ ውጤት በአፈሩ ባህርይና በሰብል ምርት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ተገምግሟል፡፡ ትርቲመንቶቹ አራት የኖራ ዓይነቶችና አንድ ኮንትሮል (ምንም ዓይነት ኖራ የሌለው) ሲሆኑ በራንደማይዝድ ኮምፕልት ብሎክ ዲዛይን በሦስት ድግግሞሽ ተሞክሯል፡፡ የጥናቱ ውጤት የሚያሳየው አራቱም ኖራዎች ለእርሻ ግብዓት የሚዉሉ መሆናቸው ነው፡፡ የጥናቱ ውጤት በተጨማሪ የሚያሳየው ስታቲስትካል ልዩነት ባለው መልኩ በኖራዎቹ መካከል በአፈር ባህርይና በሰብል ምርት ላይ ከፍተኛ ውጤት ባይገኝም፣ ከኮንትሮል (ምንም ዓይነት ኖራ ከሌለው) ጋር ስነፃፀር ከፍተኛ ውጤት ተገኝቷል፡፡ይህ ግኝት የሚያሣየው በአገርቷ የሚመረቱ የእርሻ ኖራዎች የአገርቷን አስዳማ አፈር ለማከም ምቹ እንደሆኑና ምርታማነትን እንደሚጨምሩ ታውቋል፡፡ ስለዚህ በምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ እና መካከለኛ የአገርቷ ክፍል የሚኖሩ የገንዘብ ውስንነት ያለባቸውና ከሩቅ ሥፍራ ኖራዎችን ለማጓጓዝ የማይችሉ አርሶአደሮች ከቅርባቸው ያለውን በመጠቀም አስዳማ አፈራቸውን ማከም እንደሚችሉ ነው፡፡


 


Abstract


 The potentials of lime to restore soil health and fertility of the acidic soils is one of the best options of sustainable soil fertility management practices. However, the liming effects depend on its source, composition, purity, and fineness. The study initiated to evaluate the effectiveness of different lime materials produced in Ethiopia. Lime samples collected from different producing factories and were characterized at Holeta Agricultural Research Centre. Following characterization on station and on-farm experiments were conducted to evaluate crop and soil response for the different lime sources. The treatments comprised of four different lime materials and control laid out in randomized complete block design with three replications. The result showed that all lime sources fulfill the standards of agricultural lime. The result also showed that there were significant differences between and among lime sources on soil properties as well as crop yield but highly significant between the control treatments. This implies that the lime materials can be suitably used nationally to ameliorate soil acidity and increase crop productivity. Thus, the resource-poor farmers dwelling in western, northwestern, and central highlands who cannot afford to transport the lime sources from far distances can make use of the lime sources near to areas as there is no significant difference.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie