Main Article Content

Why Has a Single Rice Cultivar Dominated the Lowland Rice Production Portfolio of Ethiopia for so Long?


Mulugeta Atnaf
Abebaw Dessie
Fisseha Worede
Zelalem Zewdu
Assaye Berie
Taddesse Lakew

Abstract

አህፅሮት

 ሩዝ በኢትዮጵያ የእርሻ ስርዓት ውስጥ ተመራጭ እየሆነ የመጣ ሰብል ነው፡፡ የፎገራ አካባቢ የአገሪቱን 68 ፐርሰንት የሩዝ መሬት ሽፋንና 71 ፐርሰንት ምርት ይሸፍናል፡፡ የዚህ ጥናት አላማዎች ለምን አንድ ኤክስ-ጅግና የተባለ የሩዝ ዝርያ በፎገራ አካባቢ ሳይተካ ለረጅም ጊዜ (ከ30 ዓመታት በላይ)  በምርት ሂደት ሊቆይ እንደ ቻለ እና ከዚህ ሁኔታ የሚገኙት አስተመህሮቶች ለብሔራዊ ሩዝ ምርምር ፕሮገራም የሚጠቅሙበትን ሁኔታ መሻት የሚሉ ናቸው፡፡ ኤክስ-ጅግና ከሰሜን ኮሪያ ወደ ኢትዮጵያ በ1980ዎቹ አጋማሽ የገባና በኮሪያዉያን ሳይንቲሰቶች ለፎገራ አካባቢ ተላማጅነቱ ተረጋግጦ  ወደ ማማረት ሂደት እዲገባ የተደረገ የሩዝ ዝርያ ነው፡፡ በ2009 እና 2010 ዓ.ም የተደረገ የሩዝ ዝርያ ስርፀት ጥናት አንዳመለከተው የፎገራ አካባቢ ሩዝ ልማት 81 ፐርሰንት የተሸፈነው በኤክስ-ጅግና ነው፡፡ ዝርያው ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜ በማምረት ሂደት የቆዬ ቢሆንም ከፍተኛ ምርታማነት፤ ጥሩ የበሽታ መከላከል አቅም፤ በከፍተኛ ደረጃ በተጠቃሚዎች ተወዳጅነት (በተለይም ደግሞ ነጭ የፍሬ ቀለሙ) ባህሪያትን  እያሳዬ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አርሶ አደሮች የኤክስ-ጅግና  ዱቆቱ ወሃ ያነሳል እንጀራውም ቶሎ እይደርቅም ብለው ይገልፁታል፡፡ በአጠቃላይ አርሶ አደሮች ኤክስ-ጅግናን አብዛኛውን ተፈላጊ ባህሪያት የያዘ ዝርያ  ነው ይላሉ፡፡ የሩዝ ብሔራዊ ምርምር ፕሮገራም ከስድስት የሚበልጡ ለፎገራ አካባቢ ተስማሚና ምርታማ የተሻሻሉ የሩዝ ዝርያዎችን ለቋል፡፡ ይሁን እንጅ ከዝርያ የስርፀት ጥናት እነደምንረዳው አንዳቸውም ዝርያ ኤክስ-ጅግናን ሙሉ በሙሉ መተካት አልቻሉም፡፡ ብሔራዊ የምርምር ፕሮግራሙ ይህ ለምን እንደ ሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል፡፡ ፕሮግራሙ ከተከተለው መንገድና የተለቀቁት  ዝርያዎ አነስተኛ ስርፀጽ ከሚያመላክቱት ክፍተቶች አንዱና ዋነኛው የዝርያዎችን ነጠላ ባህሪ ማሻሻልን እንደ ስልት መከተሉ ነው፡፡ ለወደፊቱ ፕሮገራሙ ፍላጎት ተኮር እንዲሁም አብዛኛዉን ተፈላጊ ባህሪያት የሚያሟላ ዝርያ ለማውጣት በሚያስችል መልኩ መቃኘት ይኖርበታል፡፡


 
Abstract

 Rice is becoming an enterprise of choice in the Ethiopian farming system. The Fogera plain accounts for 68% of the area and 71% of the production of rice in the country.  This paper attempts to explain why a single cultivar called ‘X-Jigna’ has dominated the lowland rice production portfolio of the Fogera plain in the country for more than 30 years and pinpoints the lessons that these inform to the national rice breeding program.  X-Jigna was introduced from North Korea and adopted and recommended by Korean scientists in mid-1980s. Rice adoption study (2016-2017) in the Fogera plain showed more than 81% X-Jigna cultivation. Despite its long time deployment into the production, it has been showing good performance in terms of grain yield, biomass yield with good palatability, good disease reaction, phenotypic acceptability, good tillering capacity, and white caryopsis color. Furthermore, the cultivar has a long and well-exerted panicle, uniform stand, good physical quality, acceptability, and wider utilization. In addition, farmers describe its quality in terms of high flour density ‘wuha yanesal’ and softness stay of the enjera. Generally, farmers describe X-Jigna as a variety that fulfills most of their important traits. The national breeding program developed at least six lowland rice improved varieties for the Fogera plain to replace X-Jigna. However, the replacement rate of the old varieties is quite low as evidenced by the high adoption rate and longtime cultivation of X-Jigna. The breeding program needs to stop by and question why this happened and the journey undergone to come here. One of the critical issues that can be learned from the over years of engagement of the breeding program is that it has followed a trait-based improvement approach to deploy new varieties, which led to the low adoption of new varieties. As a way forward, the breeding program has to be demand-driven and product-oriented.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie