Main Article Content

Rapid Generation Advance in Chickpea for Accelerated Breeding Gain in Ethiopia: What Speed Breeding Imply?


Asnake Fikre
Tulu Degefu
Tesfaye Geleta
 Mahendar Thudi
Pooran Gaur
Chris Ojiewo
 Lee Hickey
Rajeev K.  Varshney

Abstract

አህፅሮት


 ሽምብራ በሀገራችን በተለያዩ ስነ-ምህዳራትና የአዘማመር ስርዓት ውስጥ የሚመረት ሰብል ነው፡፡ሰብሉ የመድረሻ ተለያይነት በዓለም ላይ 80 አስከ 180 ቀናት ይደርሳል፡፡ እያደገ ያለውን ህዝብናተለያዩ ፍላጎቶችን ለመመለስ የሰብል ማሻሻያ ስርዓቱ ጊዜን በቆጠበ ሁኔታ መከወን የሚያስችሉ ዘዴዎችን መጠቀሙ አንዱችግሩ መፍቻ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ላይ የሰብሉን ማሻሻያ ለማፍጠን እንዴት በርካታ ትውልዶቸን በአንድ ዓመት ማግኘት እንደሚቻል ቀርቧል፡፡ አስር የሚሆኑ ምርት ላይ ያሉሽምብራ ዝርያዎችን ከሌሎች ዘጠኝ በዘመናዊ ላብራቶሪ ልየታ ድርቅን የሚቋቋም ባህሪ ያላቸውን ቤተሰቦቸ በማዳቀል ሂደት ወደ 46 ግንኙነቶችን መፍጠር የተቻለበትንና ትውልዶችን ማፍጠንንና ማግኘትን በትኩረት ተከናውኗል፡፡ ዓላማውም ድርቅን የሚቋቋሙና ምርታማ ትውልዶችን ፍተሻ ማድረግ ሲሆን ይህንንም ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመከወን አዲስ የነጠላ ዘር ትውልድ ማሻገሪያ ስርዓትን ከቀድሞ ደራሽ እምቡጦች ጋር በማቀናጀት አራት ትውልዶችን በዓመት ማግኘት የተቻለበትን ሁኔታ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ይህ ትውልዶችን የማስኬድ ሁኔታ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በወረርናደብረዘይት ማእከላት የሙከራ ማሳዎችን በመጠቀም የተሰራ ጥናት ሲሆን በውጤቱም ቀድሞ ደራሽ እምቡጦችን ለማግኘት 80-85 ቀናት ብቻ የፈጀ ነበር፡፡ ትውልዶቹ የመካከለኛ መድረሻ ጊዜ ያለው ውስጥ የሚመደቡ ሲሆን በዚህ ስሌት የዝርያ መልቀቂያ ጊዜውን ከተለመደው 10-12 ዓመታት 50 በመቶ በመቀነስ የአማራጭ ቴክኖሎጂ አቅርቦትና ምርታማነት እንዲሁም አዋጭነት ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው ውጤት አመላክቷል፡፡ ይህ ቴክኒክ በቶሎ የመድረሻድሜ ያላቸው ላይ ተፅዕኖው አስከ ስድስት ትውልድ በዓመት ማስገኘት እንደሚያስችል የተሰላ ሲሆን በቀላሉ የሚለመድ፣ በጥቂት የመዋዕለ ነዋይ፣ ፋሲሊቲና ክህሎት በትሮፒካል ንፍቀ-ክበብ ውስጥ አገልግሎት ላይ ሊውል የሚችልና ቴክኖሎጂ ለቀቃን ብሎም መተካካትን የሚያፋጥን፤ በዚህም ረገድ የምርታማነት እመርታን የሚያስገኝ የተሻሻለ ዘዴ እንደሆነ መገንዘብ ተችሏል፡፡


Abstract


Chickpea (Cicer arietinum L.) is grown in a wide range of environments and cropping systems and its maturity ranges from 80 to 180 days. Time-saving breeding is key to responding to the dynamics of demands and environmental changes. The study employed the Single Seed Descent (SSD) technique in advancing the generation, supported by the independent observation of chickpea seed germination and seedling establishment in the seed lab. The filial generation nursery was derived from 46 initial crosses with the aim of enhancing drought and yield response of otherwise commercial 10 cultivars. Between 5 December 2017 and 20 December 2018 we were able to obtain four rounds of working chickpea seeds (F2-F5) using two research locations. The average time required to obtain early matured pods varied from 80 to 85 days. Harvesting four generations in an annual cycle enables a saving of at least 50% time in variety release, which has the potential to double the rate of genetic gain and variety replacement. As long as measures are taken to reduce risk associated with extreme weather events or animal damage, this low-cost rapid cycling approach could be adapted for large-scale breeding programs to fast track the development of more productive varieties.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605