Main Article Content

Market Integration and Price Transmission of Maize in Ethiopia


Mesay Yami

Abstract

አህፅሮት


 ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ችግር አየሆነ መጥቷል። አንደመፍትሄ መንግስት የተለያዩ የገበያ ዋጋን የማረጋጋት ስራዋችን ቢሰራም ለችግሩ መፍትሄ ሊሆኑ አልቻሉም። በአብዛኛው ሸማቾችና የመንግስት አካላት ለዚህ ዋነኛ ተጠያቂ የሚያደርጉት የነጋዴዎች ዋጋን አለአግባብ መጨመርና ዋጋ ሲቀንስ ደግሞ በፍጥነትና ወይም ሙሉ በሙሉ አለመቀነስ ነው። የዚህ ጥናት አላማ የነጋዴዎችን የገበያ ዋጋ ሲጨምርና ሲቀንስ፣ የሽያጭ ዋጋው አተማመን ምን ይመስላል የሚለውን ለማጥናት ነው። ጥናቱ የተከናዋነው በአስራ አምስት የበቆሎ ገበያዎች የተሰበሰበውን የመግዥና መሸጫ ዋጋ በመጠቀም ነው። የጥናቱ ግኝት እንደሚያመለክተዉ የነጋዴዎች ዋጋ ከማህል አገር (አዲስ አበባ) ሲጨምር አምብዛም የበቆሎ የሽያጭ ዋጋ አይጨምርም። አንዳውም በአንዳንድ የበቆሎ ገበያዎች (ነቀምትና መቀሌ) ነጋዴዎች የመሸጫ ዋጋ ከአዲስ አበባ ሲቀንስ እነዚህ የበቆሎ ገበያዎች ግን በፍጥነት የበቆሎ የመሽጫ ዋጋን ሲቀንሱ ታይተዋል። በአጠቃላይ ጥናቱ አንደሚያሳየው ከሆነ ነጋዴዎችን  ለዋጋ ግሽበቱ መሉ ለሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ትክክል አንዳልሆነ ያሳያል። ነገር ግን መንግስት ዋጋን ለማረጋጋት የሚወስዳቸው ርምጃዎች ወጥና ግልጽ መሆን አለባቸው። በተለይ መንግስት የዋጋን ግሽበት የማረጋጋት ስራ በግልጽ በህግ የታገዘና የገበያ ተዋናዮችን ፍላጎት አካታች አንዲሆን ይህ ጥናት ያስገነዝባል፡፡ 


Abstract


In this study, we investigated the presence of predatory price adjustment practices in the grain market in Ethiopia by relying on data during the post-agricultural market liberalization period from July 2004 to March 2016. We employed an Asymmetric Error Correction (AECM) model to test the presence of Asymmetric Price Transmission (APT) between integrated wholesale regional maize markets. The results demonstrate that out of 14 regional maize market pairs with the central Addis Ababa maize market, APT is confirmed in only two regional wholesale maize markets of Mek’ele and Nekemete. Hence, the widely held belief by consumers and government that traders’ inappropriate price adjustment contributes to the persistence of soaring food prices in Ethiopia is just a misconception. It is argued in this study that the recent surge in maize price in Ethiopia has little to do with APT in maize market.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605