Main Article Content
Screening Mung bean [Vigna radiata (L.) Wilczek] Genotypes for Drought Tolerance
Abstract
አህፅሮት
ድርቅ የማሾ ምርትና ምርታማነትን ከሚቀንሱ ማነቆዎች በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማ ድርቅን ሊቋቋሙ የሚችሉ ብዝሀ-ዘሮችን ለመምረጥ የሚያግዙ ዋና ዋና የድርቅ መቋቋሚያ ጠቋሚዎችን መለየትና ድርቅን የሚቋቋሙ የማሾ ብዝሀ-ዘሮችን መለየት ነው፡፡ በዚህ ጥናት ስልሳ (60) የማሾ ብዝሀ-ዘሮችን ሁለት የመስኖ አማራጮችን በመጠቀም በአልፋ ላቲስ ዲዛይን በሁለት ድግግሞሽ ማከናወን ተችሏል፡፡ የጥናት ዉጤቱ እንደሚያሳየዉ በብዝሀ-ዘሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ የምርት ልዩነት በሁለቱም የመስኖ ዉኃ አጠቃቀም ዘዴዎች ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም የጥናቱ ዉጤት የሚጠቁመዉ የስብሉ ምርታማነት፣ ጂኦሜትሪክ አማካይ ምርታማነት፣የምርት ኢንዴክስ እና የድርቅ መቆጣጠሪያ ኢንዴክስ ድርቅን የሚቋቋሙ ብዝሀ-ዘሮችን ለመምረጥ በዋናነት የሚያስፈልጉ ጠቋሚዎች እንደሆኑ ነዉ፡፡ እነዚህ ኢንዴክሶች ከምርት ጋር ከፍተኛ የሆነ ግንኝነት እንዳላቸዉ በሁለቱም የውሃ አማራጮች የተረጋገጠበመሆኑ የተሻሻሉ ብዝሀ ዘሮችን ለመምረጥ አስፈላጊ እንደሆኑ ለማወቅ ትችሏል፡፡ በተጨማሪም የክሊስተር ትንተና ውጤት እንደሚያሳየዉ በጥናቱ ውስጥ የተካተቱ 60 የማሾ ብዝሀ ዘሮች በአምስት ቦታዎች ሊከፈሉ ችለዋል፡፡
Abstract
Drought is among the major constraints in mung bean production. The main goal of the current study was to investigate the response of 60 mung bean genotypes to two constrasting moisture regimes using diverse indices. The experiment was made at Jinka Agricultural Research Center using a 6 x 10 alpha lattice design replicated twice. Correlation analysis revealed that seed yield under stressed condition was positively correlated with stress tolerance index (STI), yield index (YI), harmonic mean (HM), mean relative performance (MRP), and relative drought index (RDI). PCA of the first two components accounted for 93.4% of the total variations where PC1 contributed for 64.39% of the variations. Based on cluster analysis, 60 mung bean genotypes used in the current study were grouped into five distinct clusters. In conclusion, this study showed that selection based on indices with seed yield under moisture-stress (Ys) and seed yield under non moisture-stress (Yp) conditions are useful for mung bean breeders. Therefore; stress tolerance index (STI), yield index (YI), harmonic mean (HM), geometric mean productivity (GMP) and mean relative performance (MRP) were found to be more suitable indices since these indices had the highest correlation with seed yield under both moisture-stressed and non moisture-stress conditions.