Main Article Content
The Role of Conservation Agriculture for Soil Quality Improvement: A Review
Abstract
አህፅሮት
በኢትዮጵያ በሰብል መሬት ላይ ያለው የአፈር መከላት በዓመት ከ40-130 ቶን በሄክታር የሚደርስ ሲሆን፣ ከ1.0-1.5 ሚሊዮን ቶን እህል ምርትን እያሳጣት ይገኛል፡፡ የዕቀባ እርሻ በሶስት እርስ በእርስ በሚደጋገፉ መሰረታዊ መርሆዎች ላይ ተመስርቶ የአፈር መከላትን በመቀነስ፣ የአፈርን ጥራት በማሻሻል እና ዘላቂነት ላለው የግብርና ምርት አስተዋጽኦ እያደረገ ስለመሆኑ በሰፊው ይታወቃል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ የምርምር እና የሰርቶ ማሳያ ጥረቶች ቢኖሩም የረጅም ጊዜ ጥናቶች ለአፈር ጥራት መጎልበት ያለዉን ጥቅሞች በበቂ ሁኔታ በማሳየት ላይ ውስንነት አለባቸው፡፡ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የረጅም ጊዜ የዕቀባ እርሻ ጥናቶችን መዳሰስ እና ያለውን እውቀት መቀመር የወደፊት የዕቀባ እርሻ አጠቃቀም ላይ ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለመስጠት፤ እንዲሁም የምርምር እና የማስተዋወቅ ስራዎች ለመምራት ይረዳል፡፡ ይህ ጥናት ዓላማው የዕቀባ እርሻ ለአፈር ጥራት መሻሻል እና ተያያዥ ተግዳሮቶች ላይ የተሰሩ ጥናቶችን በመተንተን በኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫን ለማሳየትና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለመጠቆም ነው፡፡ የዕቀባ እርሻ ከ3-5 ዓመታት ውስጥ የአፈር ጥራትን ሊያሻሽል እንደሚችል እና ዘላቂነት ላለው የግብርና ምርት አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት የታዩት ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ በተጨማሪም ዝቅተኛ ርጥበት ባለባቸው አካባቢዎች የሰብል ምርት መሻሻልን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማምጣት እንደሚችል ያሳያሉ፡፡ ሆኖም በኢትዮጵያ ውስጥ የዕቀባ እርሻ የመጠቀም ልምድ በአርሶ አደሩ ዘንድ እምብዛም አልሰፋም፡፡ ለዚህም ዋና ዋና ምክንያቶች የሰብል ተረፈ-ምርቶች ለተለያዩ ጠቀሜታዎች መዋልና የአቅርቦት እጥረት፣ ለዕቀባ እርሻ ተብለው የተመከሩ አሰራሮች እና ግብዓቶች ውስንነት፣ ለዕቀባ እርሻ ምቹና አቅም ያላቸው አካባቢዎችን ቅድሚያ ሰጥቶ አለመሥራት፣ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶች ውስንነት እና ለዕቀባ እርሻ ትግበራ ምቹ ሁኔታዎች የማመቻቸትና የማስቀጠል ውስንነቶች ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ባለሙያዎችን በማሳተፍ፣ አካባቢያዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን ያማከለ የዕቀባ እርሻን በማጎልበት ለተጠቃሚው ማቅረብ እና ለሚኖሩት ተግዳሮቶች ቀድሞ ተገቢዉን አማራጭ መፍትሄዎችን በመተግበር ከዕቀባ እርሻ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ለአርሶ አደሩ ማሳየትና ተጠቃሚ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለተመራማሪዎች፣ ለኤክስቴንሽን ሰራተኞች ለልማት ባለሙያዎች እና ለአርሶ አደሮች እንዲሁም ለወሳኝ ባለድርሻ አካላት የሚታዩትን ውስንነቶች የሚቀርፍ በቂ የአቅም ግንባታ ሥራም ወሳኝነት አለው፡፡
Abstract
Ethiopia experiences a very high soil loss of 40–130 t ha-1year-1 from croplands that costs the country about 1.0-1.5 million tons loss of grain production per year. Founded on its three interlinked principles, Conservation Agriculture (CA) is widely documented to reduce soil loss, improve soil quality and contribute to sustainable agricultural production. Despite more than three decades of research and promotion efforts on CA in Ethiopia, long-term comprehensive studies are scanty to sufficiently demonstrate its benefits for soil quality enhancement. Drawing lessons from long-term CA studies both within and outside the country would help to make informed decisions for wider use of CA and guide future research and promotion activities. Available pertinent CA literatures from peer-reviewed journals, research reports, dissertations, and proceedings were reviewed. This review was aimed to collate and analyse studies documented the effect of CA practices on soil quality improvement and associated challenges, and suggest the way forward for its application by smallholder farmers in Ethiopia. The review indicated that, when properly implemented, CA improves soil quality in 3-5 years and contributes to sustainable agricultural production. Besides, yield improvement is possible in early stages of CA application in the low moisture areas under sufficient crop residue retention. However, CA adoption in Ethiopia is generally low which is mainly attributed to limited availability and competing uses of crop residue, limited availability and use of CA based recommendations, mis-location of CA promotions, limited participatory extension services and enabling conditions. Overall, the review suggested the need for a concerted multi and inter-disciplinary research effort to develop CA innovations suiting to the different biophysical environments and socioeconomic circumstances. Effectively demonstrating the power of CA on relieving soil problems, and providing alternative solutions for the challenges surrounding it are requisites to get its full benefits. Capacity building on innovative CA practices is crucial for researchers, extension workers, development practitioners and the smallholder farmers.