Main Article Content
Exploring Optimized Synergetic Solutions for Major Constraints of Sustainable Agricultural Production in Chencha, Southern Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
የጨንቻ ወረዳ የግብርና ዘይቤ ምርታማነት በተለያዩ ማነቆዎች ተጽዕኖ ስር ያለ መሆኑ አሁን ያለው የግብርና ዘይቤ መሻሻል እንዳለበት ያመለክታል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ቁልፍ የሆኑ የአፈር ለምነት፣ የሰው ጉልበትና የገቢ እጥረት ችግሮችን በአንድ ላይ አዳብሎ ለመፍታት እንዲቻል አማራጭ ለመሻት ይህ ጥናት ተካሂዷል፡፡ በዚህ ጥናት ወረዳውን ሊወክሉ ከሚችሉ አስራ ሁለት አባ/እማወራ ማሳዎች እና ከተለያዩ መዛግብት መረጃዎች ተወስደዋል፡፡ የግብርና ዘይቤውን ለማሻሻልና ለችግሮቹ የመፍትሄ አማራጭ ለማመንጨት፤ ፋርም ዲዛይን (FarmDESIGN) የተባለ የመረጃ ትንተና ዘዴ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህ የትንተና ዘዴ መፍትሄ ለማመንጨት ሁለት ሁኔታዎች ታሳቢ ተደርገዋል፡፡ እነዚህም አሁን ባለው የግብርና ዘይቤ ውስጥ ያሉትን የአመራረት ዘዴዎችን መሠረት በማድረግ የተሻለ አማራጭ ማውጣት እና አዳዲስ ተጨማሪ ቴክኖሎጂዎችን በማስረፅ እና በማሻሻል ለአስራ ሁለቱም ማሳዎች የመፍትሄ አማራጭ ማውጣት ናቸው፡፡ የትንተና ውጤቱ እንደሚያሳየው አሁን ባለው አሠራር በሁሉም ማሳዎች ላይ የአፈር ለምነት መቀነስ፣ የቤተሰብ ጉልበት ማነስ እና የገቢ እጥረት መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ይሁን እንጂ ለእነዚህ ችግሮች በርካታ የተቀናጁ አማራጮች እንዳሉም ውጤቱ ይጠቁማል፡፡ ታሳቢ ከተደረጉ ሁኔታዎች የተሻለ አማራጭ ማግኘት የተቻለው አሁን ያለውን የአመራረት ዘዴ ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር አጣምሮ በመስራት ነው፡፡ የተሻለ ለውጥ ማምጣት ካስቻሉ ምክንያቶች ዋነኛው የሰብል ስርዓትን ወይም የሰብል ቦታ ሽፋን ድልድልን ማስተካከል ሲሆን ይህም ከእያንዳንዱ የሰብል የቀደመ አያያዝ ወይም እንክብካቤ ጋር ተያያዥነት ያለው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰብሎች የሚኖራቸውን የማሳ ሽፋን ስሌት እና ተያያዥ አሠራሮችን በግል ለማስተካከልና ለመተግበር አርሶ አደሩ ሊቸገር ስለሚችል የግብርና ባለሙያ ምክር በእጅጉ ያስፈልገዋል፡፡ ስለዚህ የአርሶ አደሩን ግንዛቤ ማሳደግና ስለሰብል ማሳ ዕቅድና ከሰብል ጋር ተያያዥ የሆኑ የተሻሻሉ የአመራረት ዘዴዎችን፣ የባህር ዛፍን ቦታ አጠቃቀም፣ የሰብል ቅሬት አጠቃቀም እና የፍግ አያያዝና አጠቀቀምን በተሻለ እንዲያውቅ ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ከግብርና ሥራ ውጪ የሆኑ ቦታ የማይሻሙ የገቢ አማራጮችን መተግበር፣ ጉልበት ቆጣቢ የሆኑ ቀላል የመውቂያ መሣሪዎችን ለአርሶ አደሩ ማስተዋወቅ እና ምርታቸውን በተሻለ ዋጋ መሸጥ እንዲችሉ የገብያ አማራጭና ትስስር መፍጠር ወሳኝ ተግባራት ናችው፡፡
Abstract
Several constraints affect the performances of the farming system in Chencha suggesting the necessity of adjustments in the farm components. Therefore, an exploration was made to simultaneously optimize operating profit, labour and soil organic matter balances. Data from twelve farms and secondary data on improved technologies were used as bases for the exploration. Using the multi-objective model FarmDESIGN, the optimization was conducted for two scenarios for each farm, i.e., optimization based on the currently existing farm components and practices and by introducing new technologies and practices to amend the current farm management options. The results revealed that the farm operating profit, labour balance and organic matter balance were not yet optimized with the current farm configurations of all farms. But there is ample scope to improve and simultaneously optimize both the economic, social and environmental sustainability either through optimization of management within current farm resources, or through using improved technologies. The highest improvement could be made through combined optimization of management within current farm resources and improved technologies. The major important factor that influenced the optimization was the cropping plan, which might be associated with the management practices applied for a particular crop. However, adjusting areas of crops and implementation of some other optimized solutions may be difficult for individual farmers and requires advice through agricultural extension programmes. Therefore, there is a need to improve the awareness of farmers to wisely manage: crop area and associated crop and soil management practices, land use for eucalyptus, straw use and storage of farm yard manure. Moreover, it is important to diversify off-farm income sources, introduce alternative threshing machineries and improve market access for farm products.