Main Article Content

Sensory Quality Attributes of Tef [Eragrostis tef (Zucc.) Trotter] Injera as Influenced by Genotype and Environment


Anteneh Abewa
 Enyew Adgo
Getachew Alemayehu
Birru Yitaferu
Ayenew Meresa

Abstract

አህፅሮት


ጤፍ በአብዛኛው ለእንጀራ አገልግሎት ይውላል፡፡ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ሚመረት ነጭ ጤፍ በሌሎች ቦታዎች ከሚመረተው በጥራቱ የተሸለ ነው ተብሎ ስለሚታመን በከፍተኛ ዋጋ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ ይህ የምርምር ስራ ያተኮረው ነጭ ቀለም ያላቸውን ሶስት የተለያዩ የጤፍ ዝርያዎቸን (ዕፀብ፣ ማኛ እና ቁንጮ) በአምስት የተለያዩ የመካከለኛውና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በመዝራት በእንጀራ ጥራት መስፈረቶች መሰረት በማወዳደር ያለቸውን የጥራት ልዩነታቸውን ለማወቅ እና ጥራታቸውን ከዝርያዎቹ የፍሬ እና ዱቄት ቀለም ጥራት እንዲሁም ከተመረቱበት አካባቢ የአፈርን የአየር ፀባይ ጋር ያለቸውን ዝምድና ለማጥናት ነው፡፡ በዚህ ጥናት በእንጀራ መጋገርና መብላት ጥልቅ ዕውቀት ያላቸውን 21 ሰዎችን በማስገምገም የተሰራ ስራ ነው፡፡ እነዘህ 21 የእንጀራ ጥራት ገምጋሚዎች በእንጀራ የላይ ገፅታ ቀለም የጀርባ ገፅታ ቀለም፣ የዓይን አደራደር፣ የመጠቅለል/ልስላሴ ባሀሪ እና አጠቃላይ የእንጀራ ጥረታ ላይ ሲሳተፉ ከእነዚህ ውስጥ 11 ተመርጠው የጥፍጥና ጥናት ላይ ተሳትፈዋል፡፡ የልዩነት ትንተና ስሌቱ እንደሚያሳየው የእንጀራ ጥፍጥና ጤፍ በተመረተበት አካባቢ ብቻ ካሳየው ልዩነት ውጭ ሌሎች የእንጀራ ጥራት መስፈርቶች በሙሉ በዝርያ በተመረቱበት አካባቢ እና ዝርያዎች ከበቀሉበት አካባቢ ባላቸው መስተጋብር ከፍተኛ (P < 0.05 to P < 0.001) ልነቶች እንዳላቸው ያሳያል፡፡ የእንጀራ ጥራት ማለትም የላይ ገፅታ ቀለም፣ የጀርባ ገፅታ ቀለም፣ የዓይን አደራደር፣ የመጠቅለል፣ የጥፍጥና  እና አጠቃላይ የእንጀራ ጥራት ልዩነት የመጣበትን የትንተና ልየታ ውጤት ስናይ ደግሞ፤ በበቀሉበት ቦታ ምክንያት የመጣው ልዩነት የ52.4በመቶ፣ 38.7በመቶ፣ 62.5በመቶ፣ 87.6በመቶ፣ 69.0በመቶ፣ እና 80.8በመቶ እንዲሁም ዝርያዎች ከተመረቱበት ቦታ ጋር ባለቸው መስተጋብር የ40.9በመቶ፣ 53.0በመቶ፣ 26.0በመቶ፣ 12.0በመቶ፣ 28.6በመቶ፣ እና 18.6በመቶ በተከታታይ ለልዩነታቸው ምክንያት ሲሆን በዝርያዎቹ ምክንያት የመጣው የጥራት ልዩነት ደግሞ (6.6በመቶ፣ 8.3በመቶ፣ 11.6በመቶ፣ 0.3በመቶ፣ 2.4በመቶ እና 0.6በመቶ ቅደም ተከተል) ዝቅተኛ ነበር ፡፡ የእንጀራ ጥራት ጤፍ ከሚበቅልበት የአፈር ዓይነት (መረሬ/ዋልካ)፣ ኮምጣጣነት፣ የንጥረ-ነገር ቅይይር ብቃት፣  ካልሽዬም፣ ፖታሽየም፣ ማግኒዥየም መጠን ጋር እንዲሁም ከጤፍ ቀለም ፍካት/ብሩህነት/ (brightnes) እና የተመረተበት ከባህር ጠለል በላይ ካለው ከፍታ መጨመር አወንታዊ/ቀጥተኛ የሆነ ግነኙነት አለው፡፡ የአፈር ውስጥ የናይተሮጅን እና  የሳልፈር መጠን አሉታዊ/ተቃራኒ የሆነ ትርጉማዊ ግንኙነት እንዳላቸው ውጤቱ አሳይቷል፡፡ የዝናብ መጠን መጨመር የእንጀራ ጥራትን የመቀነስና ጤፍ የተመረተበት ቦታ ከባህር ወለል እየጨመረ ሲሄድ የእንጀራ ዓይንና ልስላሴ መጨመር  ተስተውሏል፡፡  በአጠቃላይ የእንጀራ ጥራት ከዝርያ ይልቅ በሚመረቱበት አካባቢ የአፈርና የአየር ፀባይ እንዲሁም ዝርያዎች ጤፉ ከሚመረትበት ከባቢያዊ ሁኔታ ጋር ያላቸው መስተጋብር ይበልጥ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፡፡ ይህ ጥናት ሲደመደም መረሬ/ዋልካ አፈር የሆነና ከኮምጣጣነት ወደ አልካላይንነት የሚያደላ፣ በቤዝ ካታዮን/ብረተ-አስተኔ የበለፀገ ከሆነ የእንጀራ ጥራቱ እንደሚጨምር እና በቀይ አፈር ላይ በአንሰተኛ የአፈር በቤዝ ካታዮን/ብረተ-አስተኔ የተመረተ ጥራቱ እንደሚቀንስ አመላክቷል፡፡ ከአሁን በፊት ሰሜን ምዕራብ አማራ የተመረተ ጤፍ በእንጀራ ጥራቱ ከመካከለኛው የኢትዮጵያ ክፍል ከሚመረተው ያንሳል የሚለው አሰተሳሰብ በመረሬ/አፈር የተመረቱትን የጤፍ ዝርያዎችን አወዳድረን ስናይ ልዩነት አላቸው የሚል ድመዳሜ ላይ አያስደርስም፡፡ የበለጠ ግልፅና አስተማማኝ ውጤት ይኖር ዘንድ የአፈር ንጥረ-ነገር ማዳበሪያዎች ለጤፍ እንጀራ ጥራት ያለላቸውን ተፅዕኖ የሚዳሰስበት ጥናት በተለያዩ ስነ-ምህዳሮችና አፈር ዓይነቶች መሞከር ተገቢ ነው፡፡


 


Abstract


 Tef is used to make injera (bubbly, pancake-like bread). It is believed that the white color tef grain produced in the central highlands of Ethiopia fetches the highest price as compared to the other areas due to its injera quality. Therefore, this experiment was conducted in the central and northwestern highlands of Ethiopia to evaluate Injera Sensory Quality Attributes (ISQA) on the three white-colored tef genotypes (Etsub, Magna, and Quncho) produced on five environments and to assess its relationship with edaphic factor, climatic factor, and grain and flour color of tef. The responses of the 21 knowledgeable consumer panelists' for top surface color, bottom surface color, malleability, eye appearance, and general rating; and 11 of them for taste subjected to Analysis of Variance (ANOVA). The ANOVA result showed that except taste significantly (P < 0.05) different only on the environment, other ISQA were significantly (P < 0.05 to P < 0.001) different on the genotype, environment, and genotype by environment interaction effects. The variance component result revealed that the environment (52.4%, 38.7%, 62.5%, 87.6%, 69.0%, and 80.8%) and genotype (40.9%, 53.0%, 26.0%, 12.0%, 28.6%, and 18.6%) contribution to the variation of BSC, TSC, eye appearance, Malleability, taste, and general rating were high, while  the genotype was low (6.6%, 8.3%, 11.6%, 0.3%, 2.4% and  0.6%).  There were also significant positive correlations of soil properties (black color/vertisols pH, CEC, ca, Mg, and K), grain and flour color V value, and altitude; while soil total nitrogen and sulfur as well as precipitation showed an indirect significant relationship with IQSA. These results concluded that tef grown on vertisols with slightly acidic to neutral soil pH and relatively high in basic cations have a better quality of injera as compared to tef grown in nitisols with low soil pH and basic cations. Based on our results, we argued that the quality of tef injera “as low quality” grown in Vertisols of the northwestern highlands couldn’t be substantiated. A further study under controlled environment is recommended to evaluate the effects of different soil nutrients effect on ISQA under different soil types and agro-ecologies of Ethiopia.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605