Main Article Content

Virulence Spectrum of Phytophthora infestans and Spatial Distribution of Physiological Races in Northwestern Ethiopia


Esmelealem Mihretu
Wassu Mohammod
Bekele Kassa
Hannele Lindqvist-Kreuze

Abstract

አህፅሮት

ድንች ለምግብና ለአመጋግብ ዘዴ ዋስትና በተለይም የምግብ ዋስትና ችግር ባለበት አካባቢ ዋነኛ ምግብ ነው፡፡ ምንም እንኳን ድንች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ቢሆንም ፋይቶፍቶራ ኢንፌስታንስ በሚባል ተዋስያን አማካኝነት የሚከሰተው የድንች ምች በሽታ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ለድንች ማምረት ትልቅ  ማነቆ ነው፡፡ ጥናቱ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ዋና ዋና የድንች አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ላይ የፋይቶፍቶራ ኢንፌስታንስ በሽታ አምጭ የዝርያ ዓይነቶችን እና ስርጭታቸውን ለመለየት 2018 የተካሄደ ነው፡፡ በአጠቃላይ 74  ናሙናዎች ተሰብስበው በድንች ቁርጥራጮች ላይ በማባዛትብላክስ በሽታ ተቋቋሚ የድንች ዘረመሎች ላይ በሽታ አምጭነታቸው ተገምግሟል፡፡ ናሙናዎቹ በሽታውን በሚቋቋሙ ዘረመሎች ላይ ተሞክረው በአሳዩት አፀፋዊ መልስ መሠረት 6 11 እና 16 የተለያዩ ዓይነት በሽታ አምጭ ዝርያዎች በአዊ፣ በደቡብ ጎንደር እና በምዕራብ ጎጃም በቅደም ተከል መሠረት እንደሚገኙ አሳይቷል፡፡ የሻኖን የአይነት ብዛት መለኪያ ውጤት ለሁሉም ናሙናዎች በአጠቃላይ 0.8 ሲሆን ለአዊ፣ ለደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች ለየራሳቸው ደግሞ 0.75 0.84 እና 0.92 በቅደም ተከተላቸው መሠረት ነው፡፡ በአጠቃላይ 74ቱም ናሙናዎች የሦስቱም ዞኖች ፑል ተደርገው ሲታይ 27 የተለያዩ ዓይነት በሽታ አምጭ ዝርያዎች እንዳሉ ተለይተዋል፡፡ ምንም አይነት የዝርያ ውስብስብነት የሌለው ናሙና በደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች የተገኘ ቢሆንም ከፍተኛ የዝርያ ውስብስብነት 10 የበሽታ አምጭነት ነገር ያላው ዝርያ በደቡብ ጎንደር ተገኝቷል፡፡ በሽታውን ከሚቋቋሙ ዘረመሎች ውስጥ R3, R5, R8 እና R9 አጠቃላይ ከታየው ልዩነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሲሆን R9 እና R5 በጣም ውጤታማ የነበሩ 95% እና 92%  የሚሆኑትን ናሙናዎች በቅደም ተከተል መቋቋም የቻሉ ዘረመሎች ናቸው፡፡ በጠቅላላው ዋና ተቋቋሚ ዘረመል የያዙ የድንች ዝርያዎችን በመጠቀም በሽታውን መከላከል አዳጋች ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉንም ናሙናዎች መቋቋም የቻለ ዘረመል ባለመኖሩ እና ውስብስብ በሽታ አምጭ የዝርያ ዓይነቶች በአካባቢው ተሰራጭተው ስለሚገኙ፡፡

 

Abstract

Despite the importance of potato the late blight disease, caused by the oomycete Phytophthora infestans is most destructive disease for potato production. The study was conducted to identify virulent races and spatial distribution of Phytophthora infestans populations in major potato growing areas of northwestern Ethiopia in 2018. Seventy-four isolates (samples) were collected and multiplied on potato tuber slices and virulence was assessed on Black’s potato differentials. Isolates reaction to differentials revealed 6, 11, and 16 race types at Awi, South Gondar and West Gojam, respectively. Shannon diversity index was 0.80 for the entire isolates but it was 0.75, 0.84 and 0.92 for isolates collected from Awi, South Gondar and West Gojam, respectively. Tewnty-seven physiological races were detected in the pooled population when the 74 isolates from the three populations were combined. Absence of race complexity was found in isolates of South Gondar and West Gojam while the highest race complexity with virulence factors of 10 was found in South Gondar. Differentials, R3, R5, R8, and R9 had larger contribution to the total variability of isolates and R9 and R5 genes were most effective withstood 95% and 92% of isolates. It is concluded that potato varieties resistant to major genes are hardly possible to be used as disease management option due to the absence of R genes resistant to all isolates, the complexity, and distribution of races in the region.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605