Main Article Content
Precision Agriculture and the Need to Introduce in Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
የዕቅጩ እርሻ የተለያዩ የረቀቁ የእርሻ መሳሪያዎች፣ የአይሲቲ ቴክኖሎጂዎችንና አሰራሮችን የሚያጠቃልል ሲሆን የሰብል ምርትን ሊቀንሱ የሚችሉ በማሳ ውስጥ ያሉ በተለይም የአፈር ተለያይነትን በመቀነስ ትክክለኛና ሰብሉ የሚፈልገውን የማሳ ዝግጅት፣ ዘር አዘራር፣ የመስኖ ውሀ አሰጣጥ፣ የማዳበሪያና ፀረ አረም በመጠቀም የሰብል ምርትንበማሳደግ ወጭን በመቀነስ ትርፋማነትን ማሳደግና በአካባቢ ላይ ሊደርስ የሚችል ተፅዕኖን በተለይም የአፈር ጨዋማነትንና በፀረ ተባይ የሚደርስ ጉዳትን በእጅጉ መቀነስ ነው፡፡ የዕቅጩ እርሻ በማሳ ውስጥ የሚታይና በዕፅዋት ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሲሆን የአፈር ካርታን ወይም በእርሻ ማሳሪያዎች ላይ የተገጠሙ የዕፅዋት ወይም አፈር የረቀቁ ሴንሰሮችን በመጠቀም ትክክለኛ ግብአትን መጠቀም ያስችላል፡፡ በአገራችን የሚታየው የአነስተኛ አርሶ አደሮች የማሳ ይዞታ የዕቅጩ እርሻን ለመተግበር ተግደሮት ቢሆንም፤ በክለከስተር የተደራጁ፤ ሰፋፊ እርሻዎች እና የስኳር ፕሮጀክቶችን ማሳን ለማስተካካልና ትክክለኛ የግብዓት መጠን በመጠቀም ምርታማነትን፣ ትርፋማትንና የምርት ጥራትን በእጅጉ ሊያሳድግ ይችላል ፡፡ ምንም እንኳ ለዕቅጩ እርሻ የሚውሉ የእርሻና የመገናኛ መሳሪያዎች ዋጋ እና የሚጠይቀው አጠቃቀቀም ዕውቀትና ክህሎት ከፍ ያለ ቢሆንም የሚሰጠው ጥቅም ከወጪው በእጅጉ እንደሚልቅ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡
Abstract
Precision Agriculture (PA) includes several techniques, technologies and management factors aimed at addressing field variation that affect crop yield by using more precise land leveling, seeding, fertilizer application, irrigation and pesticide use in order to optimize crop production, improve profitability and reduce environmental risk. PA recognizes temporal and spatial variability of production fields through information acquisition; interpretation; evaluation; and control. This can be achieved using map or management zones based on soil survey and property data or real time based for variable rate application of inputs while on the go. It has been shown that PA conserves irrigation water and power, improves profitability through correct application of fertilizers and pesticides, and reduces environmental risk. PA can be implemented in large and cluster farms as well as lowlands of Ethiopia particularly in irrigated fields. It can help to precisely level land, correct seeding, and application of the right amount of fertilizer, irrigation water, and pesticide based on the plant need. Despite its superior advantage, the high cost of machineries, software and skilled labor could scare the adoption of PA in Ethiopia. However, studies have shown that the benefits of PA out weights the cost and it can contribute to food security significantly.