Main Article Content

Pests of Belg and Irrigated Tef (Eragrostis tef) in the Amhara Region, Ethiopia


Tebkew Damte
Gebrekidan Feleke
Shigut Adisu
Kebebew Assefa
Habtamu Tesfaye

Abstract

አህፅሮት

በበልግ ዝናብ እና በመስኖ የሚመረት ጤፍን ሰለሚያጠቁ ፀረ-ሰብሎች ማንነት መሠረታዊ መረጃ ለማመንጨት በ 2008 እና በ 2009 ዓም በአምስት ዞኖች ቅኝት ተካሄደ፡፡ የአረም ናሙና የተወሰደው 50 ሳሜ በ 50 ሳሜ በሆኑ አራት ካሬዎች ሲሆን በእያንዳንዱ ካሬ ውስጥ የነበሩ የአረም ተክሎች ብዛት እና የዝርያ ማንነት በመመዝገብ ነበር፡፡ የተባይ እና የበሽታ ናሙና የተወሰደው ደግሞ ሙሉውን ማሳ በዓይን በመመልከት እና የተባዩን እና የበሽታውን ምልክት በመለየት የጉዳቱን መጠን በመገመት ነበር፡፡ የጤፍ ግንጫፍ ዝንብ ፣ የበቆሎ ክሽክሽ እና ማንነቱ ያልተለየ ግንድ ቦርቧሪ ተባይ በበልግ ዝናብ እና በመስኖ የሚለማ ጤፍን ያጠቃሉ፡፡ እነዚህ ተባዮች የጤፍ ተክል ላይ የሚያደርሱት የጉዳት መጠን ዝቅተኛ ሲሆን እስከ 10 በመቶ ሊደርስ ይችላል፡፡ ሁለት የጤፍ በሽታዎች ማለትም የጤፍ ዋግ  እና ገሳሽ በተወሰኑ የጤፍ ማሳዎች ብቻ ተገኝተዋል፡፡ የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች ጤፍን ያጠቃሉ፡፡ በ 14 ቤተሰብ ውስጥ የሚመደቡ ከ 22 የሚበልጡ የአረም ዝርያዎች በሁለቱም ዓመት ተመዝግበዋል፡፡ በ 2008 ዓም እንግጫ፣ የጥጃ ሥጋ፣ ቅንጨ አረም፣ የውሻ ጎመን እና የሞኝ ፍቅር በብዛት የተገኙ የአረም ዝርያዎች ሲሆኑ፤ በ 2009 ዓም ደግሞ የውሻ ስንደዶ፣ ቅንጨ አረም እና ነጭ ለባሽ በብዛት የተገኙ የአረም ዝርያዎች ነበሩ፡፡ ስርጭቱ በምስራቅ፣ ደቡብ  ምዕራብ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች ብቻ የተወሰነው ጋሻ ነቃይ አረም ቁንጮ በተዘራ አንድ ማሳ ውስጥ ብቻ ተመዝግቧል፡፡

 

 

 

Abstract

Field surveys were conducted in 2016 and 2017 belg season to generate baseline information on the type of pests prevailing in Belg and irrigated tef. The survey was conducted in five zones. Weeds were sampled in four 50 cm x 50 cm quadrats and the number of individual weed plants were counted and identified to species level in situ. Insect pests and diseases were determined by visual search for damages done by insects or symptoms of diseases throughout the field. Tef shoot flies (Atherigona spp.), maize aphid (Rhopalosiphum padi) and unidentified stalk borer infested tef. But the severity of damage caused by these insect pests was trace to 10%. Tef rust (Uromyces eragrostidis) and Sclerotium sp. were prevalent in limited tef fields. Tef is also attacked by different bird species. More than 22 weed species in more than 14 families were recorded throughout the surveyed areas. The two families Poaceae and Compositae accounted for the larger proportion of weed species. In the 2016 season Cyperus spp., Portulaca oleracea, Parthenium hysterophorus, Amaranthus hybridus and Xanthium strumarium, in decreasing order, were the most abundant weed species, whereas in the 2017 season  Setaria pumila, Eragrostis cilianensis, P.  hysterophorus and Argemone ochroleuca, in decreasing order, were abundant weed species. Field bindweed, Convolvulus arvensis, which is found only in East, Southwest, and West Shewa Zones, was found in one field sown to Quncho.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie