Main Article Content
The R elationship s between S tem C haracters and L odging T olerance in T ef ( Eragrostis tef ) G enotypes
Abstract
አህፅሮት
ጤፍ በብዙ ሚሊየኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ለምግብነት፣ ለእንስሶች ምግብ፣ ለቤት መስሪያነት እና ለመኝታ
የሚያገለግል ዘርፈ ብዙ የሰብል አይነት ነዉ፡፡ ነገር ግን በ ተለያዩ የምርት ማነቆዎች ምክንያት ከጤፍ የሚገኘው ምርት
ከሌሎች የብርዕ ሰብሎች ከሚገኘው ምርት ጋር ሲነጻጸር ትንሽ ነው ፡፡ የ ሰብል ግሽበት የጤፍን ምርት እና ምርታማነቱን
ለማሳደግ የሚደረገውን የምርምር ስራ እየገቱ ካሉ ማነቆዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የሰብል ቁመት፣ የሰብል ግንድ ውፍረት
እና ስፋት፣ የአንጓ ቁጥር እና ርዝመት የብርዕ ሰብሎችን የግሽበት ባህርይ ከሚወስኑ ባህሪያት መካከል ይገኙበታል፡፡
የሰብል ግንድ ባህሪያት ከግሽበት ጋ ር ያላቸውን ትስስር ማወቅ ግሽበትን የሚ ቋቋ ሙ የጤፍ ዝርያዎችን በምርምር
ለማውጣት የሚደገረውን ስራ በእጅጉ እነደሚያግዝ ይታመናል፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉ የምርምር ስራዎች የሰብል ግንድ
ባህሪያት ከግሽበት ግር ያላቸውን ትስስር ለማወቅ የሚያስችል መሰረትን ቢጥሉም የሰብሉን የ ግንድ ባህሪያት ከማዳረስ
አንጻር ውስን ነበሩ፡፡ በዚህ የምርምር ስራ አንድ መቶ የጤፍ ዝርያዎችን በሶስት የተለያዩ አካባቢዎች በመዝራት ከዚህ
በፊት በተጠኑት የግንድ ባህሪያት ላይ ተጨማሪ የግንድ ባህሪያትን አካቶ በማጠናት ከዚህ በፊት የነበረውን ዕውቀት
ለማስፋት ተሞክሯ ል፡፡ ይህ ጥናት ከዚህ በፊት የጤፍን የግሽበት ባህርይ ሊወስኑ ይችላሉ ከተባሉት የግንድ ባህሪያት
በተጨማሪ የ አጓ እና የፔደንክል ርዝመት ግሽበትን የሚ ቋቋ ሙ የጤፍ ዝርያዎችን ለማውጣት በ ሚደረገው ምርምር ውስጥ
ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አመላክቷ ል፡፡
Abstract
In cereals is stem characters such as plant height, culm thickness and diameter and the
number of internodes and their length are among the factors known to modulate
lodging tolerance, a key trait in the development of high yielding tef varieties.
Knowledge of the relationship between stem characters and lodging has significant
implications with respect to designing sound breeding strategies for tef Eragrostis
tef )), a staple cereal crop for millions of people in Ethiopia. Previous studies were
limited mainly to plant height and the diameter of the two basal culm internodes. With
the aim of expand ing this knowledge by exploring additional stem characters one
hundred tef landraces were studied at three different experimental sites and
affirmative evidence was obtained showing that in addition to plant height the length
of internodes and peduncle are apt to breeding lodging tolerance in tef.