Main Article Content
Yield and Nitrogen Uptake of Wheat as Affected by Nitrogen Fertilizer and Compost in the Central Rift Valley of Ethiopia
Abstract
አህፅሮት
የተፈጥሮንና የኬሚካል ማዳበሪያን አቀናጅቶ መጨመር የአፈርን ንጥረ-ነገር በሰብል የመጠቀም ሁኔታና ምርትን ይጨምራል፡፡ ሆኖም ግን የአፈርን ዓይነት፣ የተሇያዩ ሰብሎችንና አካባቢን ግምት ውስጥ ያስገባ የሁሇቱን ማዳበሪያዎች መስተፃምር የመሇየት ምርምር ሥራ ብዙ አልተካሄደም፡፡ በዚህም ምክንያት የኮምፖስትንና የኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያዎች መስተፃምርና መጠን አንዲሁም አዋጭነቱን ሇመሇየት በስንዴ ሰብል ላይ መስኖ ውሃ በመጠቀም በመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል በ2006 ዓ.ም. ጥናቱ ተከናውኗል፡፡ ሇዚህም ጥናት አራት የተሇያየ የኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያ መጠን (0፣ 23፣ 46 እና 69 ኪ.ግ ሇአንድ ሄክታር) እና አራት የተሇያየ የኮምፖሰት መጠን (0፣ 5.6፣ 11.2 እና 16.8 ቶን ሇአንድ ሄክታር) አቀናጅቶ ማሳ ላይ በመጨመር ተከናውኗል፡፡ የጥናቱ ውጤት አንደሚያሳየው ኮምፖሰትን እና ኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያን ሇየብቻም ሆነ ሁሇቱን ማዳበሪያዎች አቀናጅተን ስንጨምር በስንዴ ምርትና የሰብለን ናይተሮጅን ንጥረ-ነገር አጠቃቀም ላይ ጥሩ የሚባል መሻሻል አሳይቷል፡፡ ነገር ግን ሁሇቱን ማዳበርያዎች ሇየብቻ በመጨመር ከተገኘው ውጤት በተሻሇ ሁኔታ ኮምፖሰትንና ኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያን በቅንጀት የተጨመረው ከፍተኛ የሆነ የስንዴ ምርት አስመዝግቧል፡፡ በተሇየ ሁኔታ 69 ኪ.ግ ኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያን እና 5.6 ቶን ኮምፖሰትን በአንድ ላይ በቅንጀት የተጨመረው ተመጣጣኝና አዋጭ የሆነ የስንዴ ምርት አስገኝቷል፡፡ በተጨማሪም ሁሇቱን ማዳበርያዎች ሇየብቻ ከተጨመረው የልቅ ኮምፖሰትንና ኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያን በቅንጅት የተጨመረው በተሻሇ ሁኔታ የሰብለን የናይተሮጅን ንጥረ-ነገር አጠቃቀም ጨምሯል፡፡ ስሇዚህ ከዚህ ጥናት ማጠቃሇል የሚቻሇው 69 ኪ.ግ ኬሚካል ናይተሮጅን ማዳበሪያን እና 5.6 ቶን ኮምፖሰትን አቀናጅቶ መጠቀም፤ ዘላቂ የሆነ የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ መሆኑን ነው፡፡
Abstract
Integrated applications of organic and inorganic nutrient sources are indispensable for enhanced nutrient use efficiency and crop yields. However, it requires determination of the optimum combination of these resources based on soil type, crop species, and location. Cognizant of this fact, an experiment was conducted to determine the optimum levels and combinations of compost and inorganic N fertilizers for maximum profitable grain yield of wheat at Melkassa under irrigation in 2014. The experiment involved factorial combinations of four rates of N (0, 23, 46 and 69 kg ha-1) and four levels of compost (0, 5.6, 11.2, and 16.8 t ha-1) laid out in RCB design with three replications. The results revealed that both chemical N and compost and their interactions significantly and positively affected the yield of wheat and N uptake. The highest grain yield was obtained from the combined applications of chemical N and compost than that obtained from N and compost applied alone. Accordingly, combinations of 69 kg N ha-1 and 5.6 t ha-1 produced optimum grain yield and realized the maximum net returns of wheat. Significantly, higher N uptake was obtained from the combined application of N and compost than that obtained from either source applied alone. Therefore suggested that combination of 69 kg mineral N ha-1 and 5.6 t ha-1 compost are the best combination to achieve sustainable yield.