Main Article Content

Soil Fertility and Crop Management Research on Cool-season Food Legumes in the Central Highlands of Ethiopia


Getachew Agegnehu

Abstract

 

አህፅሮት

የአፈር ሇምነት መመናመንና አስፈላጊ የሆኑ የዕጽዋት ንጥረ ነገሮች በከፍተኛ ደረጃ መሟጠጥ በሀገሪቱ በስፋት ሰብል በሚመረትባቸዉ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ሇዘላቂ እርሻ ልማት ቁልፍ ችግር መሆኑ የሚታወቅ ነዉ፡፡ ይህ ጽሁፍ እስከአሁን በማዕከላዊ የሀገሪቱ ከፍተኛ ቦታዎች በደጋ ጥራጥሬ ሰብሎች ላይ የተከናወኑ የአፈር ሇምነት፣ የዕፅዋት ሥነ-ምግብና የሰብል አያያዝ ምርምር ዋና ዋና ግኝቶችን በማጠናቀር ያቀርባል፡፡ ተገቢ ያልሆነ የሰብል አያያዝ፣ ኋላቀር የውኃ ማጥፈፍ ዘዴ፣ የአፈር አሲዳማነትና እንደዚሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰብሎች በተሇያየ የዕድገት ደረጃቸው ወቅት አጥጋቢ የሆነ የፎስፎረስ ንጥረ ነገር ማግኘት ያሇመቻል ሇሰብል ዝቅተኛ ምርታማነት ዋና መንስዔዎች መሆናቸው በጥናት ሇማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የደጋ ጥራጥሬ አመራረት ዘዴ በሀገሪቱ ከቦታ ቦታ ይሇያያል፡፡ የምርምር ግኝቶች እንደሚያመሇክቱት ከዘር በፊት ሁሇት ጊዜ መሬትን ማረስና በትክክሇኛው የሰብል ዕድገት ወቅት አንድ ጊዜ ማረም የባቄላና የአተር ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ሇመጨመር ያስችላል፡፡ እንደዚሁም ውኃ የመቋጠር ችሎታቸው ከፍተኛ በሆነ ከባድ ሸክሇማ የአፈር ዓይነቶች ላይ ዘመናዊ ውኃ የማጥፈፊያ ዘዴዎችን፣ ትክክሇኛ የዘር ወቅትና ምርታማ የሆኑ የሰብል ዝርያዎችን በማቀናጀትና በመጠቀም የባቄላና የሽምብራ ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ሇማሳደግ ተችሏል፡፡ የአሲዳማ አፈርን ምርታማነት ሇመጨመር 13 እና 5 ቶን ኖራ በአንድ ሄክታር ማሳ ላይ በመጨመር የባቄላ ምርታማነትን በ45፣ በ77 እና 81 በመቶ በቅደም ተከተል ከፍ ሇማድረግ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ በቀይ አፈር ላይ ከ20 እስከ 30 .. የፎስፈረስ ንጥረ-ነገር መጨመር በባቄላና አተር ከፍተኛ ገቢ ማግኘት እንደሚቻልና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዳሇዉ ሇማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እንደዚሁም የፎስፈረስ ንጥረ-ነገር መጠን በዝቅተኛና መካከሇኛ ሇምነት ደረጃ በሚገኝ አፈር ላይ ሲጨምር የአተር ምርታማነትም በተማሳሳይ ሁኔታ ይጨምራል፡፡ በተጨማሪም ፍግና የፎስፈረስ ንጥረ-ነገርን በቅንጅት መጠቀም የባቄላን ምርታማነት በአመርቂ ሁኔታ ከመጨመሩም በላይ የአፈርን ምርተማነት በዘላቂነት ያሻሽላል፡፡ በመጨረሻም የደጋ ጥራጥሬዎችን ምርተማነት በስፋትና በዘላቂነት ሇማሻሻል ከምርምር ሥራው ጎን ሇጎን የቴክኖሎጂ ማስፋፋት ሥራም ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡

Abstract

Land degradation and depletion of soil fertility is the critical challenge for sustainable crop production in the highlands of Ethiopia. This paper reviews advances in the major activities and achievements of soil fertility, crop and land management research on the highland pulses, which have been done for the last two decades in the central highlands of Ethiopia. Inappropriate agronomic practices, poor internal drainage, soil acidity and associated low phosphorus (P) availability are major constraints affecting productivity of highland food legumes. Production practices differ across the major highland pulse growing areas of the country. Research findings showed that twice tillage before planting and one properly timed hand weeding resulted in optimum yields of faba bean and field pea. Substantial increments in seed and biomass outputs of faba bean and chickpea were recorded on Vertisols due to the integrated application of improved surface drainage, sowing date and genotypes. At Holetta, the application of lime as calcium carbonate at the rate of 1, 3 and 5 t ha-1 on Nitisols increased mean seed yield of faba bean by 45, 77 and 81%, respectively over non-treated plots. Similarly, application of 23/20-32/30 kg N/P ha-1 on Nitisols resulted in the highest net benefit for faba bean and field pea production. Phosphorus by farmyard manure interaction significantly increased faba bean seed yield. Field pea seed yield also increased at the low and medium soil fertility levels with increasing rates of P application. In conclusion, a concerted effort is necessary to extend the available technologies in order to improve the productivity of highland food legumes.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie