Main Article Content
Agro-Morphological Traits Diversity in Tef [Eragrostis Tef (Zucc.) Trotter] Genotypes from Various Sources
Abstract
አህፅሮት
ጤፍ መገኛው በኢትዮጵያ የሆነ ፈርጀ-ብዙ የአመራረት፣ የአመጋገብና የጤና ጠቀሜታ ያለው ሰብል ቢሆንም ምርታማነቱ በተለያዩ ማነቆዎች የተነሳ በሰፊው ከሚመረቱት የብርዕና አገዳ ሰብሎች አንፃር እጅግ ዝቅ ያለ ነው፡፡ ያለንን የጤፍ ዝርያ ብዝሃነት ማጥናት ግን እነኚህን የምርት ማነቆዎች ተቋቁመው የተሻለ ምርት ሊሰጡ የሚችሉ ዝርያዎችን ለመለየት ዕድል ይፈጠራል፡፡ የዚህ ጥናት ዓላማ ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ 188 የጤፍ ብዝሃ-ዘሮችን በሆለታና በደብረ ዘይት ምርምር ማዕከል ውስጥ በኮምፕሊቲሊ ረንዶማይዝድ ብሎክ ዲዛይን ዘርቶ በመገምገም ያላቸውን የዝርያ ተለያይነት፣ ብዝሃነትና ስብጥር ምን እንደሚመስል ለማወቅ ነበር፡፡ በዚህ ጥናት መረጃዎችን ለመተንተን የቫሪያንስ፣ የክላስተር እና የፕሪንሲፓል ኮምፖንነት ትንተና ዘዴዎች ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ የዚህ ትንተና ውጤት በስብስቦቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የመድረሻ ጊዜ (ፌኖሎጂ)፣ የምርታማነትና የምርት ኮምፖነንት፣ የግሽበት እና የሞርፎሎጂ ባህሪያት ተለያይነት እንዳለ ይጠቁማሉ፡፡ በተጨማሪ የክላስተር ትንተና በጥናቱ ውስጥ የተካተቱ 188 ብዝሃ-ዘሮችን ወደ ስድስት ቦታ ሲመድባቸው፤ 14 ፖፑለሽኖች ደግሞ ወደ አራት ምድብ ከፍሏቿዋል፡፡ እነዚህ ቡድኖች ግን በማህበረሰብ ከቦታ ቦታ ዝውውር የተነሳ የግድ የዘረ-መል ዝምድናንና የአካባቢ ቅርበትን መሰረት ያደረጉ ብቻ ሆነው አልተገኙም፡፡ የዚህ ጥናት ውጤት በአጠቃላይ ወደፊት በጤፍ ምርምር ማሻሻያ ውስጥ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው የብዝሃ-ዘር ተለያይነት እንዳለ ይጠቁማል፡፡
Abstract
A total of 188 tef genotypes including 144 pure lines selected from germplasm collection, 35 released varieties, eight breeding lines and their parents were evaluated in three replications at two locations in Ethiopia. The objectives were to assess the magnitude and pattern of phenotypic diversity in tef genotypes obtained from various sources in Ethiopia. Combined analysis of variance revealed highly significant (P < 0.01) differences among genotypes, locations and genotype by environment interaction for all studied traits. Thus, wide ranges of variations were observed for days to heading (40.3 to 60.8 days) and maturity (101 to 122.5 days), plant height (60.7 to 107.1 cm), panicle length (19.5 to 39.5 cm), number of fertile tillers per plant (2.1 to 5.5) and spikelet per panicle (156.7 to 441.7), 1000 kernel weights (20.7 to 33.0 mg), grain yield (3.7 to 7.3 t/ha) and lodging index (44.7 to 79.3%). Cluster analysis revealed six distinct clusters of 188 individual tef genotypes while the 14 populations were grouped into four distinct clusters. In general, existence of sufficient level of genetic variation was revealed for future use in tef improvement.