Main Article Content

Comparative Study of Production and Reproductive Performance of Various Strains of Chicken Parent Layers Raised in Floor Pens


Dawud Ibrahim
Gebeyehu Goshu
Wondmeneh Esatu
Gashahun Bino
Tesfaye Abebe

Abstract

 አህፅሮት

ጥናቱ የሚያተኩረው አምስት ወላጅ ዶሮዎች በአውሮፓ የተዳቀሉ እና አንድ ከሀገር ውስጥ ለንፅፅር ተወስደው ለምርትና እና ምርታማነት በኢትዮጵያ ሁኔታ ተገመገሙ፡፡ ወላጅ ዶሮዎቹም ዶሚናነት ቀይ፣ ዶሚናነት ሰሴክስ፣ ኮኮክ፣ ሎህማን ብራውን እና ሎህማን ጥምር ነበሩ፡፡ ስራው የተሰራው በአንድ ክፍል በወል ላይ ሲሆን፣ አነኚህ ዶሮዎቸ የተገመገሙበት መስፈርት፡ በምግብ አወሳሰድ፣ በክብደት፣ በዕንቁላል ምርት፣ በዕንቁላል ይዘት፣ በዕንቁላል መዳበር፣ በዕንቁላል መፈልፈል እና በሌሎችም ከነባራዊ ሁኔታ ጋር ተላምዶ መኖር ወይም መሞት ነበር፡፡ በአጠቃላይ ለዚህ ስራ 600 ሴት እና 75 ወንድ ወላጅ ዶሮዎች በሶስት ጊዜ ድግግሞሽ በዝርያ በአንድ ቤት ውስጥ በcompletely randomized design መሰረት ተሰራጩ፡፡ ይህ ስራ ከፍተኛ የሆነ በዝርያ፣ በዕድሜ እና በሁለቱም ማለትም በዝርያና ዕድሜ ላይ ልዩነቶች የታየው በአመጋገብ፣ በክብደት፣ በዕንቁላል ምርት፣ በዕንቁላል ይዘት፣ በዕንቁላል መዳበር፣ በዕንቁላል መፈልፈል እና በሌሎችም መመዘኛ ነበር፡፡ በዚህ ሙከራ በአማካይ ከፍተኛ የሴት ክብደት በዶሚናነት ቀይ፣ በመቀጠልም በዶሚናነት ሰሴክስ እና በኮኮክ ላይ ተመዝግቧል፡፡ ዝቅተኛ ክብደት ደግሞ በሎህማን ብራውን እና በሎህማን ጥምር ላይ ነበረ፡፡ በወንዶች ላይ ደግሞ በሎህማን ጥምር ላይ ከፍተኛ ክብደት ሲመዘገብ በመቀጠል ደግሞ በዶሚናነት ቀይ፣ በኮኮክ፣ ዶሚናነት ሰሴክስ ሲሆን፣ ዝቅተኛ ክብደት ደግሞ በሎህማን ብራውን ተመዝግቧል፡፡ ይህ በሎህማን ጥምር ወንድ ወላጅ ዶሮ ላይ የታየው ከፍተኛ ክብደት የስጋ ዶሮ ደም ስላለበት ሲሆን ለሌሎቹ ከዝቅተኛ ክብደት ግን ከሎህማን ጥምር ጋር ሲነፃፀር የተመዘገበበት ምክንያት መደበኛ የዕንቁላል ጣይ ዶሮ ደም ስላላቸው ነበር፡፡ በአማካይ ከፍተኛ የዕለታዊ የምግብ አወሳሰድ የተመዘገበው በዶሚናነት ቀይ እና ዶሚናነት ሰሴክስ በተለይ ከ17 እስከ 24 እና ከ25 እስከ 32 የሳምንት ዕድሜ ክልል ሲሆን በመቀጠልም በኮኮክ ላይ ተመዝግቧል፡፡ ነገር ግን በሎህማን ብራውን እና በሎህማን ጥምር ላይ ዝቅተኛ የዕለታዊ የምግብ አወሳሰድ ተመዝቧል፡፡  በአማካይ ከፍተኛ የዕንቁላል ምርት በሎህማን ብራውን እና በሎህማን ጥምር ላይ ሲታይ በመቀጠል ከፍተኛ ምርት የተመዘገበው በዶሚናነት ቀይ፣ ዶሚናነት ሰሴክስ እና በኮኮክ ላይ ነበር፡፡ በአማካይ ከፍተኛ የዕንቁላል የመዳበር እና የመፈልፈል በኢንኩቤተር ከታቀፈው ዕንቁላል የተመዘገበው በዶሚናነት ቀይ፣ ዶሚናነት ሰሴክስ፣ በኮኮክ እና በሎህማን ብራውን በመቀጠልም የዕንቁላል የመዳበር እና የመፈልፈል በኢንኩቤተር ከታቀፈው ዕንቁላል ሲታይ ዝቅተኛው ሆኖ የተመዘገበው በሎህማን ጥምር ላይ ነበር፡፡ ይህ ዝቅተኛ የመዳበር እና የመፈልፈል በኢንኩቤተር ከታቀፈው ዕንቁላል በሎህማን ጥምር ላይ የታየው ሙከራው በተካሄደበት ወቅት በሙሉ ነበር፡፡ በአጠቃላይ በዚህ  በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ላይ በተካሄደው የምርምር ሙከራ ጊዜ በተወሰደው የመገምገሚያ መስፈርት ማለትም በአመጋገብ፣ በክብደት፣ በዕንቁላል ምርት፣ በዕንቁላል ይዘት፣ በዕንቁላል መዳበር፣ በዕንቁላል መፈልፈል እና በሌሎችም መሰረት ከከፍተኛ ወደ ዝቅተኛ ምርትና ምርታማነት ሲቀመጡ፡ ሎህማን ብራውን፣ ኮኮክ፣ ዶሚናነት ቀይ፣ ዶሚናነት ሰሴክስ እና ሎህማን ጥምር ነበሩ፡፡           

Abstract

Five Parent Stocks (PS) bred by European companies, and one local PS, were evaluated for their production and reproductive performance under typical conditions in Ethiopia. The PSs were Dominant red Barred (DR), Dominant Sussex (DS), Koekoek (KK), Lohmann Brown (LB) Lohmann-Dual (LD), and reared in floor pensup to 60 weeks of age, were evaluated for feed intake, body weight, egg production, egg quality, fertility, hatchability, and mortality. A total of 600 females and 75 males were kept in three replicated pens per strain and distributed in a house using completely randomized design. There were significant (P<0.05) effects of strain, age and strain by age interactions at all stages of the laying phases in terms of feed intake, fertility, hatchability, body weight of females and  males, and egg production. Significantly, highest average female body weight was recorded in DR, followed by DS and KK. The lowest average female body weights were recorded in LD and LB at all ages of the laying phases.Among the average male body weight of LD was significantly higher than other strains, followed by DR, KK and DS, the lowest average male body weights were recorded in LB during laying phase. This (LD) superiority was from the dwarf (homozygous dw/dw) meat-type line of LD. The other male strains were from the layer-types and hence lowest in body weight during the laying stages compared to that of LD male.Significantly higher average daily feed intakes were recorded in DR and DS than other PS in week 17 to 24 and 25 to 32, followed by the KK, while the lower average feed intakes were recorded in LB and LD. The average egg production of LB and LD were significantly higher than the rest, followed by KK, DS and DR. DR, DS, KK and LB were higher in egg fertility and hatchability per set eggs, followed by LD. The present result clearly indicated that the LD was poor in fertility (%) and hatchability (%) per set eggs at all stages of the laying phases. Therefore, LB, KK, DR, DS and LD were ranked 1 to 5, respectively, top to lowest in feed consumption, body weight, egg production, and reproductive performance when raised in floor pens management in Southern part of Ethiopia.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie