Main Article Content

Assessment on Feed Resources, Feeding Practices and Major Productive and Reproductive Performances of Smallholder Dairy Farms Selected from Districts in Oromia and Amhara Regions of Ethiopia


Kitaw Getu
Getenet Assefa
Getachew Animut

Abstract

አህፅሮት

ይህ የመስክ ጥናት የተካሄደው2009 .ም ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በተመረጡ የሰበታና በደሌ ከተሞች እንዲሁም ከአማራ ክልላዊ መንግስት በተመረጠ የደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ ጥናቱ በአጠቃላይ 195 የከተማ ወተት ከብት አርቢዎችን ያሳተፈ ሲሆን ዝርዝር ዓላማዎቹም በተመረጡት ከተሞች ውስጥ ለወተት ከብቶች ለመኖነት የሚውሉ የመኖ ዓይነቶች ከነአመጋገብ ሥርዓታቸው በመለየት የዲቃላ ወተት ከብቶቹን የምርማነት እና የሥነ-ተዋልዶ ደረጃቸውን ማወቅ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ተጠያቂ አርቢዎች ለወተት ከብት እርባታ፤ ለመኖ እና ሰብል ምርት ልማት ሊውል የሚችል  0.57±0.04፣ 0.15±0.03፣ 0.72±0.06 ሄክታር በተጠያቂ አርብቶ-አደር ደረጃ በግል፣ በኪራይ የተገኘ እና ጠቅላላ የመሬት ይዞታ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተነፃፃሪ አርቢዎቹ ከአጠቃላይ አማካይ የመሬት ይዞታቸው ለዓመታዊ የሰብል፤ግጦሽ እና የተፈጥሮ ሣር ድርቆሽ ልማት ያዋሉት መሬት በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በ7.51 ትሮፒካል የከብቶች ልኬት በአርቢ ደረጃ ሲታይ የወተት ከብቶች ይዞታ ከአጠቃላይ የእንስሳት ኃብት 79.14 በመቶ እንደሚሆን ለማስላት ተችሏል፡፡ ከኮርማዎችና ሴት ታዳጊ ጥጆች ውጭ በተነፃፃሪ በሰበታ የሚገኙ የወተት ከብት አርቢዎች በዛ ያሉ ዲቃላ የወተት ከብቶች፣ ታላቢ ላሞች እና የርቢ ጊደሮች እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሌላ መልኩ በሰበታ የሚገኙ አርቢዎች በዕለታዊ እና በአነድ አለባ ወቅት የሚያገኙት የወተት ምርት ከሌሎቹ የተሻለ ሲሆን በጥጃ የውልደት ጊዜ ርዝማኔ እጥረት በበደሌ ከተማ የሚገኙ አርቢዎች የተሻሉ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ መኖን በተመለከተ በሁሉም ጥናቱ ያካተታቸው ከተሞች የተፈጥሮ ሣር ድርቆሽ ሣር እና የግብርና ተረፈ-ምርት መኖዎች በዋነኛነት በመሰረታዊ መኖነት ጥቅም ላይ ሲውሉ ተረፈ-ግብርና እንደስትሪ መኖዎችና ከባህላዊ የመጠጥ ምርት (የአረቄና ጠላ አተላ) የሚገኙ መኖዎች በስፋት ለወተት ከብቶች የድጎማ መኖነት በስፋት መዋላቸውን በጥናቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጥናቱ ከተካሄደባቸው ከተሞች በአማካይ 73.85 በመቶ የሚጠጉ አርቢዎች ዲቃላ የወተት ከብቶቻቸውን በቤት ውስጥ አስረው የሚቀልቡ ሲሆን 26.15 በመቶ የሚጠጉት ደግሞ በከፊል የቤት ውስጥ እንዲሁም በከፊል የግጦሽ አመጋገብ ሥርዓት እንደሚከተሉ ለማስተዋል ተችሏል፡፡ የመጠጥ ውኃን በተመለከተ 64.35 በመቶ የሚጠጉት አርቢዎች ከቧንቧ የሚገኝ የመጠጥ ውኃን ለከብቶቻቸው የሚጠቀሙ ሲሆን 25.12 በመቶዎቹ ደግሞ ከወራጅ ወንዝ የሚገኝ ውኃን እንደሚጠቀሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ጥናቱ በተካሄደባቸው ከተሞች ለርባታ እና መኖ ልማት ሊውል የሚችል በቂ መሬት እጦት፣ ንፁህ እና በቂ የመጠጥ ውኃ እጥረት፣ በሣይንስ የተደገፈ የወተት ከብቶች አረባብ ዘዴ ሥልጠና ያለመኖር፣ የመረጃ አያያዝ እጦት፣ የተረፈ-ግብርና እንደስትሪ የድጎማ መኖ እና ሠው-ሰራሽ የማዳቀያ ዘዴዎች ያለመገኘት ወይም የአቅርቦት ዋጋቸው ውድ መሆን ወዘተ. ለአርቢዎቹ ስኬት ከፍተኛ ማነቆ መሆናቸውን ጭምር በዚህ ጥናት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡     

 

Abstract

The study was conducted in Sebeta and Bedele towns, Oromia regional state and Debre Berhan town, Amhara regional state, Ethiopia, between October-January, 2016/17. The objective of the study was; to assess the feed resource base, feeding practices and major productive and reproductive performances of selected urban smallholder dairy farms in study districts. A total of 195 household (HH) respondents were participated in the survey study. The survey result indicated that respondents on average owned about 0.57±0.04, 0.15±0.03, 0.72±0.06 ha of private, rented-in and total land respectively, with no difference among the dairy urban centers. Land use pattern on the other hand indicated as more land was allocated to annual crop production followed by dry season grazing and hay making (P<0.05).With an overall mean of 7.51 TLU/HH, dairy cattle species accommodated more than 79.14% of the total livestock holding per HH in the areas. Except for breeding bulls and female calves, HH respondents in Sebeta town had significantly (P<0.05) higher number of total crossbred cattle population, milking cows and heifers compared to dairy farmers in Bedele and Debre Berhan towns. On the other hand, while dairy cows at Sebeta had higher daily and lactation milk yield (P<0.05), crossbred cows in Bedel town exceeded the other two in calving intervals (P<0.05). In terms of basal and supplemental feed utilizations, while grass hay and crop residues were the prominent basal feeds used, agro-industrial and local brewery waste dominated supplemental feed utilization in the study districts. The majority of the HH respondents (73.85%) in the study districts were practicing indoor feeding (P<0.05) while only 26.15% (P<0.05) of the HH respondents practiced partial grazing. Among the watering sources tap water (overall avg. respondents = 64.35%) followed by river streams (Overall avg. respondents = 25.12%) were the most dominantly used drinking water sources in studied districts (P<0.05). Major challenges observed in the survey areas were: shortage of land for feed production and luck of sustainable drinking water sources; luck of need based regular trainings; absence of recording keeping; poor access to agro-industrial feed supplements and AI etc.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie