Main Article Content

Effect of Cattle Breed on Milk Composition in the same Management Conditions


Ewonetu Kebede

Abstract

አህፅሮት

ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በተመሳሳይ አያያዝ ሁኔታ ውስጥ የወተት ከብቶች ዝርያ በወተት ምርት ውህደት ወይም ንጥረ ነገር ላይ የሚያስከትለውን ውጤት ለማየት ነው:: ለዚህ ጥናት 32 የተለያዩ ዝርያ ያላቸው የወተት ከብቶች ሲሆኑ እነሱም ሆልስቲን ፍርዥያን፣ ጀርሲ፣ የኢትዮጵያን ኦጋዴን እና የሆሮ  የድብልቅ ዝርያዎች ከእያንዳንዳቸው 8 ከብቶች በመጀመሪያ የእልበት እና በተመሳሳይ የውልጃ ደረጃ ያሉ ሆን ተብሎ ከተመረጡ 60 ተከታታይ ቀናት የክትትል ስራ ተደርጓል:: በዚህ ጥናት ውስጥ ከእያንዳንዱ ከተመረጡ ከብቶች 100 ሚሊ የወተት ናሙና 3 ጊዜ 20 ቀን ልዩነት ተወስዶ በቤተሙከራ ውስጥ የወተቱን ቅባትነት፣ ገንቢ ንጥረ ነገር፣ ማዕድን፣ የውሃ መጠን፣ ቅባት የሌለው ንጥረ ነገር፣ አጠቃላይ ደረቅ ንጥረ ነገር፣ የስኳር እና የወተት ዩሪያ ናይትሮጂን ይዘት በጥልቀት ተመርምሯል:: የእነዚህ ከብቶች ዝርያ የወተት ንጥረ ነገር ከዚህ በፊት ሌሎች ተመራማሪዎች ሰርተው ባስቀመጡት እርከን መጠን ውስጥ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል:: በአጠቃላይ የዚህ ጥናት ግኝት ውጤት የሆልስቲን ፍሪዥያን ከብቶች  50 ፐርሰንት የደም እርከን 25 ሆሮና 25 ጀርሲ ጋር ተዳቅሎ ከኢትዮጵያው ኦጋዴን 50 ፐርሰንት ጀርሲና ሆሮ ሲዳቀል ውጤቱ ተመጣጣኝ ነው:: ስለዚህ የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸው ከብቶች ከውጭ ዝርያ ካላቸው ከብቶች ጋር በተለያየ የደም እርከን ሲዳቀሉ የውጭ ከብቶች የወተት ስኳር እና ቅባት የሌለው ንጥረ ነገር በስተቀር ሌሎች የወተት ንጥር ነገሮች መጠናቸው ጨምሯል:: በመጨረሻ ይህ ጥናት ኦጋዴን እና ሆሮ ዝርያ ያላቸው የኢትዮጵያ ከብቶችን ብቻ ላይ የተደረገ በመሆኑ ወደፊት ሌሎች የተዳቀሉ አገር በቀል የኢትዮጵያ ዝርያ ያላቸው ከብቶች ላይ  ሰፋ ያለ ጥናት እንዲደረግ እጠቁማለሁ::

 

Abstract

 

This study evaluated the effect of bovine breed on milk composition under the same environmental conditions. Thirty two dairy cattle breeds of Holstein Friesian, Ethiopian Ogaden cattle, Jersey x Horro crosses, and Holstein Friesian x Jersey x Horro crosses were used in the study. Eight cows in early lactation stage and with the same parity were purposively selected from each breed and monitored for 60 days. Animals were maintained under intensive systems and all consumed on the same diet. 100ml milk samples collected three times every twenty days from each milking cows and separate analysis were done for each breed in duplicate using a MilkoScanTM FTl to determine fat, protein, ash, water, SNF), TS, lactose, and MUN. The major content of milk for breed in this study is within the range for the milk composition standard requirement for bovine. The breed had a significant effect on water (p ≤ 0.0001), Protein (p ≤ 0.05), TS (p ≤ 0.05), fat (p ≤ 0.05), MUN (p ≤ 0.001) and ash (p ≤ 0.0001) content of milk. The study finding revealed that the milk content of Holstein Frisian at 50 percent blood level cross with 25 percent Horro and 25 percent Jersey cattle was comparable to the milk content of Ethiopian indigenous pure Ogaden cattle and Jersey and Horro crosses at 50 percent blood levels. This study suggesting that crossbreeding schemes of indigenous Horro cattle breeds with Holstein and Jersey cows at different blood level had a significant effect on milk content of bovine except lactose, FFA and SNF. Further studies are needed to better understand of genetic aspects of other cross breed Ethiopian indigenous cattle on milk composition.


Journal Identifiers


eISSN: 2415-2382
print ISSN: 0257-2605
 
empty cookie