Main Article Content

የዓለም አቀፍ የሰብአዊነት ሕግጋትና መርኆች በዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ የጦር ሜዳ ውሎዎችና ውሳኔዎች ውስጥ የነበራቸው ቦታ


ነጋ መኮንን

Abstract

በኢትዮጵያ የተደረጉ ጦርነቶችን፣ የነገሥታት የጦር ሜዳ ውሎዎችንና ውሳኔዎችን አስመልክቶ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የውጭ አገር ጻሕፍት በአብዛኛው በአንድ ነገር ይስማማሉ፡፡ ይህም የነገሥታት ፍርዶች በተለይም የጦር ሜዳ ውሎዎች በጭካኔ የተሞሉና ኢሰብአዊ እንደሆኑ አድርገው ሲያቀርቡ ይስተዋላል፡፡ በታሪክ ወደኋላ መለስ ብለን የአውሮፓዊያንን የጦር ሜዳ ታሪክ ብንፈትሽ እጅግ በጣም አስቀያሚና ዘግናኝ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ የሩቁን ትተን በአንጻሩ የቅርቡን እ.አ.አ. በ1859 ዓ.ም በፈረንሳይ፣ ሰርዲኒያና ኦስትሪያ መካከል የተደረገውን የሶልፈሪኖ ጦርነት አንኳ ብንወስድ አሰቃቂነቱንና ኢሰብአዊነቱን ከሄነሪ ዱና ማስታወሻ በሚገባ አንረዳለን፡፡ A Memory of Solferino የሚለውን መጽሐፍ ያነበበ ጦርነት ይረግማል እስኪባል ድረስ የሶልፈሪኖ ጦርነትን አሰቃቂነት ሄነሪ ዱና ጽፏል:: የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር እንዲቋቋም የታሪክ አጋጣሚ እንዲፈጠር በዋናነት አስተዋጾ ያደረገውም ይህ ጦርነት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ርስበርስም ይሁን ከውጭ ወራሪ ጋር የተደረጉ ጦርነቶች ዘግናኝ የሆኑና የሰው ልጅን ለከፋ መከራ የዳረጉ እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በአንጻሩ ግን ርህራሄን መሠረት ያደረጉ፣ አስተዋይነት የተሞላባቸው፣ ለሰው ልጅ ክብር የሰጡ የነገሥታት የጦር ሜዳ ውሎዎችንና ውሳኔዎችን እናገኛለን፡፡
ጦርነትን ጨምሮ ትላንት የተፈጸመ አንድ ነገር መመዘንና መለካት ያለበት በዛሬ አስተሳሰብ፣ አስተምህሮ፣ መስታውትና ሕግ መሆን የለበትም፡፡ ሁሉም ትላንት የሆነ ነገር መታየት ያለበት በራሱ በትላንት ዐይንና አስተሳሰብ ነው፡፡


Journal Identifiers


eISSN: 2709-5827
print ISSN: 2306-224X
 
empty cookie