Main Article Content
የይቅርታ ሕጎችና አፈጻጸማቸው በባሕር ዳር ማረሚያ ቤት
Abstract
ይቅርታ ወንጀልን ፈጽመው ጥፋተኛ በተባሉ ወንጀለኞች ላይ የተወሰነው የወንጀል ቅጣት በአስፈጻሚው የመንግስት አካል አማካኝነት የሚቀነስበት ወይም የሚሻሻልበት ሥርዓት ነው፡፡ መንግስት ወንጀለኞች የሚያሳዩትን የባህሪ መሻሻልና በጥፋታቸው መጸጸት መነሻ በማድረግ ከተወሰነባቸው ቅጣት ውስጥ ከፊሉ ቀሪ እንዲሆንላቸው በማድረግ የይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ ይህም በብዙ አግሮች የተለመደና አሰራሩም በህግ የሚመራ ነው፡፡ በዚህ ጥናት ውስጥ የይቅርታ አሰጣጥ ሥርዓትን በህግ እንዲመራ በማድረግ ይቅርታ የሚሰጡ የጥቂት አገሮች ተሞክሮ ተዳስሷል፡፡ ኢትዮጵያም ይቅርታን በፌዴራልና በክልል የህግ ማአቀፎች እንዲካተት በማድረግ ለታራሚዎች በየጊዜው ይቅርታን ታደርጋለች፡፡
የዚህ ጥናት አላማ የባሕር ዳር ማረሚያቤት የይቅርታ አሰጣጥ ሥርዓት ከኢፌዴሪና ከአማራ ክልል ሕግጋት አንጻር ምን እንደሚመስል መመርመር ነው፡፡ የጥናት ዘዴው አይነታዊ ሲሆን በባሕር ዳር ማረሚያቤት በይቅርታ አሰጣጥ ሂደት የሚስተዋሉትን የሕግና የአፈጻጸም ችግሮች ለይቶ የመፍትሄ ሃሳቦችን በጥናቱ ለማመልከት ጥረት ተደርጓል፡፡
በጥናቱም በአብክመ የይቅርታ አሰጣጥ አዋጅና መመሪያ ውስጥ የሰፈሩ የይቅርታ ቅድመሁኔታዎች ግልጽነት የጎደላቸውና ለአፈጻጸም አስቸጋሪ መሆናቸው ከመረጋገጡም በላይ በነዚህ የክልል ሕግጋትና በፌዴራል ሕጎች መካከል የሚስተዋሉት መጣረስና ልዩነት ተለይተው የመፍትሄ ሃሳቦች ተጠቁመዋል፡፡