Main Article Content

Case Comment የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሕግ የተፈፃሚነት ወሰን ከጊዜ አንፃር᎓- በፍርዶች ላይ የቀረበ ትችት


Berihun Adugna

Abstract

በተለይ ከውርስ አንጻር በቀድሞዎቹ የገጠር መሬት ሕጎች እና አሁን በስራ ላይ ባሉት ሕጎች መካከል ሰፊ ልዩነቶች አሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ የቀድሞዎቹ ሕጎች (ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 89/1989ወይም አዋጅ ቁጥር 46/1992) ስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ሳይናዘዝ የሞተ ሰው የገጠር መሬትይዞታ በውርስ ሊተላለፍ የሚችለው እንዴት ነው? ወራሾች በወቅቱ ውርሱን ያልጠየቁ ሆኖ ነገርግን አዋጆቹ ከተሻሩ በኋላ አሁን ስራ ላይ ባለው አዋጅ ቁጥር 133/1998 እና ደንብ ቁጥር 51/1999መሠረት ክስ ቢያቀርቡ ፍርድ ቤቶች ጉዳዩን እልባት መስጠት ያለባቸው በየትኛው ሕግ መሰረትነው? የሚሉ ጥያቄዎች አዘውትረው ይነሳሉ፡፡ በዚህ ረገድ በአማራ ክልል ፍርድ ቤቶች ከፍትሐብሔር ሕጉ የውርስ መከፈት ጽንሰ ሀሳብ በመነሳት የገጠር መሬት ውርስ የሚጠይቅ ሰው ባለይዞታው በሞተበት ዘመን ከሚኖረው አጠቃለይ የማውረስ መብት አንፃር እየታየ ሲሰራቆይቷል፡፡ሆኖም የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በቅርቡ በሁለት ጉዳዮች ላይየመሬት ባለይዞታው የሞተበት ጊዜ ግምት ውስጥ ሳይገባ ክርክሩ መታየት ያለበት አሁን ስራ ላይባሉት ሕጎች መሠረት ነው የሚል አስገዳጅ ትርጉምና ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ይህ ትርጉም ከሕጎችተፈጻሚነት ወሰን አንፃር አከራካሪ ሆኗል፡


Journal Identifiers


eISSN: 2709-5827
print ISSN: 2306-224X